በኮሮናቫይረስ ፅኑ ህሙማን ክፍል ያለጊዜያቸው የተወለዱት መንትዮች አንድ ዓመት ሞላቸው

የፎቶው ባለመብት, Perpetual Uke
በእንግሊዟ በርሚንግሃም ባለፈው ዓመት እናታቸው በኮሮናቫይረስ በጠና ታማ በሰመመን እያለች በፅኑ ህሙማን ክፍል ያለጊዜያቸው የተወለዱት መንታ ህፃናት አንድ ዓመት ሞላቸው።
ልክ የዛሬ ዓመት እንደ አውሮፓውያኑ ሚያዚያ 10/2020 መንትያዎቹ የተወለዱት በ26ተኛ ሳምንታቸው ነው።
መደበኛ የእርግዝና ጊዜ 38 ሳምንታት ሲሆን በበርሚንግሃም የተወለዱት መንትዮች ከዚህ 12 ሳምንታትን ቀድመዋል።
የህፃናቱ እናት ዶክተር ዩክ አሁን ላይ የእሳቸውም ሆነ የልጆቹ ሁኔታ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በነበሩት ጊዜያት "እየጠነከርን እና እየተሻሻልን" ነው ብለዋል።
ይህ ቀን "ሁላችንም የደስታ ዘውድ የደፍንበት ቀን ነው። ምክንያቱም ሁላችንም እዚህ አለን" ሲሉም ተናግረዋል።
ነገሩን ወደ ኃላ ሰንቃኘው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የበርኒግሃም ሆስፒታል የሩማቶሎጂ አማካሪዋ ዶ/ር ዩክ ጤንነት አይሰማቸውም ነበር።
እናም ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል እንዲገቡ ተደረገ። በመተንፈሻ ማገዣ መሳሪያ/ቬንትሌተር ታግዘው ኮማ ውስጥ እንዲገቡ ተደረገ።

የፎቶው ባለመብት, Perpetual Uke
በወቅቱ ከመትዮቹ ልጆች ሴቷ 77 ወንዱ 80 ግራም ነበር የሚመዝኑት።
ከ16 ቀናት በኃላ ከሰመመን የነቁት እናት መንትዮቹ ልጆች የኔ መሆናቸውን "አላመንኩም ነበር" ብለዋል።
"ወደ ኃላ መለስ ብሎ ከዋሻው ጫፍ ያለውን ብርሃን ማየት መልካም ነው! ሲሉ ተናግረዋል ዶ/ር ዩክ
ሴቷ ልጅ ወደ ምድር ስትመጣ ከነበራት ጥንካሬና ፈጣን የጤንነት ለውጥ በተቃራኒ ወንዱ ልጅ በአስቸጋሪ የጤንነት ሁኔታ ሰለማለፉ ተናግረዋል።
አንደኛ ዓመታቸውንም በበይነ መረብ ራቅ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር በማክበር ያሰቡት ሲሆን "ባለፈው ዓመት ባለፉበት ሁኔታ ማለፍ ዕድል ሊሆን እንሰሚችል ዶክተር ዩክ" ገልፀዋል።
"ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ ኮማ ውስጥ ነበርኩ። ልጆቼንም አላገኘዋቸውም ነበር። የትም እንዳለሁ አላውቅም ነበር። በህይወትና ሞት ግብግብ ውስጥ ነበርኩ።" ሲሉ የገለፁት ዶክተር ዩክ
"ከፈጣሪና ከህክምና ቡድኑ ዕርዳታ ባይኖር እዚህ አንሰርስም ነበር። በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር [ለመንትዩቹ] እኛም ከነሱ ሁኔታ ጋር ከፍ ዝቅ ብለናል። አሁን ጠንካራ ነን። ተስፋ እንዳርጋለን ካሰብንበት እንደርሳለን።" በማለት ተናግረዋል።












