መንትዮቹ ዶክተሮች፡ እየሩሳሌም ጌታሁንና ቃልኪዳን ጌታሁን

ዶ/ር ቃልኪዳን ጌታሁንና ዶ/ር እሩሳሌም ጌታሁን

የፎቶው ባለመብት, Dr. kalkidan

የምስሉ መግለጫ, ዶ/ር እየሩሳሌም ጌታሁን (በግራ) እና ዶ/ር ቃልኪዳን ጌታሁን (በቀኝ)

መንትዮቹ ዶ/ር ቃልኪዳን ጌታሁንና ዶ/ር እየሩሳሌም ጌታሁን ተወልደው ያደጉት በሻሸመኔ ከተማ ነው። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉትም እዚያው ነው። ከዚያም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል።

በአዲስ አበባ ሃያት ሜዲካል ኮሌጅ ገብተው ህክምና አጥንተዋል። አሁንም በማዕረግ ነበር የተመረቁት። ሻሸመኔ መልካ ወረዳ ሪፈራል ሆስፒታል ተመድበው የተወሰነ ጊዜ አገልግለዋል። በአሁን ሰዓት 'ትዊንስ ክሊኒክ'ን ከፍተው እየሠሩ ይገኛሉ።

በትዊንስ ክሊኒክ ከህክምናው ባሻገር ዶ/ር እየሩሳሌም ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቃልኪዳን ደግሞ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ያገለግላሉ።

ዶ/ር እየሩሳሌም ለዶ/ር ቃልኪዳን የ5 ደቂቃ ታላቅ ናት።

ድምፃቸው፣ ቁመታቸው፣ ክብደታቸው፣ የትምህርት ውጤታቸው፣ ስሜታቸው፣ ፍላጎታቸው፣ የጫማ ቁጥራቸው በጣም ይመሳሰላል። ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ ታካሚዎቻቸውና ሌሎችም እነርሱን ለመለየት ይቸገራሉ።

እኩል ይደሰታሉ፤ እኩል ያዝናሉ፤ አንደኛቸው ህመም ሲያጋጥማቸውም ስሜቱ ለሌላኛቸውም ይተርፋል። አለባበሳቸው፣ የፀጉር አሠራራቸው እንዲሁም የሚያደርጉት ጌጥ ተመሳሳይ በመሆኑ መምታታቱን ጨምሮታል። እነርሱ እንደሚሉት የባህርይ ልዩነትም የላቸውም።

የማያመሳስላቸው ምንድን ነው?

አምጠው የወለዷቸው እናታቸው እንኳን በቀላሉ አይለዩዋቸውም። ብዙ ጊዜ ከስህተት በኋላ ነው ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚያረጋግጡት። ከአገር ውጭ የሚገኙ እህትና ወንድሞቻቸው በስልክ ሲያናግሯቸው ማንነታቸውን ካልገለፁ በስተቀር አንደኛቸው ሌላኛቸውን ወክለው መልስ ቢሰጡ አይነቃባቸውም።

መንትዮቹ ዶክተሮች

የፎቶው ባለመብት, Dr. Kalkidan

በጣም የጎላ መለያየትና የማያመሳስላቸው ባይሆንም በንፅፅር ሰዎች የሚለዩባቸው መንገዶች ግን መኖራቸው አልቀረም- ያም ቢሆን ለቅርብ ሰው ነው።

"ቃል ኪዳን ከእኔ በተለየ ተግባቢ፣ ተጨዋችና ሳቂታ ናት፤ እኔ ደግሞ ኮስታራና ዝምተኛ ነኝ" ትላለች ዶ/ር እየሩሳሌም ልዩነታቸውን ነቅሳ ስታወጣ።

ዶ/ር ቃልኪዳን በበኩሏ"ብዙም ባይሆን በክብደት እኔ እበልጣለሁ፤ እርሷ ከእኔ ቀጠን ትላለች፤ ባህርያችን ተመሳሳይ ቢሆንም እኔ ትንሽ የመቸኮል፤ በተቃራኒው እየሩስ ደግሞ የመረጋጋትና ጊዜ የመስጠት ሁኔታ አለ" ትላለች።

በዚህም አንዳንድ ሰዎች እንደ ምንም እንደሚለዩዋቸው ይናገራሉ- መንትዮቹ።

"አንገቴ ላይ ጥቁር ነጥብ አለኝ፤ እየሩሳሌም ላይ ግን ይህች ምልክት የለችም" የምትለው ቃልኪዳን ይህ ካልሆነ በስተቀር በአካላቸው ላይ አንዳቸውን ከአንዳቸው የሚለይ ምልክት የለም።

እነርሱ እንደሚሉት አብዛኛውን ጊዜ አንድ ላይ ነው የሚውሉት፤ ተለያይተው የሚውሉበት አጋጣሚ እምብዛም ነው። ይሁን እንጂ በልጅነት ጊዜያቸው ከእህትና ወንድሞቻቸው ጋር የመሸዋወድ አጋጣሚዎች እንደነበሩ እየሩሳሌም ታስታውሳለች።

ቃልኪዳንም የማትረሳው አጋጣሚ አላት። እርሷ እንደምትለው እናታቸው ለእየሩሳሌም የማዳላት ነገር እንዳለ ይሰማታል። ሁኔታው የከነከናት ቃልኪዳንም እውነቱን ከእርሳቸው ለመስማት ፈለገች። እናም እናቷ በተኙበት እየሩሳሌምን ሆና ቀስ ብላ ሄደች።

ቃልኪዳን፡ "ግን ለምንድን ነው እኔን ከቃልኪዳን የምታስበልጭው?"

እናት፡"ሁለታችሁም ለእኔ እኩል ናችሁ፤ አንድ ዓነት ናችሁ አለያችሁም " ሲሉ ይመልሳሉ።

ቃልኪዳን፡"እርሷን ግን ትንሽ ታስበልጫለሽ?" እናቷ የምትጠይቃቸው ቃልኪዳን እንደሆነች አልለዩምና እውነቱን መናገር ጀመሩ።

እናት፡"እየሩስዬ፣ ትንሽ ወደ አን የማደላውና የማጋድለው ስለሚያምሽ ነው" ሲሉ በራራ የእናት አንደበት ይመልሳሉ (በእርግጥ በጊዜው እየሩስን ትንሽ ያማት ነበር)።

በኋላ ላይ ማንነቷን ሲለዩ በጣም ነበር የደነገጡት፤ ይህን አጋጣሚ እናታቸውም አይረሱትም፤ ሁልጊዜም በቤታቸው ይነሳል።

ታካሚዎቻቸውም ዶክተሮቹን ለመለየት ይቸገራሉ፤ ነገርግን መንታ መሆናቸውን ሲያውቁ አንዳቸውን ከአንዳቸው ለመለየት ምልክት ማጥናት ይጀምራሉ።

መንትዮች አንድ ዓይነት አለባበስና አጊያጊያጥ ለምን ይከተላሉ?

ቃልኪዳን እንደምትለው ፍላጎታቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ተመሳሳይ ስለነበር የሚገዛላቸው ነገር ሁሉ ተመሳሳይ ነው። እንደውም ልጅ እያሉ ትንሽ መለያየት ሲኖረው እንኳን ደስተኛ አይሆኑም።

አሁንም ያላቸው ፍላጎት ተመሳሳይ ነው። ተመሳሳይ አልባሳትና ጌጣጌጥ ለማግኘት የሚችሉትን ያህል ይሞክራሉ። ብዙ ጊዜ የሚፈልጉትን ለማግኘት አይቸገሩም።

የእየሩሳሌም ሐሳብም ተመሳሳይ ነው። "በልጅነታችን ልብሳችን ላይ አንዳች ልዩነት ስናይ እናለቅሳለን፤ እናታችን እንደገና ሄዳ ትለውጣለች" ስትል ትውስታዋን አጋርታናለች።

መንትዮቹ

የፎቶው ባለመብት, Dr. Kalkidan

ፍላጎትም ብቻ ሳይሆን የሰዎችም ግፊት አለበት። የተለያየ ልብስ ሲለብሱ ጥያቄ ይበዛባቸዋል። ጥያቄው የሚበዛው ሲለያዩ እንጂ ሲመሳሰሉ አይደለም።

ፎቶግራፍ የሚጠየቅባቸው የትምህርት፣ የሥራና ሌሎች የሕይወት እንቅስቃሴዎች መለየት ስለሚያዳግት የአንደኛቸውን ፎቶ በሌላኛዋ መረጃ ላይ አሳስተው ይለጥፉታል። "ብዙ ጊዜ አንድ ዓይነት ስለምንለብስ መለየት አይችሉም" ይላሉ።

በዚህም ምክንያት ፎቶግራፋቸው ጀርባ ላይ ስማቸውን እንዲፅፉ ይጠየቃሉ።

የመንትዮቹ የትምህርት መስክም ሆነ የትምህርትና ሥራ ምደባ ተመሳሳይ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ እንጂ እነርሱ ያደረጉት ጥረት የለም።

ይሁን እንጂ የሥራ ምደባ ሲደረግ እንለያይ ይሆን የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር። የፈሩት አልቀረም ታዲያ እየሩሳሌም በጂማ ኒቨርሲቲ እንድታስተምር ተመደበች።

ሥራ ከመጀመሯ አስቀድሞ ለሥልጠና ወደ አዳማ ዩኒቨርስቲ አቀናች- ለሁለት ሳምንታት ብቻ። ያኔ ቃልኪዳን አዲስ አበባ ነበረች።

መንትዮቹ በመመረቂያ ገዋን

የፎቶው ባለመብት, Dr. Kalkidan

ይህ ወቅት ለቤተሰቡ ሁሉ ፈተና ሆኖ ማለፉን ሁለቱም አይዘነጉትም። 'መለያየት ሞት ነው'ን የዘፈኑት ያኔ ነው ማለት ይቻላል። አሁን ግን የልባቸው ሞልቶ አንድ የሥራ ገበታ ላይ ተሰይመዋል።

መንትዮቹ ራሳቸውን በበጎ ሥራ ጠምደዋል። መንትዮቹ ማኅበርን (Twins Association) አቋቁመዋል። የፌስቡክ ገፅ ከፍተው በማንኛውም ዕድሜ የሚገኙ መንትዮችን ማሰባሰብ ጀምረዋል።

ዓላማው ብዙ ቢሆንም መንትዮችን ማሰባሰብ፣ የመንትዮችን ቀን ማክበር፣ ልምዳቸውንና ተግዳሮቶቻቸውን የሚጋሩበትና የሚተወቃወቁበት ማኅበር ነው። ይህንን ዓላማ ለማሳካትም በሂደት ላይ እንደሚገኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል -መንትዮቹ ዶክተሮች።

እንደ ጨዋታ...

ቢቢሲ፡ መንትዮች የፍቅር ግንኙነት ላይ አንዳቸው ባንዳቸው ቅናት ያድባቸዋል ባላል?

እየሩሳሌም፡ መስፈርታችን ተመሳሳይ ስለሆነ የምንፈልገው ተመሳሳ መሆኑ አይቀርም (ረዥም ሳቅ) እንዲያውምመንትያ ሲ መንትያ የይወት አጋር ቢኖርይባላል ያ ደግሞ አያጋጥምምለታችንምበጎ ነገር ከገጠመ አንዳችን ላንዳችን ደስተኛ ነው የምንሆነው። እዲህ ዓነት ስሜት እኛ ጋ የለም።

ቃልኪዳን፡መንታ ይምጣ ነዋ የምንለው (ሳቅ)... ቅናቱን በተመለከተ ግን ሰዓት መማቱ ስለሚኖር ትንሽ ቅር ሚል ነገር ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ያንዳችን ደስታና ስኬት ስለሚያልብን ያን ያህል የከፋ ነገር አይኖርም