ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ኩባንያ ገቢው በእጥፍ ማደጉ ተነገረ

የቲክቶክ አርማ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የአጫጭር ቪዲዮዎች ማጋሪያ የሆነው የቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ እንደ አውሮፓውያኑ በ2020 ያገኘው ገቢ በእጥፍ እንደጨመረ ተገልጿል።

ለሰራተኞች በተሰራጨ የውስጥ ለውስጥ ማስታወሻ የኩባንያው የባለፈው ዓመት ገቢ 34.3 ቢሊዮን መድረሱን ይህም በ111 በመቶ ማደጉን አመላክቷል። እናም ይህ ቁጥር ቲክቶክ ያለውን ተዳጅነተ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ኩባንያው እዚህ ገቢ ላይ የደረሰው ራሱን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የቻይና የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያዎች በዓለም ዙሪያ ካሉ መንግስታት ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ባለ ወቅት ላይ ነው።

ባይትዳንስ ዓመታዊ አጠቃላይ ትርፉ በ 93 በመቶ አድጎ ወደ 19 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የተመለከተ ሲሆን በተመሳሳይ ዓመት የተጣራ 45 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስመዘጉም ተገልጿል። ይህ ኪሳራ ግን ከኩባንያው ስራ በቀጥታ የተያያዘ አይደለም ተሏል።

የውስጥ ለውስጥ ማስታወሻው በተጨማሪ ካለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ጀምሮ ባይትዳንስ በሁሉም መተግበሪያዎቹ ላይ በየወሩ ወደ 1.9 ቢሊዮን የሚጠጋ ንቁ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ያሳያል ፡፡

በማስታወሻው ላይ የሰፈሩት ቁጥሮችን ትክክለኝነት የተቋም ቃል አቀባይ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።