የፀረ-ቫይረስ ፈጣሪው በእስር ቤት ሞቶ ተገኘ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የኮምፒውተር ፀረ-ቫይረስን የፈለሰፈው ጆን ማክአፌ የስፔን ፍርድ ቤት ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ ከወሰነ በኋላ በባርሴሎና በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
የግብር ስወራ ክስ የነበረበት ማክአፌ ህይወትን ለማዳን የእስር ቤቱ የህክምና ቡድን ቢረባረብም እዳልተሳካላቸው የካታላን የፍትህ መምሪያ ተናግሯል።
መምሪያው <<ሁሉም ነገር ማክአፌ የራሱን ሕይወት እንዳጠፋ ያመላክታል›› ሲል በመግለጫው ላይ አካቷል ። በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ አወዛጋቢ የሆነው ማክአፌ ኩባንያው የመጀመሪያውን ለንግድ የቀረበ ፀረ-ቫይረስ መተግበሪያ ያቀረበ ነበር።
በኮምፒውተር አለም ውስጥ የፀረ-ቫይረስ ገበያ ቢሊዮን ዶላሮችን የሚያንቀሳቅስ ኢንዱስትሪ ያደረገው ማክአፌ በመጨረሻም ድርጅቱን ለግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባኒያ ኢንቴል ከ 7.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ (4.7 ቢሊዮን ዩሮ) ተሽጧል።
ባለፈው አመት ነሃሴ በስፔን ከተማ ወደ ቱርክ የሚበር አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።
የተጠረጠረበት ወንጀልም ለአራት አመታት የግብር ተመላሾቹን ባለመክፈሉ ነበር።
በማማከር ስራ ሚሊዮኖችን የሚያገኘው ማክአፌ የተለያዩ ንግሮችን በማድረግ፣ የክሪፕቶ ከረንሲን በመሸጥ እንዲሁም የህይወት ታሪኩን የቅጂ መብት በመሸጥ ገቢ ቢሰበስብም ተመላሾቹን መክፈል አልቻለም በሚል ነበር የተከሰሰው።
የአሜሪካው ጀስቲስ ዲፓርትመንት በባንክ አካውንቱ ሲገቡ የነበሩ ክፍያዎችን ብሎም የክርፒቶ ከረንሲ አካውንቶቹ ላይ ያሉ ልውውጦችን አስመልከቶ የግብር ስወራ አድርጓል ሲል ከሶታል። የሪልስቴት አብቶቹን ጨምሮ የተለያዩ ሃብቶችን በመሰወርም ክሶች ቀርበውበታል።
የስፔኑ ፍርድ ቤትም ወደ አሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ ሮብ ሰኔ 16 ውሳኔ አሳልፏል። ከቅርብ አመታት ወዲህ ማክአፌ በተቀነባበረ መልኩ እኔን የማጥቃት እቅድ አለ ቢልም ችሎቱ ክሶቹ በፖለቲካ ወይም በርዕዮተ አለም ምክኒያቶች የቀረቡ መሆናችን የሚያስረዳ ማስረጃ አልቀረበልኝም ሲል ውድቅ አድርጓቸዋል።
በያዝነው ወር በችሎት ተገኝቶም ክሶቹ ፖለቲካዊ ምክኒያ ያላቸው እንደሆኑ እና ወደ አሜሪካ ከተመለሰ በእር ቤት ህይወቱን ሙሉ ለቆይ እንደሚችለ ተናግሮ ነበር። ጠበቃው እንዳሉትም ሁሉንም ክሶች ለመከላከል ሞክሮ ነበር።
‹‹የአሜሪካ መንግስት ማክአፌን ለማጥፋት የሚያደርገው ነው›› ሲሉ ጠበቃው ለ ኤንፒአር ተናግረዋል።
በተጨማሪም እ.ኤ.አ. በ 2016 እና በ 2020 ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሊበርታሪያን ፓርቲ እጩ በመሆን ያልተሳካ ሙከራ አድርጎ ነበር አካሂደዋል ።
ማክአፌ እኤአ በ 2019 ለግብር ያለውን ንቀት ሲገልጽም ‹‹ግብር ህገወጥ ስለሆነ ለስምንት ዓመት ያህል የግብር ተመላሽ አላደረኩም›› ሲል ተናግሮም ነበር ።












