በቀን ምን ያህል ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? ዓይነ ምድራችን ስለጤናችን ምን ያመለክታል?

በቀን ስንት ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ?

የፎቶው ባለመብት, Emmanuel Lafont/ BBC

በቀን ስንት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? አንዴ? ሁለቴ? ወይስ አልፎ አልፎ? ለመሆኑ ዓይነ ምድር ስለ ጤናዎ ምን ያናገራል?

በምንበላበት ጊዜ ሁሉ ትልቁ አንጀት ምግብን ወደ ምግብ መፍጫ ቱቦ ይገፋል።

ይህ ሂደት "ጋስትሮ-ኮሊክ ሪፍሌክስ" ሆርሞኖችን እንዲለቀቁ ያደርጋል። ይህም የመጸዳዳት ፍላጎትን ይፈጥራል።

አብዛኞቻችን ይህንን ፍላጎት መቆጣጠርን ተምረናል። በዚህ ምክንያትም በቀን አንድ ወይም ከዚያ ላነሰ ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት መሄዳችን መደበኛ ሆኗል ማለት ነው።

በአውስትራሊያ ካንቤራ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨጓራ ​​ሕክምና ባለሙያ የሆኑት ማርቲን ቫይይ "ሁላችንም የመጸዳዳት ተፈጥሯዊ ግዴታ አለብን" ይላሉ።

በተለምዶ በቀን አንድ ጊዜ መጸዳዳት ጥሩ የአንጀት ጤና ምልክት እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል።

ቀደም ባሉት ጊዜያት ግን 'መደበኛ ስለሚባል' የአንጀት እንቅስቃሴ አይታወቅም ነበር።

አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በየተወሰነ ሳምንታት ወይም ወራት ውስጥ ከአንድ የአንጀት ንክኪ እስከ 24 ዓይነ ምድር ድረስ ያለው እንደ ጤነኛ ሊቆጠር ይችላል።

በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሚገኘው የብሪስቶል ሮያል ኢንፍሪሜሪ አማካሪ እንደ ሆኑት ኬን ሂተን ላሉ ሳይንቲስቶች ሥራ ምስጋና ይግባውና አሁን ብዙ እናውቃለን።

በአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ መገባደጃ ላይ ኪተን እና ባልደረቦቻቸው የምሥራቅ ብሪስቶል ነዋሪዎችን ላይ የዳሰሳ ጥናት አድርገዋል። ምን ያህል ጊዜ ይጸዳዳሉ? ሲሉም ጠይቀዋል።

የአንጀት እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ልዩነት እንዳለ ውጤቶቹ አሳይተዋል።

ምንም እንኳን በጣም የተለመደው በቀን አንድ ጊዜ ቢሆንም፤ 40 በመቶ ወንዶች እና 33 በመቶ ሴቶች ብቻ ይህንን ተግባር ተከትለዋል።

አንዳንዶቹ በሳምንት ከአንድ በላይ ጊዜ ተጸዳድተዋል። ሌሎች ደግሞ በቀን ሦስት ጊዜ ይጸዳዳሉ።

በአጠቃላይ ጥናቱ "በተለምዶ መደበኛው የአንጀት ተግባር ከግማሽ በታች በሆነ ሕዝብ ይከሰታል። በዚህ ውስጥ በተለይ ወጣት ሴቶች በጣም የተጎዱ ናቸው" ሲል ጥናቱ ደምድሟል።

ሂተን ለዓይነ ምድር ሳይንስ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ይህ ብቻ አልነበረም።

የዓይነ ምድር ቅርፅ ሐኪሞች የምግብ መፈጨት ችግርን ለይተው እንዲያውቁ ለመርዳት በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል። ይህም የተለያዩ የዓይነ ምድር ጠቃሚ መግለጫዎችን ያሳያል።

ቶሎ ቶሎ መጸዳዳት በመልካም ጤንነት ላይ መሆንዎን ያመለክታል

የፎቶው ባለመብት, Emmanuel Lafont/ BBC

"የጎልዲሎክስ/የጎልድኢላፕስ" ዞን

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

የዩኬ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት እና ሌሎች የጤና አካላት በቀን ሦስት ጊዜ እና በሳምንት ሦስት ጊዜ መጸዳዳት እንደ መደበኛ ይቆጠራል ይላሉ።

መደበኛ እና ጤናማ ግን አንድ ዓይነት አይደሉም። የሳይንስ ሊቃውንት ምን ያህል ጊዜ እንጸዳዳለን የሚለውን እንቆቅልሽ ቢፈቱም፤ ለምን ያህል ጊዜ መጸዳዳት አለብን ለሚለው ጥያቄ ግን ምንም ምላሽ አይሰጥም።

ተመራማሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የአንጀት እንቅስቃሴ የአንድ ሰውን ጤንነት አመልካች እንደሆነ እየተመለከቱ ነው።

ለምሳሌ በ2023 የተደረገ ጥናት በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የ14,573 ጎልማሶችን የአንጀት ሁኔታን መርምሯል።

በጣም ተደጋጋሚው የአንጀት ልማድ በሳምንት ሰባት ጊዜ ነበር (50.7 በመቶ ሰዎች) እና በጣም የተለመደው የዓይነ ምድር ዓይነት "እንደ ቋሊማ ወይም እባብ ለስላሳ የሆነ" ነበር።

ተመራማሪዎች በዓይነ ምድር ድግግሞሽ እና በሞት መካከል ምን ዓይነት ግንኙነት እንዳለ ለማየት ተሳታፊዎችን ከአምስት ዓመታት በላይ ተከታትለዋል።

በሳምንት ሰባት ጊዜ መደበኛ ዓይነ ምድር ከሚጸዳዱ ሰዎች ይልቅ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የመሞት ዕድላቸው በ1.78 እጥፍ የሚበልጠው አራት ለስላሳ ዓይነ ምድር የሚጸዳዱ ሰዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

አልፎ አልፎ የሚጸዳዱ ደግሞ 2.42 (በካንሰር) እና 2.27 (በልብ እና የደም ቧንቧ በሽታዎች) እጥፍ የመሞት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው።

በሲያትል በሚገኘው የባዮሎጂ ተቋም የማይክሮባዮሎጂስት የሆነው ሺን ጊብስ የተመለከተው ደግሞ ዓይነ ምድር ምን ያህል መሆን አለበት የሚለውን ጥያቄ ነው።

በ2024 ጊብስ 1400 ጤናማ ጎልማሶችን በመጸዳጃ ቤት ልማዳቸውን መሠረት በአራት ቡድን በመከፋፈል አጥንቷል።

የሆድ ድርቀት (በሳምንት ከአንድ - ሁለት)፣ ዝቅተኛ (በሳምንት ከሦስት - ስድስት)፣ ከፍተኛ-መደበኛ (በቀን ከአንድ - ሦስት) እና ተቅማጥ በሚል ከፋፍሏቸዋል።

ከዚያም በመጸዳዳት ብዛት እና በአንድ ሰው የአንጀት ማይክሮባዮም ሁኔታ መካከል ግንኙነት ስለመኖሩ ለማየት ሞክለዋል።

በቀን ከአንድ እስከ ሦስት ጊዜ የሚጸዳዱ ሰዎች በአንጀታቸው ውስጥ የሚኖሩት 'ጠቃሚ' ባክቴሪያዎች ብዛት ወደ መጸዳጃ ቤት ብዙም ከማይሄዱት የበለጠ እንደሆነ አረጋግጧል።

በሌላ በኩል ደግሞ በሳምንት ከሦስት ጊዜ ላነሰ ጊዜ የሚጸዳዱ ሰዎች ቀደም ሲል እንደ ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ እና አልዛይመርስ በመሳሰሉት በሽታዎች ምከንያት ደማቸው ውስጥ የመበከል ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

"በጎልድሎክስ [ከፍተኛ ምድብ] ውስጥ ፋቲ አሲድ የተባሉ ኬሚካሎችን የሚያመርቱ ጥብቅ አናኢሮቢክ ማይክሮቦች ሲጨመሩ አይተናል" ሲል ጊብስ ይናገራል።

ከእነዚህ ፋቲ አሲድ (ኤስኤፍኤዎች) አንዱ የሆነው ቡቲሬት በሰውነት ውስጥ ያለውን ህመም እንደሚቀንስ ይታወቃል።

ይህ በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ሥር የሰደደ እብጠት እንደ የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታ፣ዓይነት ሁለት የስኳር በሽታ እና እንደ አልዛይመርስ ካሉ በሽታዎች በስተጀርባ ያለ መንስኤ እንደሆነ ይታሰባል።

"ከፍተኛ የቡቲሬት መጠን መኖር በደምዎ ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን በተሻለ ሁኔታ እንዲቆጣጠሩ ያስችልዎታል። ስለዚህ የተሻለ የኢንሱሊን ስሜት ይኖራችኋል" ሲል ጊብስ ይናገራል።

"ቡቲሬት በአንጀት ውስጥ ካሉ ህዋሶች ጋር ይተሳሰራል። ይህም የጥጋብ ስሜት እንዲሰማዎት የሚያደርጉ ሆርሞኖችን እንዲያመነጩ ያነሳሳቸዋል" ብሏል።

የሆድ ድርቀት ያጋጠማቸው ሰዎች በደማቸው ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ጎጂ መርዛማ ንጥረ ነገር እንዳላቸው ይታመናል።

ይህም የሚሆነው አንድ ሰው ብዙ ጊዜ በአግባቡ ካልተጸዳዳ ዓይነ ምድሩ ለረጅም ጊዜ በአንጀቱ ውስጥ ይጣበቃል። ይህም በአንጀት ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎች ሁሉንም ፋይበር እንዲበሉ ያደርጋል።

ችግሩ ግን ሁሉም ፋይበር ካለቀ በኋላ ባክቴሪያዎቹ በምትኩ ፕሮቲኖችን ማምረት ይጀምራሉ።

ይህ ደግሞ በደም ውስጥ ጎጂ የሆኑ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያስገባል። እነዚህ መርዞች ኩላሊትን እና ልብን ጨምሮ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ይታወቃል።

አንደኛው ፌኒላሴቲልግሉታሚን በመባል የሚታወቀው ሲሆን፣ ለልብ እና የደም ሥር (ለካርዲዮቫስኩላር) በሽታዎችን የሚያጋልጥ ነው።

"በደም ዝውውር ውስጥ ሥር የሰደደ ከፍተኛ የሆነ የዚህ ሜታቦላይት መጠን ካለ ኤተሮስክሌሮሲስ የተባለውን የደም ቧንቧ ማጠንከሪያ በመልቀቅ የልብ እና የደም ሕክምና ሥርዓትን ሊጎዳ ይችላል" ሲል ጊብሰን ይገልጻል።

ምንም እንኳን በቀን ከሦስት እስከ በሳምንት ሦስት ጊዜ መጸዳዳት ጤናማ እንደሆነ ጊቦንስ ቢገልጽም። ጥናቱ እንደሚያሳየው ግን ዝቅተኛ መደበኛ የዓይነ መድር ምድብ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ደም ውስጥ ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች መጨመር ታይቷል።

"በእርግጠኝት ለመናገር በጣም ከባድ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ወደፊት መታመማቸውን ለማወቅ መረጃ የለንም። ነገር ግን በተመለከትነው መረጃ መሠረት በየቀኑ ከሁለት ጊዜ እስከ በሁለት ቀን አንዴ መጸዳዳት ጤናማ ለመሆን የተሻለ ዕድል ሊሆን ይችላል" ብሏል።

የአንጀትዎ ጤና ከሚለኩ መንገዶች አንዱ ምግብ በምግብ መፍጫ ሥርዓትዎ ውስጥ ለመጓዝ የሚፈጅበት ጊዜ ነው።

ይህም የአንጀት የጉዞ ጊዜ በመባል ይታወቃል። እንደ ጣፋጭ በቆሎ ያሉ ምግቦችን በመመገብ እና ለመውጣት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድበት በቀላሉ በቤት ውስጥ ማወቅ ይችላሉ። በጥቅሉ ሲታይ የአንድ ሰው የአንጀት ጉዞ ጊዜ በረዘመ ቁጥር ዓይነ ምድሩ እየቀነሰ ይሄዳል። የሆድ ድርቀት የመጋለጥ ዕድሉም ይጨምራል።

በአውሮፓውያኑ 2020 የለንደን የኪንግ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ለ863 ሰዎች የአንጀት የጉዞ ጊዜያቸውን ለመለካት ቀላል ኬክ (መፍን) በመስጠት አጥንተዋል።

ይህ የፕሪዲክት1 ጥናት አካል ነበር። በጄኔቲክስ፤ በአንጀት ማይክሮባዮም እና በሌሎች ምክንያቶች የሚታዩ የግለሰብ ልዩነቶችን እና እንዴት የተለያዩ ምግቦች በሰውነት ውስጥ የደም ስኳር እና የስብ መጠን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ለመረዳት የተደረገ ምርምር ነው።

የተረዳነው ነገር ቢኖር ረዘም ያለ የጉዞ ጊዜ የነበራቸው ሰዎች የበለጠ 'መጥፎ' አንጀት ባክቴሪያ እንዲኖራቸው ይሆናል።

"እነዚህም ከዚህ ቀደም ከከፋ የልብ እና ከሜታቦሊዝም ጤና ጋር የተያያዙ ባክቴሪያዎች ናቸው" ያሉት በለንደን የኪንግ ኮሌጅ የማይክሮባዮሎጂ ሳይንቲስት ኤሚሊ ሊሚንግ ናቸው።

ይህ ግኝት በጣም ጎልቶ የታየው 58 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ ጊዜ ላላቸው እና በሳምንት ከሦስት ጊዜ ላነሰ ጊዜ የመጸዳዳት ዝንባሌ ላላቸው ሰዎች ነው።

ልክ እንደ ጊብስ ሁሉ ሊሚንግም ዓይነ ምድር በአንጀት ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ውስጥ ተህዋሲያን አዲስ ምግብ እያገኙ እንዳልሆነ ጥርጣሬ አላቸው።

ስለዚህ ፋይበር እና ካርቦሃይድሬትን ከመብላት ፕሮቲኖችን ወደ መብላት ይዞራሉ። ይህ ለጤና ጎጂ የሆኑ ተረፈ ምርቶችን ይፈጥራል።

ባለሙያዎች ከተጸዳዱ በኋላ መለስ ብሎ ዐይነ ምድርዎን መመልከት እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ

የፎቶው ባለመብት, Emmanuel Lafont/ BBC

ሆኖም ሁሉም ነገር ተያያዥ ላይሆን ይችላል። የጊቦን ጥናት የጤና ስጋት የሌላቸውን ጎልማሶችን ብቻ በመምረጥ ቢከናወንም ቀደም ሲል ጤነኛ ያልሆኑ ሰዎችም ተደጋጋሚ የአንጀት እንቅስቃሴ ሊቀንስባቸው ይችላል።

የሊሚንግ ጥናት እንዳመለከተው አጭር የአንጀት የጉዞ ጊዜ ያላቸው ሰዎች አነስተኛ ስብ አላቸው።

ይህም በሆድ ውስጥ እና በሆድ ውስጥ ያሉ የአካል ክፍሎችን የሚሸፍን የስብ ዓይነት ሲሆን፣ ስቡ አደገኛ ነው። ምክንያቱም የልብ ሕመም፣ የስኳር በሽታ እና አንዳንድ የካንሰር በሽታዎችን ጨምሮ ለብዙ የጤና ሁኔታዎች ያለን ተጋላጭነት ሊጨምር ይችላል።

በመጨረሻም አጭር የአንጀት የጉዞ ጊዜ ያላቸው ሰዎች ለምግብ ጤናማ ምላሽ ሰጥተዋል። ይህም 'ድኅረ-ምላሽ' በመባል ይታወቃል። ይህ ማለት ምግብ ከተመገቡ በኋላ በደም ውስጥ ያለው የስኳር እና የሊፕዲድ መጠን ዝቅተኛ መሆኑን እና ይህም የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታ ተጋላጭነታቸውን የሚቀንስ ነው።

ግኝቱ ሳይንቲስቶች ስለሆድ ድርቀት ከሚያውቁት እና ሥር ከሰደደ በሽታ ጋር ካለው ግንኙነት ጋር ይስማማል። አንድ ሰው ሥር የሰደደ የሆድ ድርቀት ካለበት እንደ አንጀት ካንሰር ላሉ በሽታዎች ከፍተኛ ተጋላጭነት ሊኖረው ይችላል።

"ነገር ግን ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ጋር ያለውን ግንኙነትም እናያለን። ለምሳሌ የፓርኪንሰን በሽታ ያለባቸው ሰዎች ምንም ዓይነት ምልክት ከማሳየታቸው በፊት እስከ 20 ዓመታት ድረስ የሆድ ድርቀት ሊኖራቸው ይችላል" ሲል ሊሚንግ ይናገራል።

ቬይሲ በበኩሉ በሚያዘግም የአንጀት የጉዞ ጊዜ እና በሐሞት ዕጢዎች መካከል ያለውን የሚታወቀውን ግንኙነት ይጠቁማል። በሐሞት ከረጢት ውስጥ የሚፈጠሩ ጠንካራ የሃሞት ክምችቶች ናቸው። "ይህም በአንጀት ውስጥ ችግር ይፈጥራል። ከካንሰር በፊት የሚከሰቱ ቁስሎች ሲሆኑ ወደ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።"

አትክልት እና ፍራፍሬ መመገብ ቶሎ ቶሎ ለመጸዳዳት ያግዛል

የፎቶው ባለመብት, Emmanuel Lafont/ BBC

ዓይነ ምድርዎ ስለእርስዎ ምን ይላል?

ሊሚንግ እንደሚለው በሳምንት ውስጥ ከሚደረጉ የአንጀት እንቅስቃሴዎች ብዛት ይልቅ (ይህ ከሰው ሰው ይለያያል) ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ዋናው ነገር የአንጀት ልምዶች ላይ ያልተገለጹ ለውጦች ላይ ነው።

ለእርስዎ የተለመደ የሆነውን የመጸዳዳት ልምድ ለማወቅ የሚጸዳዱበትን ሁኔታ መከታተል ጥሩ ሃሳብ እንደሆነ ትመክራለች።

"ሁላችንም ዓይነ ምድራችንን መመልከት አለብን። ምክንያቱም ይህ እንደ ነጻ የአንጀት ጤና ምርመራ ይቆጠራል። ምን ያህል ጊዜ እንደሚጸዳዱ ብቻ ሳይሆን ቀለሙን እና ቅርጹንም ጭምር ማየት ነው።

"መመልከት ያለብዎት ሦስተኛውን እና 4ተኛውን ዓይነት (በብሪስቶል የዓይነ ምድር ቅፅ መሠረት ማለት ነው) ሲሆን፤ ይህም ስንጥቅ ያለበት ወይም ለስላሳ መሆኑን ማየት ነው" ብሏል ሊሚንግ።

ቀለምን በተመለከተ ጥቁር ወይም ቀይ ቀለም ካዩ የደም መኖርን የሚያመለክት ነው።

ምንም እንኳን ጉዳት የሌለው ሊሆን ቢችልም፣ ይህ የኮሎሬክታል ካንሰር ምልክት ሊሆን ስለሚችል በተቻለ ፍጥነት ሐኪም ዘንድ መሄድ አስፈላጊ ነው።

አዘውትሮ ተቅማጥ ካለብዎት ወይም በጣም በድንገት ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ ካለብዎት ወይም ከተመገቡ በኋላ ብዙ ቁርጠት፣ የሆድ መነፋት እና ጋዝ ካጋጠመዎት ሐኪምዎን ማነጋገር አለብዎት።

በመጨረሻም "መደበኛ" እንዲሆን ከፈለጉ ደግሞ ማድረግ የሚችሏቸው ሦስት ቀላል ነገሮች አሉ።

"በእኛ ጥናት መሠረት በጎልድሎክስ ምድብ የሚኖሩ ሰዎች ብዙ አትክልት እና ፍራፍሬ የሚመሀገቡ፣ በርካት ያለ ውሃ የሚጠጡ እና የእንቅስቃሴ የሚያደርጉ ነበሩ" ይላል ጊብሰን።