Unit 2: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 42
Listen to find out how to buy a ticket.
እንዴት ትኬት እንደሚገዛ ለማወቅ ያዳምጡ።
Activity 1
Can I have a ticket to…?
Listen to find out how to buy a ticket.
እንዴት ትኬት መግዛት እንደሚቻል ለማወቅ ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ያዳምጡና መልመጃውን ይመልሱ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደምናቀርብበት Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል እንዴት የአውቶብስ ትኬት መቁረጥ እንደሚቻል ይማራሉ።
በአውቶብስ መናሀሪያው ውስጥ ያለውን ንግግር ያዳምጡ።
Sam
Hi, can I have a ticket to Birmingham, please? I want to go today.
Phil
Here you are. That’s twenty-five pounds, please.
ምህረተስላሴ
ንግግሩ ቢያስቸግርዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ወደ በርሚንግሃም ለመሄድ ትኬት 'ticket' ጠይቃለች። የሆነ ነገር እንዲሰጠን ለመጠየቅ “ማግኘት እችላለሁ?” 'Can I have…?' የሚለውን ሐረግ እንጠቀማለን።
Hi, can I have a ticket to Birmingham, please?
ምህረተስላሴ
'Today' ዛሬ መሄድ እንደምትፈልግ ነው የተናገረችው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I want to go today.
ምህረተስላሴ
ሁለተኛው ተናጋሪ ደግሞ “ይሄው” 'here you are' አለ፤ ይሄንን አባባል አንድ ነገር ስንሰጥ እንጠቀምበታለን።
Here you are.
ምህረተስላሴ
ትኬቱ 'twenty-five pounds' ሃያ አምስት ፓውንድ እንደሚያስከፍል ተናገረ። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
That’s twenty-five pounds, please.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ወደተለያዩ ቦታዎች ለመሄድ ትኬት የሚገዙ ሰዎችን ያዳምጡና እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
ጄኮብ አርብ 'Friday' ወደማንቼስተር መሄድ ይፈልጋል።
How can I help you?
Hi, can I get a ticket to Manchester, please? I want to go on Friday.
Here you are. That’s twenty pounds, please.
ኬሊ ነገ 'tomorrow' ወደግላስጎው መሄድ ይፈልጋል።
Hi, can I get a ticket to Glasgow, please? I want to go tomorrow.
Here you are. That’s sixty pounds, please.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ አሁን ንግግሩን እንሞክረው። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
Can I have a ticket to Birmingham, please?
Can I have a ticket to Birmingham, please?
I want to go today.
I want to go today.
Here you are.
Here you are.
That’s twenty-five pounds, please.
That’s twenty-five pounds, please.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ ትርጉማቸውን ይበሉ።
እባክዎን የበርሚንግሃም ትኬት ይሰጡኛል?
Can I have a ticket to Birmingham, please?
ዛሬ መሄድ ነው የምፈልገው
I want to go today.
ይሄው
Here you are.
ሃያ አምስት ፓውንድ ነው
That’s twenty-five pounds, please.
ምህረተስላሴ
በጣም ግሩም፤ እንዴት የአውቶብስ ትኬት እንደሚጠይቁ አውቀዋል። የአውቶብስ ትኬት ሻጭ ሆነው ለመጀመሪያዋ ተናጋሪ ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ።
How can I help you?
Here you are. That’s twenty pounds, please.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ውይይት አንዴ ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sam
Hi, can I have a ticket to Birmingham, please? I want to go today.
Phil
Here you are. That’s twenty-five pounds, please.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን በእንግሊዝኛ የአውቶብስ ትኬት መጠየቅ ችለዋል። የተማሩትን መለማመድ አይርሱ። በእንግሊዝኛ የአውቶብስ ትኬት በመጠየቅ ከጓደኛዎ ጋር ይለማመዱ። ለተጨማሪ የኢንሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል በማስቀመጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
ትኬት/ ካርኒ ማግኘት እችላለሁ?
4 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
‘Can’ የመጀመሪያው ቃል ነው።Question 1 of 4
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
‘I’ የመጀመሪያው ቃል ነው።Question 2 of 4
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
'Here' የመጀመሪያው ቃል ነው።Question 3 of 4
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
'That's' የመጀመሪያው ቃል ነው።Question 4 of 4
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዷችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Can I have a ticket to ______, please?
እባክዎን የ______ ትኬት ማግኘት እችላለሁ?I want to go today.
ዛሬ መሄድ እፈልጋለሁ።Here you are.
ይሄውThat’s ______ ______, please.
ዋጋው ______ ነው።