የኮሮናቫይረስ ተጽዕኖ በቻይናና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ

ኮሮናቫይረስ በቻይና ኢኮኖሚ አሉታዊ የሆነ ጫና አሳድሯል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኮሮናቫይረስ በቻይና ኢኮኖሚ አሉታዊ የሆነ ጫና አሳድሯል

ቻይና በኮሮናቫይረስ በርካታ ዜጎቿን በሞት ከመነጠቋም በተጨማሪ፤ በምጣኔ ሃብቱ ረገድም በዋናነት እየተጎዳች ያለችው ቻይና ስትሆን ሌሎች አገራትም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል።

የመጣኔ ሃበቱ ጉዳት በቀጥታ ቫይረሱ በቀጥታ ያስከተው ብቻ ሳይሆን ቫይረሱን ለመከላከልም ከፍተኛ ወጭ ጠይቋል።

11 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የዉሃን ከተማ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የከተማዋ መግቢያ መውጫ በሮች ተዘግተዋል።

በሁቤይ ግዛት በሚገኙ ሌሎች ከተሞችም የሰዎችና የሸቀጦች ዝውውውር እንዲገደብ እየተደረገ ነው። ይህም ለከተሞቹ ትልቅ ኪሳራ ከፍተኛ ይዞ መጥቷል።

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎችም ወደ ሥራ ስንሰማራ ቫይረሱ ሊይዘን ይችላል በማለት ሥራ መስራትና ከሰዎች ጋር መገናኘትን አቁመዋል።

ምግብ ቤቶች፣ ሲኒማዎች፣ የትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች፣ ሆቴሎችና ሱቆች የመጀመሪያዎቹ የምጣኔ ኃብት ቀውሱ ተጠቂዎች ናቸው።

አምራቾችም ከቻይና ውጭም ገበያ ለማፈላለግ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።

ባቡር ውስጥ ብቻውን የተቀመጠ ተሳፋሪ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባቡር ውስጥ ብቻውን የተቀመጠ ተሳፋሪ

ዓለም አቀፍ አከፋፋዮችም ለጊዜው በቻይና ያላቸውን መደብር እየዘጉ እየወጡ ነው። አይኪያ የተባለው የቤት እቃ አምራች ኩባንያ እና ስታርባክስ አገልግሎታቸውን በቻይና ካቋረጡት ተጠቃሽ ናቸው።

ቻይና በግዥው ሂደት በብዛት የምትሳተፍባቸው የኢንዱስትሪ ነክ ምርቶች በከፍተኛ ደረጃ በዓለም አቀፉ ገበያ ዋጋቸው ቀንሷል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ቢያንስ በ15 በመቶ ቀንሷል። ይህ ደግሞ የሆነው የቻይናው ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ 'ሲኖፔክ' የማጣራት አቅሙን በመቀነሱ ነው ተብሏል።

በቫይረሱ ምክንያት ባዶ የቀረ ሬስቶራንት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በቫይረሱ ምክንያት ባዶ የቀረ ሬስቶራንት

በርካታ የነዳጅ አምራች አገራት ዋጋውን እንደገና ለመጨመር የምርት መጠናቸውን ለመቀነስ እየተነጋገሩ ይገኛሉ። መዳብም በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በ13 በመቶ ከነበረበት ዋጋ አሽቆልቁሏል።

አንድ የኦክስፎርድ ምሁር በቫይረሱ ምክንያት የቻይና ምጣኔ ሃብት በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ4 በመቶ ባነሰ ያድጋል በማለት ትንበያቸውን አስቀምጠዋል።