በጀርመን በርሊን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢሊዩድ ኪፕቾጌ የዓለምን ክብረ ወሰን ሰበረ

ኬንያዊው አትሌት ኢሊዩድ ኪፕቾጌ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኬንያዊው አትሌት ኢሊዩድ ኪፕቾጌ

ኬንያዊው ኢሊዩድ ኪፕቾጌ በጀርመን በርሊን በተካሄደው የማራቶን ውድድር 2፡1፡39 ሰከንድ በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብሯል። የ 33 ዓመቱ አትሌት በአውሮፓውያኑ 2014 በአገሩ ልጅ ደኒስ ኪሜቶ ተይዞ የነበረውን ሰዓት በ1፡20 ሰከንድ አሻሽሎ ክብረ ወሰኑን የራሱ አድርጓል።

ውድድሩን ባጠናቀቀበት ጊዜም "የዛሬውን ቀን ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል፤ የዓለምን ክብረ ወሰንን በመስበሬ ደስተኛ ነኝ" ሲል ተናግሯል።

ኪፕቾጌ በዚህ ዓመት መጀመሪያ በለንደን የተካሄደውን ማራቶን ለሶስተኛ ጊዜ አሸንፏል። በረጅም ርቀት የኦሎምፒክ አሸናፊም ነው።

"በጣም ከባድ ነበር፤ የራሴን ፍጥነት ነበር የምከተለው፤ አሰልጣኘን አምነዋለሁ፤ ያ ነው በመጨረሻዎቹ ኪሎ ሜትር አፈትልኬ እንዲወጣ ያስቻለኝ ሲል ተናግሯል። በሴቶች ምድብ ኬንያዊቷ ግሌዲየስ ቸሮኖ 2፡18፡11 ሰከንድ በመግባት ድልን ተቀዳጅታለች። በሁለተኛ ደረጃነት ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሩቲ አጋ 2፡18፡34 በመግባት ስታጠናቅቅ፤ ታሸንፋለች ተብላ በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ2:18:55 በመግባት በሶስተኛ ደረጃ ውድድሩን ጨርሳለች።