ሴቶች ከአንድ ባል በላይ ለምን አያገቡም?

የጋብቻ ወቅት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የአገሪቱን የጋብቻ ህግ ለማሻሻል አቅዷል። በያዝነው ወርም መሻሻል አለባቸው ያላቸውን ሃሳቦች አቅርቧል።

ከነዚህም መካከል ሴቶች ሁለትና ከዚያ በላይ ባል የማግባትን እውቅናን መስጠት ነው። በእንግሊዝኛው ፖሊአንድሪ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሴቶች ከአንድ በላይ ባል ማግባት መቻልንም የሚያንፀባርቅ ሃሳብ ነው።

የዚህ ህግ መሻሻል እንደ ሃሳብ የመቅረብ ሁኔታ በደቡብ አፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያን ፈጥሯል።

አንድ ሚስት፣ በርካታ ባሎች ፤ ምን ችግር አለው? በሚልም የደገፉት አልታጡም።

"ከዚህ ርዕስ ጋር በተገናኘ በከፍተኛ ሁኔታ የደቡብ አፍሪካ ትዊተር በከፍተኛ ሁኔታ መወያያ ሆኗል" በማለት ላታሺያ ናይዶ የተባለች ጋዜጠኛ ከኬፕታውን ተናግራለች።

በአሁኑ ወቅት ይህ ማሻሻያ ህዝቡ ውይይት እንዲያደርግበትም ተመርቷል። ነገር ግን እነዚህ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚሆኑ ከሆነ በተለይም ሴቶች በርካታ ባሎች ማግባት ይችላሉ የሚለው ከተፈቀደ ለአፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናል።

ምንም እንኳን ዜናውን እሰዬው ብለው የተቀበሉ ቢሆንም የተቃወሙት መኖራቸው ብዙ የሚያስደንቅ አይደለም።

"ወንዶች ሴቶቻቸውን ወይም ሚስቶቻቸውን ከሌሎች ወንዶች ጋር መጋራት አይፈልጉም" በማለት የተናገሩት የአፍሪካ ክርስቲያኖች ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ የሆኑት ቄስ ኬኔት መሾ ናቸው

ቄሱ አክለውም "መንግሥት በውሳኔው ላይ የሰዎችን ሃሳብ ሊሰማ ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት እኔን ጨምሮ በርካቶቻችን መጥፎ ሃሳብ ነው ብለን እናስባለን" ብለዋል።

ለማንኛውም ውሳኔውን በቅርቡ የምናየው ይሆናል። የሚያመጣውንም ለውጥ እንዲሁ