Unit 2: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 43
Listen to find out how to ask how long a journey takes.
ጉዞ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ እንዴት እንደሚጠየቅ ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
How long does it take?
Listen to find out how to ask how long a journey takes.
ጉዞ ምን ያህል ጉዞ እንደሚወስድ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ያዳምጡና መልመጃውን ይመልሱ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደምናቀርብበት Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል ወደ አንድ ቦታ ለመሄድ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ስለመጠየቅ ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ወደ አንድ ቦታ ለመጓዝ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ሲወያዩ ያዳምጡ።
Sian
I want to go to Newcastle. How long does it take?
Phil
It takes about eight hours by bus.
ምህረተስላሴ
ንግግራቸውን ካልተረዱት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ወደ ኒውካስል መሄድ እንደምትፈልግ 'want' ነው የተናገረችው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I want to go to Newcastle.
ምህረተስላሴ
ከዚያ ምን ያህል ጊዜ 'how long' እንደሚወስድ 'take' ጠየቀች።
How long does it take?
ምህረተስላሴ
ሁለተኛው ተናጋሪ በአውቶብስ 'bus' ስምንት ሰዓት 'eight hours' ገደማ 'about' እንደሚወስድ ተናገረ። የሚወስደውን ጊዜ በእርግጥ ካላወቅን 'about'ን መጠቀም እንችላለን። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
It takes about eight hours by bus.
ምህረተስላሴ
በሌላ መጓጓዣ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድም መናገር ይችላሉ። 'Train' በባቡር፣ 'car' በመኪና፣ 'plane' በአውሮፕላን እና በእግር ጉዞ 'walk' ጭምር ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ መናገር ይችላሉ።
It takes about seven hours by train.
It takes about six hours by car.
It takes about thirty minutes to walk.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች ወደተለያዩ ቦታዎች ለመሄድ ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልግ ሲጠያየቁ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
ዛክ ወደ ሊድስ መሄድ ይፈልጋል። ቻርልስ ጉዞው በባቡር 'train' ሁለት ሰዓት እንደሚወስድ ነገሮታል።
I want to go to Leeds. How long does it take?
It takes about two hours by train.
ኤሪካ ወደ ካርዲፍ መሄድ ትፈልጋለች። አንጄላ ጉዞው በመኪና 'car' ሦስት ሰዓት እንደሚወስድ ነገረቻት።
I want to go to Cardiff. How long does it take?
It takes about three hours by car.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ እስኪ ንግግሩን ደግመን እንሞክረው። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
I want to go to Newcastle.
I want to go to Newcastle.
How long does it take?
How long does it take?
It takes about eight hours by bus.
It takes about eight hours by bus.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ ትርጉማቸውን ይበሉ።
ወደኒውካስል ለመሄድ እፈልጋለሁ።
I want to go to Newcastle.
ምን ያህል ሰአት ይወስዳል?
How long does it take?
በአውቶብስ ስምንት ሰዓት ይወስዳል።
It takes about eight hours by bus.
ምህረተስላሴ
በጣም ግሩም፤ አንድ ነገር ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ መጠየቅና መልስ መስጠት ተምረዋል። አንድ ነገር ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ በመናገር ለመጀመሪያዋ ተናጋሪ ምላሽ እየሰጡ ልምምድ ያድርጉ።
I want to go to Newcastle. How long does it take?
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ውይይት አንዴ ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sian
I want to go to Newcastle. How long does it take?
Phil
It takes about eight hours by bus.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ነገሮች ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስዱ በእንግሊዝኛ መጠየቅና መመለስ ችለዋል። የተማሩትን መለማመድን ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ነገሮች ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስዱ በእንግሊዝኛ በመጠየቅ ልምምድ ያድርጉ። ለተጨማሪ የኢንሴንሻል እንግሊሽ መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
ከጊዜ ጋር የምንጠቀመው ቃል የትኛው ነው?Question 1 of 3
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
ጊዜ መውሰድ የሚል ትርጉም የሚሰጠው ቃል የትኛው ነው?Question 2 of 3
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
የመጓጓዣ መንገድን ለማስተዋወቅ የምንጠቀምበት ቃል የትኛው ነው?Question 3 of 3
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ ክፍላችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
I want to go to ______.
ወደ ______ መሄድ እፈልጋለሁ።How long does it take?
ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?It takes about ______ ______ by bus.
በአውቶብስ ______ ይወስዳል።