አፕል ከ21 ዓመት በኋላ የአይፓድ ምርቱን ሊያቆም ነው

አይፓድ

የፎቶው ባለመብት, Apple

ሰዎች ሙዚቃን የሚያዳምጡበትን መንገድ በመቀየር አብዮት አስነሰቷል የሚባልለት የአፕል የሙዚቃ ማጫወቻ አይፓድ ተች ከምርት ውጪ ሊሆን ነው።

እንደ አውሮጳውያኑ በ2011 ወደ ገበያ የገባው የመጀመሪያው 'የአይፓድ ተች' ምርት 1 ሺህ ሙዚቃዎችን መጫን የሚችል ነበር። ከ21 ዓመት በኋላ ግን 90 ሚሊዮን ሙዚቃዎች መያዝ ወደሚችል የኦንላይን ማሰራጫነት ማድግ ችሏል።

'አይፓድ ተች'ን ያስተዋወቀው ኩባንያ ቆየት ብሎ አይፎንን ያስተዋወቀ ሲሆን የአይፎንን ወደ ገበያ መግባት የሙዚቃ ማጫወቻ ምርቱ ላይ ጥላውን ያጠላውበፍጥነት ነበር ።

የአይፓድ የመጨረሻ ምርት ማሻሻያ የተደረገለት እንደ አውሮጳውያኑ በ2019 ነበር። በጊዜ ሂደት ውስጥ ሙዚቃ ማጫወቻው የተለያዩ ሞዴሎችን ይፋ አድርጓል።

አፕል ያመረታቸው ምርቶች ተሽጠው እስኪያልቁ ድረስ የአይፓድ ምርት ገበያ ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል።

የአፕል ምክትል ፕሬዝዳንት አይፓድ ሙዚቃ የሚገኝበት፣ የሚደመጥበት እና ለሌሎች የሚጋራበትን መንገድ በአዲስ መልክ አስተዋውቋል ብለዋል።

አይፓድን የሚወዱ ሰዎች የምርቱ መቋረጥ በተመለከተ ያላቸውን ሀሳብ እና ትዝታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚያጋሩ ይጠበቃል።

የአይፓድ የመጀመሪያው ሞዴል በአፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 ይፋ የሆነ እና በከፍተኛ ድምቀት የተዋወቀ ነበር።

ታዲያ ምርቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ገበያ ሲገባ "1000 ሙዚቃዎችን በኪስዎ" በሚል ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖም ነበር።

በጊዜ ሂደት ምርቱ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘ ሲሆን ቢኤምደብሊው በተሽከርካሪው የአይፖድ ስርዓትን መግጠሙን ተከትሎ የመኪናው ፈላጊዎች ተበራክተው ነበር።

በወቅቱ ሌሎች መኪና አምራች ኩባንያዎችም ተመሳሳይ ፈለግን ተከትለዋል።