በኢንዶኔዥያ አንድ የታክሲ አሽከርካሪ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሳ

ተቃዋሚዎች በጃካርታ ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውጭ ያሉ አጥሮችን ሲያቃጥሉ

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, ተቃዋሚዎች በጃካርታ ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውጭ ያሉ አጥሮችን አቃጥለዋል።

በኢንዶኔዥያ ከታክሲ አሽከርካሪ ሞት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቷ የተቀሰቀሰ ተቃውሞን ተከትሎ ሦስት ሰዎች ተገደሉ።

የ21 ዓመቱ አሽከርካሪ አፋን ኩርኒያዋን በመዲናዋ ጃካርታ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እና የፖለቲከኞችን ከፍተኛ ወጪ በመቃወም እየተካሄደ ያለ ተቃውሞ በጀመረበት ወቅት ነበር በፖሊስ መኪና ተገጭቶ የተገደለው።

በመላ አገሪቱ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ የተኮሱ ሲሆን በጃካርታ እና ሱራቤይ ከተሞችም ተቃዋሚዎች ከጸጥታ አካላት ጋር ተጋጭተዋል።

የአገሪቷ ፕሬዚደንት ፕራቦው ሱቢያንቶ ወደ ኩርኒዋን ቤተሰብ በማምራት ሀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን በአገሪቷ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደ ከባድ ፈተና ታይቷል።

የአፋን ኩርኒዋን የቀብር ሥነ ሥርዓት የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቹ በተገኙበት አርብ ዕለት የተፈፀመ ሲሆን የጃካርታ ፖሊስ አዛዥ አሲፕ ኢዲ ሱህሪ እንዲሁም ፖለቲከኛው ሬክ ዲያህ ፒታሎካ እና የጃካርታ ገዥ አኒስ ባስዊዳን በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የጃካርታ ገዥው የአሽከርካሪው ሞት ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ ቃል የገቡ ሲሆን የአገሪቷ መረጋጋት ለመጠበቅ አሽከርካሪዎች ተቃውሟቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የፖሊስ አዛዡም በተደጋጋሚ ይቅርታ ጠይቀዋል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እየተፈፀመ ባለበት ወቅትም ተቃዋሚዎች በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ለአሽከርካሪው ሞት ፍትህ ጠይቀዋል።

ፕሬዚደንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶም የአሽከርካሪውን ቤተሰቦች ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት ያልተገባ እርምጃ "መደንገጣቸውንና መበሳጨታቸውን" ተናግረዋል።

የጃካርታ ገዥ ፕራሞኖ አኑንግም የኩሪኒያዋን ቤተሰብ ጋር በመሄድ ሀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን ለቀብር ሥነ ሥርዓቱ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

 ጓደኛው በ21 ዓመቱ ኩርኒያዋን መቃብር አጠገብ ቁጭ ብሎ ሲጸልይ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ጓደኛው በ21 ዓመቱ ኩርኒያዋን መቃብር አጠገብ ቁጭ ብሎ ሲጸልይ ታይቷል።
Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

አርብ ዕለት ሰባት አባላት ያሉት ተንቀሳቃሽ የጸጥታ አካላት የፖሊስን ሙያዊ ሥነ ምግባር ጥሰው ተገኝተዋል። ይህም በአገሪቷ ውስጥ ውጥረት የፈጠረ ሲሆን ተቃዋሚዎችም የፖሊስ ተሽከርካሪዎች እንዳያልፉ መንገድ በመዝጋት እና ድንጋይ በመወርወር ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ከዚያም የፕርታሚና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመቀላቀላቸው ተቃውሞው ተስፋፍቷል።

ቀደም ብሎም ተቃዋሚዎች በእግረኞች መሻገሪያ ድልድይ ላይ " እነዚህ የተረገሙ ፖሊሶች ይታሰሩ!" የሚል ጽሑፍ የሰፈረበት ባነር አስቀምጠው ነበር።

ተቃውሞው በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠለ ሲሆን ምንም እንኳን ዝናብ ቢዘንብም በፖሊስ ግቢ ውስጥ ተቀጣጣይ ርችት እና ተቀጣጣይ ፈሳሽ የያዙ ኮዳዎችን ሲወረውሩ እንደነበር የኢንዶኔዥያ የቢቢሲ አጋር የሆነው ኮምፓስ ዘግቧል።

የመንግሥት የዜና ወኪል እንደዘገበውም በርካታ ተሽከርካሪዎችም በእሳት ተቃጥለዋል።

በድሮን የተቀረጹ ምስሎችም በኩርኒያዋን የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ አሽከርካሪዎች የቀጣሪያቸው ጎጂክ መለያ የሆነውን አረንጓዴ ልብስ ለብሰው መገኘታቸውን አሳይተዋል።

ደርጅቱ ጎጂክ የአሽከርካሪውን ሞት ተከትሎ ባወጣው መግለጫም "ከእያንዳንዱ አረንጓዴ ጃኬት ጀርባ ቤተሰብ ፣ ጸሎት እና ትግል አለ" ብሏል።

"አፋን ኩርኒያዋን የዚህ ጉዞ አካል ነበር እና መለየቱ በሁላችንም ዘንድ መራር ሀዘን ጥሏል" ሲልም የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። ድርጅቱ ጨምሮም ለሟች ሰራተኛው ቤተሰብ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

በዚህ ሳምንት በተካሄደው ተቃውሞ ወቅት ተቃዋሚዎች የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ከእነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የሕግ አውጪዎች አዲስ ወርሃዊ ደመወዝ ይገኝበታል።

ለሕግ አውጪዎች 50 ሚሊዮን ሩፒያህ ( ሦስት ሺህ ዶላር) እንዲሆን የታቀደ ሲሆን ይህን በአገሪቷ መዲና ጃካርታ ዝቅተኛ ወርሃዊ የደመወዝ ወለል አስር እጥፍ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ተቃዋሚዎቹ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ከፍ እንዲል፣ ግብር እንዲቀንስ እና በሙስና ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል።