ኢሎን መስክ፡ አሜሪካዊው ሰዎችን ወደ ማርስና ጨረቃ ለማጓጓዝ እየሠራ ነው

'ስታርሽፕ ኤም ኬ1'

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኤም ኬ 1 'ስታርሺፕ' በሚመጡት ሳምንታት የከፍታ በረራ ሙከራ ያደርጋል
Presentational white space

'የስታርሽፕ' [ተወርዋሪው አውሮፕላን እና ግዙፍ ሮኬት] ወደ ጨረቃና ማርስ ለማስወንጨፍ እየሠራ የሚገኘው አሜሪካዊው ሥራ ፈጣሪ ኢለን መስክ የደረሰበትን ደረጃ አስታወቀ።

ሥራ ፈጣሪው አዲሱን መጓጓዣ ሰዎችን ወደ ጨረቃና ማርስ ለመላክ እንዲሁም በጣም በፈጠነ መልኩ መሬትም ላይ ሰዎች እንዲጓጓዙበት ለማስቻል አቅዶ እየሠራ ነው።

መንኮራኩሩ (ስታርሽፕ) 100 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ጨረቃ ማድረስ የሚያስችል አቅም አለው።

የስፔስ ኤክስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢለን መስክ በመጪው ወራት በረራውን ለማስጀመር እቅድ በማውጣት ሂደት ላይ ይገኛል።

'ኤምኬ1' የተሰኘው ይኽው ተወንጫፊ በሚመጡት አንድ ወይም ሁለት ወራት ውስጥ ከፍታ ቦታዎች ላይ በመብረር ሙከራ እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ሥራ ፈጣሪው ኢለን መስክ ሮኬቱ በተገጣጠመበት እና በቴክሳስ በሚገኘው ቦካ ቺካ ድርጅቱ፤ ለተሰበሰቡት ሰዎች "እስካሁን ካየሁት ሁሉ ያስደነቀኝ ፈጠራ ነው" ሲል ተናግሯል።

በመሆኑም ሲል ያክላል ኢለን፤ "ፈጠራው 65 ሺህ ጫማ ወይም 20 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ በመብረር ተመልሶ መጥቶ ማረፍ ይችላል፤ ይህን የሚያህል ግዙፍ አውሮፕላን በርሮ ተመልሶ ሲያርፍ ማየት የሚገርም ነው" ብሏል።

50 ሜትር ርዝመት ያለው ተወርዋሪው አውሮፕላን እጅግ በጣም ከባድ ወደ የሆነ ከፍታ መብረር ይችላል ተብሏል።

የዚህ ሮኬት የመጀመሪያ የበረራ ሙከራ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ ወደ ምህዋር ሊሄድ እንደሚችል መስክ ተናግሯል።

"ነገሩ የማይቻል ቢመስልም በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ጠፈር ለመሄድ ጥረት እያደረግን ነው። ይህንን እውን ለማድረግም የዲዛይንና ሌሎች የሚስፈልጉ የመገጣጠም ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። ይህም በቅርብ ጊዜ የሚታይ ይሆናል" ብሏል።

ሁለቱ የአውሮፕላኑ ክፍሎች ሲገጣጠሙ 118 ሜትር ርዝመት ይኖራቸዋል፤ በድጋሚ መጠቀም እንዲቻል ተደርገው የተሠሩም ናቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን አገልግሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ በሰላም እንዲያርፉም ያግዛቸዋል።

በጊዜ አጠቃቀሙ ዝንፍ እንደማይል የሚታወቀው ኢለን የጊዜ አጠቃቀሙን በተመለከተ 'ኢለን ታይም' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

ኢለን በታሪክ ግዙፍ የሆነውንና የሰው ልጆችን ወደ ጨረቃና ማርስ እንዲሁም ወደ የተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በፍጥነት የሚያጓጉዘውን ሮኬት አስመልክቶ የደረሰበትን ይፋ አስድርጓል።

በዚህ የወደፊት በራሪ 'ፋልኮን 9' የተባለውን የፈጠራ ሥራ ሙሉ ለሙሉ ለመተካት ይፈልጋል።

የአሜሪካው ስፔስ ኤጀንሲ ናሳ አስተዳዳሪ የሆኑት ጂም ብራይደንስቲን በትዊተር ገፃቸው ላይ 'የስታርሽፕ' ጉዳይ ስፔስ ኤክስ ኩባንያን በናሳ ከሚያካሂደው ምርምር የሚያናጥበው ወይም የሚረብሸው አይደለም፤ ተደጋጋፊ ዓላማ ነው ያለን ሲሉ አስፍረዋል።

እስካሁን በስታርሽፕ በረራ ለመሳፈር አንድ ደንበኛ የተመዘገቡ ሲሆን ደንበኛው ጃፓናዊው ቢሊየነር ያሱካ ማዚዋ ናቸው። እርሳቸው ከአርቲስቶች ቡድን ጋር በመሆን ጨረቃን ከእግር እስከ ራሷ አይተው የመመለስ ፍላጎት አላቸው።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

Presentational white space