ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የውጭ ምንዛሬ ችግር ያጋጠማት ኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቧን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘገበ።
"ነዳጅ ለማስገባት እየተነጋገርን ነው። ዝርዝሮቹ ገና አላለቁም። በፕሮግራም የተያዘና መደበኛ የነዳጅ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ነው" ማለታቸውን ዘገባው ያመለክታል።
በዶላር እጥረትና የመንገድ መሠረተ-ልማት ችግር ምክንያት እስከ 1 ነጥብ 6 ሚልዮን ቶን የሚገመት ንብረት በጂቡቱ ወደብ ተከማችቶ እንደሚገኝ ዘገባው ጨምሮ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር ውስጥ እንደምትገኝ በመግለጽ ሰሞኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የውጭ ሃገር ገንዘብ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች በባንኮች እንዲመነዝሩ ጥሪ ማቅረባቸው ኣስታውሷል።








