የነጻነት ቅርጫት፡ ማሕበራዊ ሚዲያ

Social media image
ተጨማሪ ከዚህ በታች ያንብቡ
ሌላ መሣሪያ ለመምረጥ ይህን ይለፉ
News image

ዛሬ ላይ በዓለማችን ላይ ከሚኖረው የሰው ልጅ መካከል ግማሽ ያህሉ እንደ ፌስቡክ እና ትዊተር የመሳሰሉ ማሕበራዊ ሚዲያዎችን ይጠቀማል።

በምራብ እና ሰሜን አውሮፓ ደግሞ ከ10 ሰዎች አንዱ ቢያስ አንድ የማሕበራዊ ሚዲያ ኔትወርክ ተጠቃሚ ነው።

በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የተጓደኘናቸውን ወዳጆቻችንን አልያም ከምንከተላቸው ታዋቂ ግለሰቦችን ጋር የእራሳችንን ህይወት የምናነጻጽር ከሆና ምናልባትም እራሳችንን ችግር ውስጥ እየከተትን ሊሆን ይችላል።

የጥናት ውጤቶች እንደሚያሳዩት፤ የማሕበራዊ ሚዲያ አብዝተው የሚጠቀሙ ግለሰቦች በአዕምሮ ህመም መጠቃታቸውን ሪፖርት የማድረጋቸው አጋጣሚ ከፍተኛ ነው።

በተለየ መልኩ ወጣት ሴቶች ማሕበራዊ ሚዲያው ስለ መልካቸው አብዝተው እንዲጨነቁ እንደሚያደርጋቸው ይናገራሉ። ገርልጋይዲንግ የተባለ ድርጅት ያካሄደው ጥናት እንደጠቆመው፤ ዕድሜያቸው ከ7-10 የሆኑ ታዳጊ ሴቶች የማሕበራዊ ሚዲያ በሚጠቀሙበት ወቅት ዋናው የሚያሳስባቸው ጉዳይ የመልካቸው ነገር ነው። በጥናቱ ከተካተቱት ሲሶው እንከን የለሽ የሆነ መልክ ኖሮን መታየት እንሻለን ብለዋል።

ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ።

በሌላ በኩል ስለ ማሕበራዊ ሚዲያ በጎ አስተያየት የሚሰጡ በርካቶች አሉ። ማሕበራዊ ሚዲያው ሰዎች የተሰማቸውን እንዲገልጹ እና ውይይት እንዲያደርጉ እድል ይሰጣል ይላሉ።