ባለፉት 70 ዓመታት በአፍሪካ የተካሄዱ የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥታት

ከአውሮፓውያኑ 1952 ጀምሮ በአህጉረ አፍሪካ 130 የሚሆኑ የተሳኩ የመንግሥት ግልበጣዎች ተካሂደዋል። የግብፁ ንጉሥ ፋሩክ የመጀመሪያው በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱ የሀገር መሪ ናቸው።

በመፈንቅለ መንግሥት የወረዱ የአፍሪካ መሪዎች

ከቀደሙት እስከ ቅርብ ጊዜ የተደረጉ የሥልጣን ግልበጣዎች
  • አሊ ቦንጎ

    ፕሬዝደንት ጋቦን ጋቦን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሞሐመድ ባዙም

    ፕሬዝደንት ኒጀር ኒጀር
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ፖል-ሄንሪ ሳንዳዎጎ ዳሚባ

    ጊዜያዊ ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሮቻ ካቦሬ

    ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አብደላ ሐምዶክ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ሱዳን ሱዳን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • አልፋ ኮንዴ

    ፕሬዝደንት ጊኒ ጊኒ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ባህ ንዳው

    ፕሬዝደንት ማሊ ማሊ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ኢብራሒም ቡባካር ኬይታ

    ፕሬዝደንት ማሊ ማሊ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ኦማር አል-ባሺር

    ፕሬዝደንት ሱዳን ሱዳን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሮበርት ሙጋቤ

    ፕሬዝደንት ዚምባብዌ ዚምባብዌ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ብሌይስ ኮምፓዎሬ

    ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሞሐመድ ሞሐመድ ሞርሲ

    ፕሬዝደንት ግብፅ ግብፅ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ፍራንሷ ቦዚዜ ያንጉቮንዳ

    ፕሬዝደንት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • አማዱ ቱማኒ ቱሬ

    ፕሬዝደንት ማሊ ማሊ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሙአመር ጋዳፊ

    የሀገር መሪሊቢያ ሊቢያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሎረንት ባግቦ

    ፕሬዝደንት አይቮሪ ኮስት አይቮሪ ኮስት
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሆስኒ ሙባረክ

    ፕሬዝደንት ግብፅ ግብፅ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ዚን ኤል አቢዲን ቤን አሊ

    ፕሬዝደንት ቱኒዚያ ቱኒዚያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ማማዱ ታንጃ

    ፕሬዝደንት ኒጀር ኒጀር
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሻምበል ሙሳ ዳዲስ ካማራ

    ፕሬዝደንት ጊኒ ጊኒ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ማርክ ራቫሎማናና

    ፕሬዝደንት ማዳጋስካር ማዳጋስካር
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • አቡበከር ሶምፓሬ

    ፕሬዝደንት ጊኒ ጊኒ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሲዲ ኡልድ ሼይክ አብደላሂ

    ፕሬዝደንት ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ማውያ ኡልድ ሲድ አሕመድ ታያ

    ፕሬዝደንት ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ፍራዲክ ደ ሜንዜስ

    ፕሬዝደንት ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አንጌ-ፌሊክስ ፓታሴ

    ፕሬዝደንት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪብሊክ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሄንሪ ኮናን ቤዲዬ

    ፕሬዝደንት አይቮሪ ኮስት አይቮሪ ኮስት
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ጃዎ በርናርዶ ቪዬራ

    ፕሬዝደንት ጊኒ-ቢሳው ጊኒ-ቢሳው
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ታጂዲኔ ቤን ሰዒድ ማሶንዴ

    ፕሬዝደንት ኮሞሮስ ኮሞሮስ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ኢብራሒም ባሬ ማይናሳራ

    ፕሬዝደንት ኒጀር ኒጀር
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ጆኒ ፖል ኮሮማ

    የሀገር መሪ ሴራ ሊዮን ሴራ ሊዮን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ፓስካል ሊሱባ

    ፕሬዝደንት ኮንጎ ኮንጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አሕመድ ቴጃን ካባህ

    ፕሬዝደንት ሴራ ሊዮን ሴራ ሊዮን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ

    ፕሬዝደንት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ኮንጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሲልቬስተር ንቲባንቱንጋንያ

    ፕሬዝደንት ቡሩንዲ ቡሩንዲ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሞሐመድ ፋራህ አይዲድ

    ፕሬዝደንት ሶማሊያ ሶማሊያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ማሀማኔ ኡስማኔ

    ፕሬዝደንት ኒጀር ኒጀር
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ቫለንታይን ስትራሰር

    የሀገር መሪ ሴራ ሊዮን ሴራ ሊዮን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሞሐመድ ሰዒድ ጆሀር

    ፕሬዝደንት ኮሞሮስ ኮሞሮስ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሚጌል ትሮቮዳ

    ፕሬዝደንት ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ዳውዳ ካይራባ ጃዋራ

    ፕሬዝደንት ጋምቢያ ጋምቢያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ኧርነስት ሾኔካን

    ፕሬዝደንት ናይጄሪያ ናይጄሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ጆሴፍ ሞሞህ

    ፕሬዝደንት ሴራ ሊዮን ሴራ ሊዮን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ቻድሊ ቤንጄዲድ

    ፕሬዝደንት አልጄሪያ አልጄሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ጀስቲን ሌካንያ

    ፕሬዝደንት ሌሶቶ ሌሶቶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሙሳ ትራኦሬ

    ፕሬዝደንት ማሊ ማሊ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሞሐመድ ሲያድ ባሬ

    ፕሬዝደንት ሶማሊያ ሶማሊያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሂሴኔ ሀብሬ

    ፕሬዝደንት ቻድ ቻድ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሳሙኤል ዶ

    የሀገር መሪ ላይቤሪያ ላይቤሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • አሕመድ አብዳላህ አብድሬማኔ

    ፕሬዝደንት ኮሞሮስ ኮሞሮስ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሳዲቅ አል-ማሕዲ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ሱዳን ሱዳን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሀቢብ ቡርጊባ

    ፕሬዝደንት ቱኒዚያ ቱኒዚያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ቶማስ ሳንካራ

    ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ዦን-ባፕቲስት ባጋዛ

    ፕሬዝደንት ቡሩንዲ ቡሩንዲ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ቲቶ ሉትዋ ኦኬሎ

    ፕሬዝደንት ኡጋንዳ ኡጋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሊያቡዋ ጆናታን

    ጠቅላይ ሚኒስትርሌሶቶ ሌሶቶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሙሐማዱ ቡሐሪ

    ፕሬዝደንት ናይጄሪያ ናይጄሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሚልተን ኦቦቴ

    ፕሬዝደንት ኡጋንዳ ኡጋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ጋፋር ሙሐማድ አል-ኒሜሪ

    የሀገር መሪ ሱዳን ሱዳን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሞሐመድ ኾና ኡልድ ሃይዳላ

    ፕሬዝደንት ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሉዊስ ላንሳና ቢያቮግዊ

    ጊዜያዊ ፕሬዝደንት ጊኒ ጊኒ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሼሁ ሻጋሪ

    ፕሬዝደንት ናይጄሪያ ናይጄሪያ
    ...
  • ዦን-ባፕቲስት ኦድራጎ

    ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሳዬ ዜርቦ

    ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ጎኮኒ ኦዴይ

    ፕሬዝደንት ቻድ ቻድ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሂላ ሊማን

    ፕሬዝደንት ጋና ጋና
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ዴቪድ ዳኮ

    ፕሬዝደንት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪብሊክ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሳንጉሌ ላሚዛና

    ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሉዊስ ካብራል

    ፕሬዝደንት ጊኒ-ቢሳው ጊኒ-ቢሳው
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ጋድፍሬ ቢናይሳ

    ፕሬዝደንት ኡጋንዳ ኡጋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ዊሊያም ቶልበርት

    ፕሬዝደንት ላይቤሪያ ላይቤሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሞሐመድ ማሕሙድ ኡልድ ላውሊ

    ፕሬዝደንት ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ዦን-ቤዴል ቦካሳ

    ፕሬዝደንት/ንጉሥማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ፍራንሷ ማሲያስ ንጉዌማ

    ፕሬዝደንት ኢኳቶሪያል ጊኒ ኢኳቴሪያል ጊኒ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ዩሱፍ ሉሌ

    ፕሬዝደንት ኡጋንዳ ኡጋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ፍሬድ አኩፎ

    ፕሬዝደንት ጋና ጋና
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሙስጠፋ ኡልድ ሳሌክ

    ፕሬዝደንት ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ኢዲ አሚን ዳዳ

    ፕሬዝደንት ኡጋንዳ ኡጋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ዮአኪም ዮምቢ-ኦፓንጎ

    ፕሬዝደንት ኮንጎ ኮንጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሞክታር ኡልድ ዳዳህ

    ፕሬዝደንትሞሪታኒያ ሞሪታኒያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ኢግናትየስ ኩቱ አቺያምፖንግ

    የሀገር መሪ ጋና ጋና
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አሊ ሶይሊህ

    ፕሬዝደንት ኮሞሮስ ኮሞሮስ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ተፈሪ በንቲ

    ፕሬዝደንት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ጄምስ ማንቻም

    ፕሬዝደንት ሲሼልስ ሲሼልስ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሚሼል ሚኮምቤሮ

    ፕሬዝደንት ቡሩንዲ ቡሩንዲ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • አሕመድ አብደላህ አብድሬማኔ

    ፕሬዝደንት ኮሞሮስ ኮሞሮስ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ያኩቡ ጎዎን

    ፕሬዝደንት ናይጄሪያ ናይጄሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ፍራንሷ ቶምባልባየ

    ፕሬዝደንት ቻድ ቻድ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሪቻርድ ራትሲማንድራቫ

    የሀገር መሪ ማዳጋስካር ማዳጋስካር
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ጋብርኤል ራማናንሷ

    ፕሬዝደንት ማዳጋስካር ማዳጋስካር
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አማን ሚካኤል አንዶም

    የሀገር መሪ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ

    ንጉሥ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሀማኒ ዲዮሪ

    ፕሬዝደንት ኒጀር ኒጀር
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ግሪጎይር ካይባንዳ

    ፕሬዝደንት ሩዋንዳ ሩዋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ጀስቲን አሆማዴግቤ ቶሜቲን

    ፕሬዝደንት ቤኒን ቤኒን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ፊልበርት ሲራናና

    ፕሬዝደንት ማዳጋስካር ማዳጋስካር
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ዶ/ር ኮፊ ቡሲያ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ጋና ጋና
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሚልተን ኦቦቴ

    ፕሬዝደንት ኡጋንዳ ኡጋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ኤሚል ዴርሊን ዚንሱ

    ፕሬዝደንት ቤኒን ቤኒን
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አብዲራሺድ አሊ ሻርማርኬ

    ፕሬዝደንት ሶማሊያ ሶማሊያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ንጉሥ ኢድሪስ ቀዳማዊ

    ንጉሥ ሊቢያ ሊቢያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ኢስማኢል አል-አዣሪ

    የሀገር መሪ ሱዳን ሱዳን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ማዲቦ ኬይታ

    ፕሬዝደንት ማሊ ማሊ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • አልፎንስ ማሳምባ-ዴባት

    ፕሬዝደንት ኮንጎ ኮንጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አንድሩ ጀክስተን-ስሚዝ

    የሀገር መሪ ሴራ ሊዮን ሴራ ሊዮን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ክሪስቶፍ ሶግሎ

    ፕሬዝደንት ቤኒን ቤኒን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ዴቪድ ላንሳና

    መሪሴራ ሊዮን ሴራ ሊዮን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሲያካ ስቴቨንስ

    ጠቅላይ ሚኒስትርሴራ ሊዮን ሴራ ሊዮን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ኒኮላስ ግሩኒትስኪ

    ፕሬዝደንት ቶጎ ቶጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ንታሬ 5ተኛ

    ንጉሥ ቡሩንዲ ቡሩንዲ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሌዎፖልድ ቢሀ

    ጠቅላይ ሚኒስትርቡሩንዲ ቡሩንዲ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ክዋሜ ንኩሩማህ

    ፕሬዝደንት ጋና ጋና
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ንጉሥ ሙቴሳ ዳግማዊ የቡጋንዳ

    ንጉሥ/ፕሬዝደንት ኡጋንዳ ኡጋንዳ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • አቡባካር ታፋዋ ባሌዋ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ናይጄሪያ ናይጄሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሞውሪስ ያሜጎ

    ፕሬዝደንት ቡርኪና ፋሶ ቡርኪና ፋሶ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ዴቪድ ዳኮ

    ፕሬዝደንት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሱሩ-ሚጋን አፒቲ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒን ቤኒን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሞይስ ሾምቤ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዲአር ኮንጎ ዲሞክራቲክ ኮንጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አሕመድ ቤን ቤላ

    ፕሬዝደንት አልጄሪያ አልጄሪያ
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሊዮን ምባ

    ፕሬዝደንት ጋቦን ጋቦን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሁበርት ሜጋ

    ፕሬዝደንት ቤኒን ቤኒን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ፉልበርት ዩሉ

    ፕሬዝደንት ኮንጎ ኮንጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሲልቫነስ ኦሊምፒዮ

    ፕሬዝደንት ቶጎ ቶጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ፓትሪስ ሉሙምባ

    ጠቅላይ ሚኒስትርዲአር ኮንጎ ዲሞክራቲክ ኮንጎ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • አብደላህ ኻሊል

    ጠቅላይ ሚኒስትር ሱዳን ሱዳን
    ተጨማሪ ያንብቡ...
  • ሙሐመድ ስምንተኛ አል-አሚን

    ንጉሥ ቱኒዚያ ቱኒዚያ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • ሙሐመድ ናግዊብ

    ፕሬዝደንት ግብፅ ግብፅ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...
  • የግብፁ ፋሩክ

    ንጉሥግብፅ ግብፅ
    ተጨማሪ ያንብቡ ...

አዲስ ማዕበል

በአፍሪካ ባለፉት 3 ዓመታት ስምንት የተሳኩ የመንግሥት ግልበጣዎች ተካሂደዋል። አዲሱ የመፈንቅለ መንግሥት ማዕበል ወታደራዊ ግልበጣዎች እስከ 2020 ድረስ ቀዝቀዝ ብለው ድጋሚ ያንሰራራበት ወቅት ነው። በርካታ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በአህጉሪቱ ውስጥ ያጋጠመው በ1970ዎቹ ነበር።

የዕድሜ ልክ ሥልጣን

በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጡ አንዳንድ መሪዎች ለበርካታ አስርት ዓመታት በመንበራቸው ላይ ቆይተዋል። ሌሎች ደግሞ ሥልጣን በያዙ በቀናት ውስጥ ተፈንግለዋል።

ለምሳሌ የኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዝደንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ በ1979 ሥልጣን ከያዙ በኋላ ለ44 ዓመታት መንበራቸው ላይ ቆይተዋል።

News image

በዚህም በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ለበርካታ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩ መሪ ለመሆን ችለዋል።

ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የተመለሱ መሪዎች

የመፈንቅለ መንግሥት ቀጣና

በሳህል ቀጣና የሚገኙ በርካታ ሀገራት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥታት ተካሂደውባቸዋል። የመፈንቅለ መንግሥት ቀጣና በተባለው አካባቢ በቅርቡ የተካሄዱት መፈንቅለ መንግሥታት በኒጀር እና በጋቦን ውስጥ ያጋጠሙ ናቸው ነው።

በ2020 እና 2021 በማሊ ወታደራዊ መፈንቅለ-መንግሥታት ተደርገዋል። በ2021 በቻድ,በጊኒ እና በሱዳንም መፈንቅለ መንግሥታት ተካሂደዋል። ቡርኪና ፋሶ በ2022 ሁለት የመንግሥት ግልበጣዎችን አስተናግዳለች። ከሱዳን በስተቀር ሁሉም ሀገራት የቀድሞ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ነበሩ።

ከ2000 (እአአ) በኋላ ከተካሄዱ 26 የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥታት 19ኙ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በነበሩ ሀገራት ውስጥ የተፈፀሙ ናቸው። ይህ አሀዝ በአፍሪካ የፈረንሳይ ተፅዕኖ አሉታዊ ውጤት አለው የሚል ሃሳብ በአንዳንዶች ዘንድ እንዲነሳ አድርጓል።

ከ1952 በኋላ በአፍሪካ የተሳኩ መፈንቅለ-መንግሥታት

ሀገር ይምረጡ

የመፈንቅለ መንግሥት ብዛት

0

2

4

6

8

በርካታ የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት በተደጋጋሚ የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥታት ተካሂደውባቸዋል። ቢያንስ አራት መፈንቅለ መንግሥታት ካጋጠሟቸው 17 የአፍሪካ ሀገራት ግማሹ የሚገኙት በምዕራቡ የአህጉሪቱ ክፍል ነው።

ቡርኪና ፋሶ በርካታ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደባት የአፍሪካ ሀገር ስትሆን,ስምንት ጊዜ መፈንቅለ መንግሥት ተከስቶባታል። ሲራ ሊዮን እና ኡጋንዳ እያንዳንዳቸው 7 ጊዜ መፈንቅለ-መንግሥት በማካሄድ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ከአፍሪካ ሀገራት አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት እና በተለይ በደቡባዊ እና ምሥራቅ ክፍል የሚገኙ ሀገራት ናቸው የተሰካ መፈንቅለ መንግሥት ያልገጠማቸው።

በ2024፤ 34 ዓመት የሆናቸው ኢብራሒም ትራኦሬ በዓለም በዕድሜ ትንሹ የሀገር መሪ ናቸው። መስከረም 30/2022 የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የቡርኪና ፋሶ ጊዜያዊ መሪ ሆነዋል። ከዚያ ቀደም ጊዜያዊ ፕሬዝደንት የነበሩት ፓል-ሄንሪ ሳንዳዎጎ ዳሚባ ከመንበራቸው ተፈንቅለዋል።

ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት

90 በመቶው የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥታት የተካሄዱት በወታደራዊ ኃይል ታግዘው ሲሆን,4 በመቶው ደግሞ በቅጥረኛ ወታደሮች አመካይነት የተፈፀሙ ናቸው። ሌሎች የመፈንቅ-መንግሥት ዓይነቶች ሰላማዊ ተቃውሞ,ቅኝ ገዢ ኃይሎች,በአማፂያን እና በቤተ-መንግሥት ውስጥ የተካሄዱ ናቸው።

በሰይፍ የመጡ,በሰይፍ ይወድቃሉ

አብዛኞቹ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዙ መሪዎች በጉልበት ከሥልጣን እንዲወርዱ ተደርገዋል፤ አሊያም ተገድለዋል።

በ1972 ጄኔራል ኢግናቲየስ ኩቱ አቼያምፖንግ፤ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን የጋናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ኮፊ ቡሲያን ደም ባላፈሰሰ መንገድ ከሥልጣን ፈነገሉ። ከስድስት ዓመታት በኋላ ቤተ-መንግሥት ውስጥ በተካሄደ የመንግሥት ግልበጣ በተወገዱ በአንድ ዓመቱ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ተፈርዶባቸዋል።

ቶማስ ሳንካራ የቁም እስር ላይ ሳሉ ነው በእሳቸው ስም በ1983 የቡርኪና ፋሶ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደው። ሳንካራ፤ ጥቅምት 15/1987 በብሌይዝ ኮምፓዎሬ በተመራ ታጣቂ ቡድን ተገድለዋል።

ጃፋር ኒሜይሪ የሱዳኑን መሪ የነበሩትን ኢስማኢል አል-አዣሪን አስወግደው ሥልጣን የያዙት በ1969 ነበር። መጀመሪያ የወታደራዊው ቡድን መሪ ሆነው,ቀጥሎ ደግሞ ፕሬዝደንት ሆነው ካገለገሉ በኋላ በ1985 ከመንበራቸው ተፈንግለዋል።

ዦን-ባፕቲስት ባጋዛ የቡሩንዲውን ፕሬዝደንት ሚኬል ሚኮምቤሮን በ1976 ከሥልጣን አስወግደው ሥልጣን ከያዙ ከአስራ አንድ ዓመታት በኋላ ከመንበራቸው ተነስተው ለስደት ተዳርገዋል።

ኦማር አል-በሽር ወደ ሥልጣን የመጡት በ1989 ነበር። በወቅቱ የሱዳን ጦር ብርጋዴር ጄኔራል ነበሩ። ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መርተው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን አስተዳደር ጥለው ሥልጣን ያዙ። እስከ 2019 ድረስ በተለያዩ ማዕረጎች ሱዳንን ሲያስተዳድሩ ከቆዩ በኋላ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተባረሩ።

ፍራንሷ ቦዚዜ ያንጎቮንዳ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ስድስተኛው ፕሬዝደንት የሆኑት በ2003 ወደ ሥልጣን ከመጡ ከ10 ዓመታት በኋላ ከሥልጣናቸው ተወገዱ።

የቤተሰብ ጉዳይ

በአንዳንድ ሀገራት ሥልጣን ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ነው። የኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዝደንት ፍራንሷ ማሲያስ ንጉዌማ ደም አፋሳሽ በሆነ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት በዘመዳቸው ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ ነው። በ2024 ቴዎዶሮ በዓለማችን ከሚገኙ ንጉሣዊ ያልሆኑ እና ለረጅም ዘመን በሥልጣን ላይ የቆዩ ሁለተኛው መሪ ናቸው።

ሎረንት ካቢላ በ1997 ሞቡቱ ሴሴ ሴኮን ፈንቅለው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሦስተኛው ፕሬዝደንት ሆኑ። ሎረንት ካቢላ ከጠባቂያቸው በአንዱ ሲገደሉ የ29 ዓመቱ ልጃቸው ጆሴፍ ካቢላ ተኳቸው።