ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የላውሮ ግምት፡ አርሴናል ከቶተንሃም እንዲሁም ሊቨርፑል ከኤቨርተን
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሦስት ደርቢዎች ይካሄዳሉ፤ የለንደን እና መርሲ ሳይድ ደረቢ።
ኤምሬትስ ላይ አርሴናል ቶተንሃምን ሲያስተናግድ አንፊልድ ላይ ደግሞ ሊቨርፑል እና ኤቨርተን ይጫወታሉ። ቼልሲ በበኩሉ በሜዳው ፉልሃምን ያስተናግዳል።
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን እነዚህን ጨምሮ የሌሎቹንም ጨዋታዎች ግምት አስቀምጧል።
የላውሮ ግምቶች
አርብ
ካርዲፍ ከዎልቭስ
ዎልቭሶች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ማግኘት የቻሉት አንድ ነጥብ ብቻ ነው። ከእነዚህ ጨዋታዎች በአንዳንዶቹ ጥሩ መንቀሳቀስ ችለዋል።
ካርዲፎች በበኩላቸው በኤቨርተን 1 ለ 0 ተሸንፈዋል። ኤቨርተኖች ጨዋታውን ማሸነፍ የሚገባቸው ቢሆንም ካርዲፎች ጥሩ ተንቀሳቅሰዋል። ይህን ደግሞ ከዎልቭስ ጋርም ይደግሙታል።
የላውሮ ግምት: 1-1
ቅዳሜ
ክሪስታል ፓላስ
ሁለቱም ቡድኖች ከወራጅ ቀጠና ትንሽ ከፍ ያሉ ሲሆን ጎል የማስቆጠር ችግርም አለባቸው።
ፓላሶች ባለፈው ሳምንት ወደ ኦልድትራፎርድ በማቅናት አንድ ነጥብ ማግኘታቸው ጥሩ ሲሆን በዚህ ሳምንት ነጥብ መጣል አይኖርባቸውም።
የላውሮ ግምት: 1-0
ሃደርስፊልድ ከብራይተን
ዎልቭስን ካሸነፉት ሃደርስፊልዶች ጋር የሚደረገው ጨዋታ ለብራይተኖች ከባድ ነው።
ሃደርስፊልዶች ካለፉት ደካማ ውጤቶች በኋላ ጥሩ ውጤት ከማስመዝገባቸውም በተጨማሪ ጥሩ እየተንቀሳቀሱ ነው።
የላውሮ ግምት: 1-0
ሌስተር ከዋትፎርድ
ሌስተሮች በሜዳቸው ካሸነፉ ወራት ተቆጠሩ።
ዋትፎርዶች ባለፈው ሳምንት በሊቨርፑል በሦስት ጎል መሸነፍ አልነበረባቸውም።
የላውሮ ግምት: 2-0
ማንቸስተር ሲቲ ከበርንማውዝ
በርንማውዞች ከሦስት ሽንፈት በኋላ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታም የተለየ ውጤት አይጠብቁም።
ስለድል ማሰብ ያለባቸው ከዚህ ሳምንት በኋላ ነው። ምክንያቱም ብዙ ቡድኖች ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ሲጫወቱ የሚያስቡት በዚህ መልኩ ነው።
የላውሮ ግምት: 3-0
ኒውካስል ከዌስት ሃም
ኒውካስሉ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ሲጀምሩ ለብዙ ጨዋታዎች ነው። ባለፉት አራት ጨዋታዎችም አልተሸነፉም።
ዌስት ሃሞች ደግሞ ከስድስት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ነው ያሸነፉት። አቋማቸው የሚዋዥቅ ቡድን ቢሆንም ወደ ወራጅ ቀጠና ይገባሉ ብዬ አላምንም።
የላውሮ ግምት: 2-0
ሳውዝሃምፕተን ከማንቸስተር ዩናይተድ
ሳውዝሃምፕተኖች ውጤታማ መሆን እየቻሉ አይደለም። ማንቸስተር ዩናይትዶችም ቢሆኑ ጥሩ ባይሆኑም በዚህ ጨዋታ ግን የበላይ ይሆናሉ።
ከክሪስታል ፓላስ እና ያንግ ቦይስ ጋር እንዳየነው ዩናይትዶች በአጥቂ መስመር ችግር አለባቸው። ሆኖም ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ።
የላውሮ ግምት: 0-2
እሑድ
ቼልሲ ከፉልሃም
አዲሱ የፉልሃም አሰልጣኝ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ድል ቢያስመዘግቡም ይኼኛው ግን ከባድ ይሆንባቸዋል።
እንደገመትኩትም ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት ወደ ቶተንሃም በማቅናት የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል። ሆኖም ተከታታይ ሽንፈት ወይም ውጤት ማጣት ይገጥማቸዋል ብዬ አላስብም።
የላውሮ ግምት: 2-0
አርሴናል ከቶተንሃም
ቶተንሃሞች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሊጉም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ከባድ ጨዋታዎች ቢገጥሟቸውም ሁሉንም አሸንፈዋል። ከዚህ በተጨማሪ የተጫዋቾች ከጉዳት መመለስና ማገገም ይህን ጨዋታ ያሸንፋሉ እንድል አድርጎኛል።
አርሴናሎች ባለፉት ጨዋታዎች አላሳመኑኝም። ሆኖም ባለፉት 18 ጨዋታዎች ሳይሸነፉ ለመጓዝ ችለዋል።
የላውሮ ግምት: 1-2
ሊቨርፑል ከኤቨርተን
ኤቨርተኖች በአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ስር ጠንካራ በመሆን ላይ የሚገኙ ሲሆን መጀመሪያ የመርሲ ሳይድ ደርቢያቸው ግን ከባድ ፈተና ነው።
ሊቨርፑሎች በሊጉ አናት ላይ ከማንቸስተር ሲቲ ላለመራቅ ኤቨርተኖች ደግሞ እስከአራት ያለውን ደረጃ ለመያዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ከባድ ይሆናል።
የላውሮ ግምት: 2-0