በኬንያ የ27 ዓመቱ ቶም ጁኒየር ማኮ በአንድ ሰርግ ሁለት ሚስቶችን አገባ የሚሉና ሌሎችም

ኬንያዊው ከሚስቶቹ ጋር

ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚፈፀሙ ማንኛውም አይነት ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ማሳወቅ የሚቻልባቸውን የስልክ መስመሮች ይፋ አደረገ።

በስልክ መስመሮቹ በህገወጥ መንገድ ስለተያዙ መሬቶች፣ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እንዲሁም የቀበሌ ቤቶችና ሌሎችም ጥቆማ መስጠት ይቻላል።

ሶማሊያ

የቀድሞ የአልሻባብ ኮማንደር ሙክታር ሮቦው ትናንት ባይደዋ ላይ በቁጥጥር ስር መዋልን ተከትሎ በአካባቢው ግጭት ተቀስቅሷል።

በባይደዋ ከተማ በግጭቱ የኮማንደሩ ደጋፊዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች መሞታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ኬንያ

የ27 ዓመቱ ኬንያዊ ሁለት ሚስቶችን በአንድ የሰርግ ስነስርዓት አገባ።

ጋብቻው የተፈፀመው ካጃዶ በተሰኘ የኬንያ ግዛት ሲሆን ወጣቱ ያገባቸው ሴቶች የ23 እና የ25 ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የቀናት እድሜ ያላት ህፃን በህክምና ከኢቦላ ቫይረስ ዳነች።

'ተአምረኛ' የተባለችው ህፃን በአለም አቀፍ ደረጃ ከኢቦላ መትረፍ ከቻሉ ሰዎች በእድሜ በጣም ትንሿ ሆናለች።

ኢቦላ ቫይረስ ተይዛ የነበረችው እናቷ የሞተችው ህፃኗን ስትወልድ ነው።

ደቡብ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ የመጀመሪያ የተባለውን የማሪዋና ንግድ ትርኢት ልታካሂድ ነው።

ለአራት ቀናት በጆሃንስበርግ ይካሄዳል የተባለው የንግድ ትርኢት ማሪዋና ለጤና የሚሰጠው ጠቀሜታ ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።

ጃፓን

ዘጠኝ የጃፓን የህክምና ትምህርት ቤቶች ሴት ተማሪዎችን ላለመቀበል አሻጥር መስራታቸውን መንግስት አስታወቀ።

ዩኒቨርሲዎቹ ሴት ተማሪዎች ህክምና እንዳያጠኑ ያደረጉት ውጤታቸውን በመቀነስ ነው።

አሜሪካ

አሜሪካ በአፍሪካ የትኩረት አቅጣጫዋን እንደምትቀይር አስታወቀች።

አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ስትራቴጂ ቻይናና ሩሲያ በአህጉሪቱ ያላቸውን ተፅእኖ መቀነስ ላይ የተመሰረተ እንደሚሆን የአገሪቱ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ተናግረዋል።