ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ኢኳዶር የዊክ ሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅን እቃዎች ለአሜሪካ ማስረከብ ጀመረች
ኢኳዶር በለንደን ኤምባሲዋ የቀሩ የጁሊያን አሳንጅ እቃዎችን ለአሜሪካ ማስረከብ ጀመረች።
እቃዎቹ ኤሌክትሮኒክስ ፣ፅሁፎች ፣ የህግ ሰነዶችና የህክምና ሪፖርቶች ይገኙባቸዋል።
የአሳንጅ ጠበቃ እርምጃውን በጥገኝነት የሂደት ታሪክ ፈፅሞ የማይጠበቅ ሲሉ አውግዘውታል።
አሜሪካ የተለያዩ አገራት ሚስጥሮችን ያጋለጠው ዊኪሊክስ ድረ ገፅ መስራች አሳንጅ ከእንግሊዝ ተላልፎ እንዲሰጣት ትፈልጋለች።
ዊኪ ሊክስ በርካታ የአሜሪካ ምስጢራዊ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ መረጃዎች ይፋ ማውጣቱ የሚታወስ ነው።
ትውልደ አውስትራሊያዊው አሳንጅ ኮምፒውተሮችን በመጥለፍ እንዲሁም በርካታ የመንግስት ምስጢሮችን በማሾለክ ተወንጅሏል። በዚህም እስከ አምስት አመት ሊፈረድበት ይችላል።