ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ስእል በአንዲት አዛውንት ማእድ ቤት ተገኘ

ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያወጣል የተባለው ስእል

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

በፈረንሳይዋ ፓሪስ አቅራቢያ በአንዲት አዛውንት ኩሽና ተገኘ የተባለው የስእል ስራ በአስራ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ የሚታመን ነው።

ለረዥም ጊዜያት የት እንደገባ ጠፍቶ የነበረው እሄ የስእል ስራ ባለቤት ጣልያናዊው ሲምባው ወይም ሲኒ ዲ ፒፖ እንደሆነም ኤክስፐርቶች አስታውቀዋል።

እርግጥም ይህ የጥበብ ስራ የዚህ ጣልያናዊ መሆኑን ለማረጋገጥ በኢንፍራሪድ ምርመራም ተካሂዷል።

ስእሉ እአአ በሚቀጥለው ወር ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን 6̂.5 ሚሊዮን ዶላር ድረስ ሊያወጣ እንደሚችል ተገልጿል።

ዘመናትን የተሻገረውና ከፍተኛ ዋጋ ያለው ይህ ስእልን ያስቀመጡት አዛውንት ስእሉ ትልቅ የጥበብ ዋጋ ያለው ሃይማኖታዊ ስእል እንደሆነ ያምኑ እንደነበርም ተገልጿል።