አብዲ ሞሃመድ ዑመር ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ

አቶ አብዲ ሞሃመድ

የፎቶው ባለመብት, BBC Somali

የሶማሌ ክልልን ለአስር ዓመታት ገደማ ያስተዳደሩት አብዲ ሙሃመድ ዑመር ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው መደበኛ ያልሆነ ጉባዔ ነው አብዲ ሙሃመድ ዑመርን ጨምሮ የሰባት አባላቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የወሰነው።

ምክር ቤቱ የግለሰቦቹን መብት ያነሳበት ምክንያት በቅርቡ በክልሉ ከተነሳው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ እንደሆነም አስታውቋል።

የአባላቱን ያመለከሰስ መብት የማንሳት ውሳኔውንም ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ እንዳፀደቀው ነው የተገለፀው።

ከዚህ በፊት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሙስጠፋ ሙሀመድን ዑመርን የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አድርጎ መሾሙ አይዘነጋም።

ክልሉን ለበርካታ ዓመታት የመሩትን አቶ አብዲ ሙሐመድ ኡመርን በመተካት ለሁለት ሳምንታት ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አህመድ አብዲ ሞሐመድ፤ አቶ ሙስጠፋ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ የፓርቲው ሕገ-ደንብ እንደሚፈቅድላቸው ገልጸው ነበር።