ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ አለፈች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡደን ደጋፊዎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የምእራብ አፍሪካ አገሯ ካሜሮን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ እግረ ኳስ ዋንጫ ማለፏ አረጋገጠች።

ኢትዯጵያ ለአፍኮን 2021 ያለፈችው ከስምንት ዓመት በኋላ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚገኝበት ምድብ ወስጥ ያሉት የኒጀርና የማዳጋስካር አቻ መውጣታቸውን ተከትሎ ነው 9 ነጥብ በመያዝ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መቀላቀሉን ያረጋገጠው።

ዛሬ በምድብ ኬ የሚገኙት ኢትዮጵያ ኮትዲቯርና ማዳጋስካር ኒጀር የመጨረሻ ቀሪ ጨዋታቸውን አካሄደው ነበር።

በዚህ ውጤት መሰረት ኢትዮጵያና ኮትዲቯር ባደረጉት ጨዋታ ኮትዲቯር ሦስት ለአንድ ኢትዮጵያን እየመራች ሳለ በዳኛው ሕመም ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ማለፏን ያረጋገጠችው በተመሳሳይ ምድብ የሚገኙት ማዳጋስካርና ኒጀር ባዶ ለባዶ መለያየታቸውን ተከትሎ ነው።

ሰባት ነጥብ የነበራት ማዳጋስካር ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኒጀርን አሸንፋ 9 ነጥብ ያላትን ኢትዮጵያን መብለጥ ይጠበቅባት ነበር።

የዋሊያዎቹን ድል ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

በሚቀጥለው ዓመት ታኅሣሥ ወር ላይ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ 24 አገራት ተሳታፊ ይሆናሉ።

እስካሁን ድረስ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ዚምባብዌ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ማሊ፣ ግብጽ፣ ኮሞሮስ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማላዊ፣ጋና ፣ሱዳን ፣ጋምብቢ፣ ሞሮኮ እና ጋቦን ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።