የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ...

የፎቶው ባለመብት, DJ Abyssinia
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ዝግጅት በመስቀል አደባባይ በትናንትናው ዕለት የካቲት 14፣ 2012 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን 150 ሺ የሚሆኑ ሰዎች ተገኝተውበታል ተብሎም እንደሚገመት አዘጋጆቹ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የኮንሰርቱ አዘጋጅ የሆነው ላየንስ ፕሮሞሽን አንደኛው መስራች ዲጄ አቢሲኒያ (ያይንእሸት ጌታቸው) ለቢቢሲ እንደገለፀው ምንም እንኳን የቲኬት ሽያጩ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ የነበረ ከመሆኑ አንፃር ምን ያህል ሰው በትክክል እንደተገኘ በዛሬው እለት ለመናገር ቢያዳግትም ባለው ግምገማ ግን እስከ መቶ አምሳ ሺ የሚገመቱ ታዳሚዎች ተገኝተዋል ይላል።
በዲጄ የሙዚቃ ዝግጅት በተጀመረው የሙዚቃ ኮንሰርት ወደ 2፡30 አካባቢ በአቡጊዳ ባንድ ታጅቦ ቴዲ አፍሮ መድረኩን የተረከበ ሲሆን እስከ ሌሊቱ 6፡15 ድረስ በተለያየ ጊዜ የተጫወታቸውንና ህዝቡ እንደ ብሄራዊ መዝሙር የሚቆጥራቸውን ሙዚቃዎቹን ተጫውቷል።
ህዝቡ በጩኸት፣ በደስታ፣ በጭፈራ ለአርቲስቱ ያላቸውን አድናቆት የገለጸ ሲሆን፤ ዲጄ አቢሲኒያ የምሽቱን መንፈስ እንዴት መግለፅ እንዳለበት ቃለትም ሲፈልግ ነበር፤ "የነበረውን ስሜት ለመግለፅ ቃላት ያንሰኛል" ይላል።
"ሚኒልክ"፣ 'ቀነኒሳ' 'አፄ ቴዎድሮስ' 'ጥቁር ሰው' ፣ 'ኢትዮጵያ' 'ሸ መንደፈር' እንዲሁም ሌሎቹንም ዘፈኖቹን ግጥሞቹን የሚያውቁት ታዳሚዎቹ እኩል አብረውት መዝፈናቸው ምሽቱን የተለየ እንዳደረገው ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻቸው አስፍረዋል።
በተለይም "ጃ ያስተሰርያል'ን ሲዘፍን ይደገም የሚሉ ድምፆች በርክተው ነበር።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1
"ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የሙዚቃ ዝግጅት በተለይም በቅርቡ በአገሪቱ ውስጥ የሰፈነውን የብሄር ግጭቶች፣ ጥላቻና መፈራረቆችን በተወሰነ መልኩ ያስረሳ ነው የሚለው ዲጄ አቢሲኒያ "አንድነትን፣ አብሮ መሆንን ያስታወሰ ነበር" ይላል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ በተውለበለበት በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪም አድናቂዎቹ የአርቲስቱን ፎቶ ያለበት ቲሸርቶች በመልበስ ያላቸውን ፍቅር እንደገለፁ ዲጄ አቢሲኒያ ለቢቢሲ ገልጿል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 3
በተደጋጋሚ የሙዚቃ ዝግጅቶቹ በመንግሥት አካላት ዘንድ ተቀባይነት የማያገኙት ቴዲ አፍሮ፣ በመስቀል አደባባይ ላይ የሙዚቃ ዝግጅቱን ያቀረበው ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ነበር።

መስቀል አደባባይ ላይ ለማዘጋጀት የኮንሰርቱ ዋና ሃሳብ መነሻ የሆነው ከዛሬ አንድ ዓመት ተኩል በፊት በሚሊኒየም አዳራሽ አዘጋጅተውት የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ሲሆን 23 ሺ የሙዚቀኛው ወዳጆች ተገኝተውበት ነበር።
ነገር ግን ከአምስት ሺ በላይ የሚሆኑ የአርቲስቹ ወዳጆች አዳራሹ በመሙላቱ ምክንያት ብዙዎች እያዘኑ መመለሳቸውን የሚናገረው ዲጄ አቢሲኒያ አድናቂዎቹን በሙሉ አንድ ላይ ተሰብስበው የሚያዩበት ቦታ ሲፈለግ የመስቀል አደባባይ ሃሳብ መምጣቱን ይናገራል።
መጀመሪያ የሙዚቃ ዝግጅቱን ስፖንሰር የሚያደርግ አካል ከተገኘ በነፃ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ስፖንሰር በመታጣቱ በደረጃው 200 ብርና 500 ብር ለቲኬት በማስከፈል ኮንሰርቱ ሊካሄድ ችሏል።
"ጃ ያስተሰርያል" በሚለው እንዲሁም በሌሎች ዘፈኖች ምክንያት ከመንግሥት ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቶ ነበር የሚባለው አርቲስት ቴዲ አፍሮ በተለያየ ጊዜ ሊያደርጋቸው የነበሩ የሙዚቃ ዝግጅቶቹ መሰረዛቸው የሚታወስ ነው።
ይሄም ኮንሰርት ከደህንነትና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሶስት ጊዜ መገፋቱን የሚናገረው ዲጄ አቢሲኒያ በመጨረሻም ዝግጅቱ በመፈቀዱ ደስተኛ መሆናቸውን አልደበቀም።
''በመጨረሻም ኮንሰርቱ ምንም አይነት ክስተት ሳያጋጥመው በሰላም ተጠናቋል'' ብሏል።
ቴዲ አፍሮ ቀጣይ ኮንሰርቱ በጃማይካ ሞንቴጎ ቤይ በሚያዝያ መጨረሻ አካባቢ በሚካሄደው የሶስት ቀን ሮያል ፌስቲቫል ይሆናል።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ቴዲ አፍሮ ፖለቲካዊ ይዘት ባላቸው ግጥሞቹና ፍቅርን በሚሰብኩ ዘፈኖቹ ይታወቃል።












