ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩት ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተገለጸ

የፎቶው ባለመብት, SMITH COLLECTION/GADO
ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩት አራት ግለሰቦች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሁለት ቀናት በፊት በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ ሌሎች አዲስ አራት ሰዎች መገኘታቸውን አስታውቆ ነበር።
ከቀናት በፊት በቫይረሱ የተጠረጠሩት ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ቻይናዊ ነበር።
የጤና ጥበቃ ሚንስትር ከበፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳስታወቀው የአራቱ ግለሰቦች የደም ናሙና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለምረመራ ተልኮ ውጤቱ ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል ብሏል።
ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ መልኩ በቫይረሱ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ አራት ሰዎች ተገኝተው የደም ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው መነገሩ ይታወሳል።










