유닛 1: Essential English Conversation
유닛 고르세요
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
세션 33
Listen to find out how to ask people what time they have breakfast.
ሰዎች ቁርስ ስንት ሰዓት ላይ እንደሚበሉ ለመጠየቅ ይሄንን ያዳምጡ።
세션 33 점수
0 / 3
- 0 / 3엑티비티 1
엑티비티 1
What time do you have breakfast?
Listen to find out how to ask people what time they have breakfast.
ሰዎች ቁርስ ስንት ሰዓት ላይ እንደሚበሉ ለመጠየቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምፁን ያዳምጡ እና መልመጃውን ይሞክሩ።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ዘሩባቤል እባላለሁ። በዛሬው ክፍል ስንት ሰዓት ላይ ቁርስ እንደሚበሉ ‘have breakfast’ እንዲሁም ስንት ሰዓት ላይ እራት እንደሚበሉ ‘have dinner’ መናገርን እና መጠየቅን ይማራሉ።
ሁለቱ ሰዎች ስለምግብ ሰዓቶቻቸው ሲያወሩ ያዳምጧቸው።
Jane
Hi Chris, when do you have breakfast?
Chris
I never have breakfast.
Jane
When do you have dinner?
Chris
I have dinner at eight forty five.
ዘሩባቤል
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ጄን ክሪስን ስንት ሰዓት ላይ ቁርስ እንደሚበላ ‘have breakfast’ ነው የጠየቅችው። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
When do you have breakfast?
ዘሩባቤል
ክሪስ ‘never’ መቼም ቁርስ እንደማይበላ ‘have breakfast’ ነው የመለሰላት። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
I never have breakfast.
ዘሩባቤል
ከዚያም ጄን ስንት ሰዓት ላይ ራት እንደሚበላ ‘have dinner’ ጠየቀችው። ስለጊዜ ጥያቄ ለማቅረብ ‘when’ እና ‘what time’ መጠቀም እንችላለን። የትርጉም ልዩነት የላቸውም። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
When do you have dinner?
ዘሩባቤል
ክሪስ ራቱን የሚበላው ‘eight forty five’ ለሶስት ሩብ ጉዳይ እንደሆነ ነገራት። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
I have dinner at eight forty five.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ምግቦችን ስንት ሰዓት ላይ እንደሚበሉ ሲነጋገሩ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
ኒክ ቁርስ የሚበላው ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ላይ ሲሆን ‘lunch’ ምሳ ደግሞ ስድስት ከሩብ ላይ ይበላል።
Hi Nick, what time do you have breakfast?
I have breakfast at six forty five.
Ok. What time do you have lunch?
I have lunch at twelve fifteen.
ዘሩባቤል
እሺ፤ አሁን ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
When do you have breakfast?
When do you have breakfast?
I never have breakfast.
I never have breakfast.
I have breakfast at eight fifteen.
I have breakfast at eight fifteen.
When do you have dinner?
When do you have dinner?
I have dinner at eight forty five.
I have dinner at eight forty five.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ቁርስ የምትበላው ስንት ሰዓት ላይ ነው
When do you have breakfast?
ቁርስ አልበላም
I never have breakfast.
ቁርስ የምበላው ሁለት ከሩብ ላይ ነው።
I have breakfast at eight fifteen.
እራት የምትበላው ስንት ሰዓት ላይ ነው?
When do you have dinner?
እራት የምበላው ለሶስት ሩብ ጉዳይ ላይ ነው።
I have dinner at eight forty five.
ዘሩባቤል
በጣም ግሩም፤ አሁን ምግብ ስንት ሰዓት ላይ እንደሚበሉ መጠየቅን እና መናገርን ችለዋል። ለጄን ምላሽ በመስጠት እና ምግብ ስንት ሰዓት ላይ እንደምትበላ በመጠየቅ ልምምድ ያድርጉ።
When do you have breakfast?
When do you have dinner?
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ውይይት ደግመው ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Jane
Hi Chris, when do you have breakfast?
Chris
I never have breakfast.
Jane
When do you have dinner?
Chris
I have dinner at eight forty five.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! አሁን የተለያዩ ምግቦችን ስንት ሰዓት ላይ እንደሚበሉ ሰዎችን በእንግሊዝኛ መጠየቅ ችለዋል። የተማሩትን መለማመድን ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና የተለያዩ ምግቦችን ስንት ሰዓት ላይ እንደምትበሉ በእንግሊዝኛ በመጠያያቅ ልምምድ ያድርጉ። ለተጨማሪ Essential English Conversation ዝግጅቶች በቀጣይ ክፍላችን ይጠብቁን። Bye!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛ መልስ በመስጠት የተማሩትን ይፈትሹ።
ቁርስ የምትበላው ስንት ሰዓት ላይ ነው?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
도움
엑티비티
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
힌트
የአንድን ነገር ጊዜ ለመጠየቅ የምንጠቀምበት ቃል ምንድን ነው?Question 1 of 3
도움
엑티비티
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
힌트
መብላት ለማለት የምንጠቀምበት ቃል ምንድን ነው?Question 2 of 3
도움
엑티비티
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
힌트
በመጀመሪያ ሰዓቱን ይናገሩ፤ ከዚያም ደቂቃውን።Question 3 of 3
Excellent!Great job!네 안타깝군요이번 점수입니다:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
When do you have ______?
መቼ ነበር ______ የወሰድከው?I never have ______.
መቼም ______ አልወሰድኩም።I have ______ at ______.
______ በ ______ ሰዓት ወስጃለሁbreakfast
ቁርስdinner
እራትeight forty five
ለሶስት ሩብ ጉዳይtwelve fifteen
ስድስት ከሩብ