በጋና ሌቦች ፖሊስ ጣቢያን ዘረፉ

የፎቶው ባለመብት, Star FM
በዛሬዋ ዕለት በጋና መዲና አክራ ዘራፊዎች አንድ የፖሊስ ጣቢያን መስኮት ሰብረው በመግባት ላፕቶፕ፣ ቴሌቪዥንና የፖሊስ መለዮ አልባሳቱን እንደሰረቁ ተገልጿል።
ኒማ በተባለው ፖሊስ ጣቢያ መስኮት ሰብረው በመግባት መዝረፋቸው ተገልጿል።
ባለስልጣናቱ ምርመራ ቢጀምሩም እስካሁን በተጠርጣሪነት የያዙት እንደሌለም አሳውቀዋል።
ክስተቱ ብዙዎችንም አስደንግጧል፤ መገረምም ፈጥሯል። አንደኛ ሌቦቹ እንዴት ቢደፍሩ ነው ፖሊስ ጣቢያውን ለመዝረፍ የቻሉት የሚለው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ፖሊስ ጣቢያ የተመደቡ ጠባቂዎች አለመኖራቸው መነጋገሪያ ሆኗል።
ነገር ግን ባለስልጣናቱ ለቢቢሲ እንዳስታወቁት ዘራፊዎች መስኮት ሰብረው በገቡበት ወቅት ፖሊሶች የጦር መሳሪያዎችን እንዲሁም ሌሎች ተጠርጣሪዎች የተያዙበትን ህንፃ እየጠበቁ ነበር ብለዋል።
በአሁኑ ወቅትም በዘራፊዎቹ የተሰበረው የፖሊስ መስኮትም እየተጠገነ ነው ተብሏል።








