ካለሁበት 33፡ አስቸጋሪ የአየር ንብረትን በቴክኖሎጂ አመቺ ያደረገችው- ስዊድን

ረታ ዳርጌ

የፎቶው ባለመብት, Rattaa Daargee

የምስሉ መግለጫ, ረታ ሰዊድን ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ለኑሮ ምቹ የሆነች አገር ነች ይላል።

ረታ ዳርጌይ ሹረሞ እባላለሁ። ባለትዳርና የሁለት ልጆች እባት ንኝ። በአሁን ጊዜ በስዊድን ቦነስ በምትባል ከተማ ነዋሪ ነኝ። ቦነስ ከስዊድን መዲና ስቶክሆልም የሁለት ሰዓት መንገድ ርቀተ ላይ ትገኛለች።

ሃገሬ እያለሁ በልጅነቴ ሃብትና ንብረት ያፈራሁ ሰው ነበርኩ። በቡና ንግድ ነበር የተሰማራሁት። ቡና ገዝቼ ወደ አዲስ አበባ በመጫን ለማዕከላዊ ቡና ገበያ አቀርብ ነበር። በርትቼ የሙጥኝ ብዬ በመሥራት የግል መኪና ሁሉ ገዝቼ ነበር።

የበለጠ ለማደግም ታላላቅ ጥረቶችን ሳደርግ የነበርኩ ቢሆንም በማንነቴ ምክንያት በሚደርሱብኝ ተጽዕኖዎች ስራዬን ለማቋረጥ ትገደድኩኝ። በዚህም ሥራዬን፣ ኑሮዬን እና ንብረቴን ጥዬ ወደ ሱዳን ኮበለልኩኝ።

በሱዳንም የተለያዩ ገጽታዎች የያዙ ፈተናዎች፣ ስቃይና እንግልት ደርሰውብኛል። ብዙዎች ስደተኞችን በግዳጅ እንዲኖሩ ያደርጋሉ። እዚያ ያለው ችግር ደግሞ ከሁሉ የከፋ ነበር።

በካርቱም ከተማ ሳለው ብዙ ስቃይ አሳልፍያለሁ። ይሁን እንጂ በርትቼና ሳልሰላች ዩኤንኤችሲአርን (የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን) በመከታተል በመጨረሻ ላይ ከ6 ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ስዊድንስ ሃገር ሄጄ ኑሮን ሃ ብዬ ጀመርኩኝ። አሁን ወደ ስዊድን አገር ከመጣሁ 5 ዓመታት አስቆጠርኩኝ።

ስለ ሱዳን ሃገር ያለኝ ትዝታ መከራ ብቻ አይደለም። መልካም ነገሮችም ሆነውልኛል። የምወዳትን ባለቤቴንና የሁለት ልጆቼን እናት በሱዳን ነው ያገኘኝዋት። ይህ ደግሞ ጥሩ ማስታውሻ ነው።

አቶ ረታ ከባለቤቱ እስከዳር ጫላ እና ሁለት ልጆቹ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Rattaa Daargee

የምስሉ መግለጫ, አቶ ረታ ከባለቤቱ እስከዳር ጫላ እና ሁለት ልጆቹ ጋር

ስዊድንን ከኢትዮጵያ በጣም ልዩ የሚያደርጋት ብዙ ነገሮች አሉ። በተለይም እዚህ ሃገር ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት በእጅጉ የሚከበርበት ሃገር መሆኑ ነው። ሰዎች እንደልባችው ሃሳባችውን መግለጽ ይችላሉ። እንኳን የሰው ልጅ ይቅርና ለዱር አራዊት እንኳን የተደነገገ ሕግ አለ።

የስዊድን የአመጋገብ ባህልና ከእኛ በብዙ ይለያል። ይሁን እንጂ ካሉት ብዙ የምግብ ዓይነቶች አብልጬ የምወደው ቶፌስ ወይም ሻትቡላ የሚባለውንና ከተፈጨ ሥጋ የሚሠራውን ነው። እንደ ኳዋስ ድቡልቡል ተደርጎ የሚጠበስና የተለያየ መረቅ ተጨምሮበት ይበላል።

ቶፌስ ወይም ሻት ቡላ የሚባል ምግብ

የፎቶው ባለመብት, Rattaa Daargee

ከሃገሬ … ሰውን፣ ወንዙን፣ ጋራውን፣ ዛፉንም ጨምሮ ሁሉም ይናፍቀኛል። በተልይ ወላጆቼ፣ ቤተስቦቼ፣ ዘመዶቼና ጓድኞቼ በጣም ናፍቀውኛል። እዚህ ኑሮ በግለኝነት ነው። መጠያየቅ የለም።

በዚህ ከተማ አዘውትረን በመሄድ የምንዝናናበትና የምንወደው ቦታ 'ሲማን' የሚባለው ውሃ ዋና ሥፍራ ነው። በእዚህ ማዕከል ከውሃ ዋና ጋር ተያይዞ የተለያዩ ስፖርቶች ያሉበትና ለስው ልጆች ምቾት የሚሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያሟላ ሥፍራ ነው።

እንዲህ ዓይነት ማዕከል በሁሉም ከተሞች ከትልቅ እስከ ትንሽ ከተማ በየቀበሌውና በየመንደሩ ሁሉ የሚገኝ ሲሆን በክረምትና በበጋ እንዲያገለግል ተደርጎ የትሠራ ነው።

የመዝናኛ እና የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ

የፎቶው ባለመብት, Reta Darge

በምኖርበት ከተማና ሃገር ውስጥ አንድ የተለየ ሥልጣንኝ ወይም አቅም ቢኖረኝም፣ በዚህ ሃገር ውስጥ መለወጥ የምፈልገው ነገር ቢኖር ዋነኛው በአሁኑ ጊዜ ሕጋዊ የሆነውን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ህግ መፋቅ ወይም መሰረዝ ነው።

እዚህ ሃገር እንደመጣሁ ትልቅ ችግር ሆኖብኝ የነበረው ቋንቋው ነበር። እኔ ብቻ ሳልሆን ከተለያዩ ሃገሮች የሚመጡ ሰዎች ተመሳሳይ ችግር ይገጥማቸዋል። ቋንቋችውን መማር በጥም ከባድ ነው። እሁን እኔ እስፈላጊ በሆን ደረጃ ቋንቋችውን ከተማርኩ በኋላ በጤናና በሙያ የሚሰጠውን ተክታትዬ በመጨረስ ሥራ ጀምሪያልሁ።

ወደዚህ ሰላማዊና ለሰው ልጅ ኑሮ የተመቻቸ ሃገር በመምጣቴ ብዙ ነገሮች ተሳክተውልኛል። ከሁሉ የሚበልጠው ግን በረከትና የደስታ ምንጭ የሆኑኝን ሁለቱን ልጆቼን እዚህ ስዊድን መውለዴ ነው። ትልቁን ልጄን ኬናዋቅ (የእግዜር ስጦታ) ሲሆን ሁለተኛዋን ደግሞ ሜላላ ትባላለች።

ረታ ከሁለት ልጆቹ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Rattaa Daargee

የምስሉ መግለጫ, ረታ ከሁለት ልጆቹ ጋር

ከዚህ በቅጽበት ነጥቆ ሃገሬ ሊወስደኝ የሚችል ኃይል ቢኖር ከቤተሰቦቼ ጋር እራሴን ማግኘት እመኛለሁ። በተለይ ብምዕራብ ኦሮምያ በምትገኘው አሺ በምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ ነው። ወላጆቼን እና የባለቤቴን ቤተሰቦች ማገናኘትና ልጆቼን ሃገሬን ማሳየት እሻለሁ።

Presentational grey line

የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦