ጆ ባይደን ጾታዊ ጥቃት ፈጽሞብኛል ያለቸው ሴት ፤ ባይደን እራሳቸውን ከውድድር እንዲያገሉ ጠየቀች

ጆ ባይደን ጾታዊ ጥቃት ፈጽሞብኛል ያለቸው ሴት ፤ ባይደን እራሳቸውን ከውድድር እንዲያገሉ ጠየቀች

የፎቶው ባለመብት, MEGYN KELLY

ጆ ባይደን ከ27 ዓመታት በፊት ጾታዊ ጥቃት ፈጽመውብኛል ያለችው ሴት፤ ጆ ባይደን ከቀጣዩ ምርጫ እራሳቸውን እንዲያገሉ ጠየቀች።

ቃለ መጠይቅ ያደረገችው ታራ ሪድ ‘ለደረሰብኝ ጾታዊ ጥቃት ባይደን እራሱን ተጠያቂ ማድረግ አለበት’’ ብላለች።

“የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ለመሆን መወዳደር አይኖርብህምም” ብላለች በቃለመጠይቋ ወቅት።

ከ7 ወራት በኋላ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተቀናቃኝ ሆነው የሚቀርቡት ዲሞክራቱ ጆ ባይደን በታራ የቀረበችባቸውን የጾታዊ ትንኮሳ ክስ ያጣጥላሉ። ታራ ጆ ባይደን አድርሰውብኛል ያለችውን ጾታዊ ጥቃት ዝርዝር ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ተናግራለች።

ዛሬ ላይ የ56 ዓመት ሴት የሆነችው ታራ እ.አ.አ. 1993 ላይ ጆ ባይደን የአንድ ግዛት ሴናተር ሳሉ፤ ከግድግዳ ጋር አጣብቆ ይዞ ጾታዊ ተንኮሳ ፈጽሞብኛል በማለት በዝርዝር የደረሰባትን ተናግራለች።

ጆ ባይደን የቀረበባቸውን ክስ ሃሰት ነው ማለታቸውን ተከትሎ ታራ ባይደን እውነት ወይም ውሸት እየተናገረ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ፈተና የሚወስድ ከሆነ እርሷም ፈተናውን ለመውደስ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

እ.አ.አ. 1996 ላይ በወቅቱ የታራ ባለቤት የነበረው ግለሰብ ታራ በሥራ ቦታዋ ላይ ‘ችግር’ እያጋጠማት ነው በማለት ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡበት ዶሴ መውጣት ሌላው መነጋገሪያ የሆነ ጉዳይ ነው።

በካሊፎርኒያው ጋዜጣ የተገኘው ዶሴ ምናልባትም ታራ በወቅቱ ስለደረሰባት ጥቃት የሚያመላክት ብቻኛው ማስረጃ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ተራ ጨምራ እንደተናገረችው የጆ ባይደን ደጋፊዎች ‘የሩሲያ ተላላኪ ነሽ’ በማለት የግድያ ዛቻ አድርሰውባታል።

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ጾታዊ ትንኮሳ