ማላዊቷ ነርስ በማዋለጃ ክፍል 'ሰልፊ' በመነሳቷ ከስራ ታገደች

ቁጣን የቀሰቀሰው ፎቶ

የፎቶው ባለመብት, Malawi 24

የማላዊ ዜግነት ያላት ነርስ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ 'ሰልፊ' ተነስታ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፏ ከስራ ታግዳለች።

ቀጣይ ምርመራም እንደሚደረግ ተገልጿል።

ይህ ብዙዎች ያጋሩትና ለመውለድ የተዘጋጀች ሴት እርቃኗን ተንጋላ የሚያሳየው ፎቶ ቁጣን አስነስቷል።

የማላዊ የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ጆሹዋ ማላንጎ ለ ቢቢሲ ፎከስ አፍሪካ ራዲዮ ፕሮግራም እንደተናገሩት ፎቶውን "አስደንጋጭ" ብለውታል።

በተጨማሪም ጉዳዩ ወደ ነርሶች ማህበር የተመራ ሲሆን ፎቶውን ማን እንዳነሳውና እንዳሰራጨው ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።