የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ደፍሮ የገደለን ተጠርጣሪ ስም ይፋ እንዲደረግ ወሰነ

የተማሪዋን ሞት ተከትሎ የተነሳው የተቃውሞ ሰልፍ

የፎቶው ባለመብት, Gallo Images

የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ19 አመቷን ኡይኔኔ ምርዌትያናን ደፍሮ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ላይ ስሙ ይፋ እንዳይሆን ጥሎት የነበረውን ገደብ አንስቷል።

የቀድሞ የፖስታ ቤት ሰራተኛው ሉያንዳ ቦታ የሚባል ሲሆን ነሐሴ ወር ላይ ነው ተጠርጥሮ የታሰረው፤ እስካሁንም ጥፋተኛነቱን አላመነም።

በወቅቱ የኬፕታውን ዩኒቨርስቲ ተማሪዋ እቃ ለመውሰድ ፖስታ ቤት አቅንታ በነረበት ወቅት ደፍሮ በብረት ዘንግ እስክትሞት ድረስ እንደቀጠቀጣት ተገልጿል።

ጥቁር ሹራቡም በደም እንደተለወሰ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

የተማሪዋ መሞት በኃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፤ ብሔራዊ የተቃውሞ ሰልፍም ተደርጓል።

ከዚህም በተጨማሪ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቀጣይዋ እኔ ነኝ በሚል ሃሽታግም በኃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አጋልጧል።

ይህንንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጥቃት በሚያደርሱት ላይ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።