ቶተንሃም ከሊቨርፑል - ማን ያሸንፋል? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ወደ ለንደን አቅንቶ ቶተንሃምን ይገጥማል።
"አስደናቂ ጨዋታ ይሆናል" ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ተናግሯል።
"በቶተንሃም አጨዋወት እና በሊቨርፑል መልሶ ማጥቃት ምክንያት አስገራሚ ጨዋታ ይሆናል" ብሏል።
ይህን ጨዋታ ጨምሮ ሱተን በ17ኛው ሳምንት እንዲካሄዱ መርሃ ግብር የተያዘላቸውን ጨዋታዎች በሙሉ እንደሚከተለው ገምቷል።
ቅዳሜ

አስቶን ቪላ ከማንቸስተር ሲቲ
አስቶን ቪላዎች ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበሩበት ጊዜ በ10 ነጥብ ዝቅ ብለው ይገኛሉ።
ሰባተኛ ደረጃ ላይ ከመቀመጣቸውም በላይ በብዛት ያሸነፉት በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኙ ክለቦችን ነው።
ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ከማንቸስተር ሲቲ አንጻር አነስተኛ ነጥብ የሰበሰቡት ሌስተር እና ሳውዝአምፕተን ብቻ ናቸው።
ሲቲ በየሳምንቱ ወደ ጥሩ አቋሙ የሚመለስበትን ውጤት እንደሚያስመዘግብ ቢግምትም ይህ እስካሁን አልሆነም።
በዚህ ጨዋታ ወደ ድል የሚመለሱ ባይመስሉም ቪላም የማሸነፍ የሚችል አይመስልም።
ግምት፡ 1 - 1
ውጤት፡ 2 - 1
ብሬንትፎርድ ከኖቲንግሃም ፎረስት
ብሬንትፎርድን በሜዳው አለመደገፍ ከባድ ሲሆን ፎረስት ደግሞ ከሜዳው ውጭ ጠንካራ ነው።
ፎረስት ከሜዳ ውጭ በተመዘገበ ውጤት ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ከዚህ ጨዋታም አንድ ነገር የሚያገኙ ይመስላል።
ብሬንትፎርድ በሳምንቱ አጋማሽ በካራባኦ ካፕ ከኒውካስል ጋር ተጫውቶ መሸነፉ በዚህ ጨዋታ ላይ ተጽዕኖ ይኖረው እንደሆነ እንመለከታለን።
ጨዋታው በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስላል።
ግምት፡ 1 - 1
ውጤት፡ 0 - 2
ኢፕስዊች ከኒውካስል
የሊጉን ጥንካሩ በሚያሳይ መልኩ ክለቦች በጥቂት ነጥቦች ብቻ ተለያይተዋል።
አራተኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው ፎረስት እና በ13ኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ መካል ያለው ልዩነት ስድስት ነጥብ ብቻ ነው።
ኒውካስል 12ኛ ደረጃ ላይ ቢቀመጥም ካለው ስብስብ አንጻር ተገቢው ቦታ አይደለም።
በገና ሰሞን መርሃ ግብር ሁለት ጨዋታዎችን የሚያሽንፍ ወደ ላይ ከፍ ማለቱ እሙን ነው።
ኒውካስል ይህንን ማሳካት ይችላል። ኢፕስዊች በሜዳው የሚያሸንፍበት የመጀመሪያው ጨዋታ አይሆንም።
ግምት፡ 1 - 2
ውጤት፡ 0 - 4
ዌስት ሃም ከብራይተን
ይህ ለመገመት ከባድ ሆነ ጨዋታ ነው።
ዌስትሃም ዘንድሮ እስካሁን አሳማኝ አልሆነም። ብቸኛው ጥሩ የሚንቀሳቀሰው ተጫዋቸው ጃሮድ ቦዌን ብቻ ነው።
ብራይተኖችም መጥፎ የውድድር ዓመት እያሳለፉ ሲሆን ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።
በመኪና አደጋ ከሜዳ በሚርቀው ማይክል አንቶንዮ ምትክ በክረምቱ የፈረመው ኒክላስ ፉክሩግ ዕድል ይመቻችለታል።
ብራይትን ባለፈው ሳምንት በክሪስታል ፓላስ ቢሸነፍም የሚያንሰራራበት ዕድል አለው።
ግምት፡ 1 - 2
ውጤት፡ 1 - 1

ክሪስታል ፓላስ ከአርሰናል
ሁለቱ ቡድኖች ረቡዕ ምሽት በካራባኦ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ተገናኝተው ነበር።
በጨዋታው መድፈኞቹ በጠባብ ውጤት አሸናፊ የሆኑ ሲሆን ይህን ጨዋታም ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ይሆናል።
ጨዋታው ለመድፈኞቹ ቀላል አይሆንም።
ሆኖም አርሰናል ከጨዋታው የሚፈልገውን ሦስት ነጥብ የሚያሳካበተን መንገድ አያጣም።
ግምት፡ 0 - 1
ውጤት፡ 1 - 5
እሑድ
ኤቨርተን ከቼልሲ
የኤቨርተን የባለቤትነት ጉዳይ አሁን እልባት አግኝቷል። ቀጣዩ የአሰልጣኙ ሾን ዳይሽ ጉዳይ ነው።
ቡድኑ በሊጉ እንዲጥል አሰልጣኙ ቢቆዩ የተሻለ ነው።
ቡድኑ በጠንካራ አቋም ላይ ባይገኝም ከአርሰናል ጋር እንዳደረገው ውጤት ማስጠበቅ የሚችል ነው።
በዚህ ጨዋታ ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ሦስት ነጥብ ያሳካል።
ግምት፡ 1 - 2
ፉልሃም ከሳውዝአምፕተን
ፉልሃም ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል ጋር የተመጣጠነ ብቻ ሳይሆን በተወሰነ ደረጃም ጥልቀት ያለው ቡድን መሆኑን አሳይቷል።
በዚህ ጨዋታ አዲስ አሰልጣኝ ያልቀጠረው ሳውዝሃምፕተን የሚያሸንፍበት ዕድል ያለው አይመስልም።
የቡድኑ ተጫዋቾች በራስ መተማመን ከመውረዱም በላይ በሊቨርፑል ተሸንፈው ከካራባኦ ዋንጫ ውጭ ሆነዋል።
አዲስ አስልጣኝ ሲሾሙ ምን አይነት አጨዋወት እንደሚመርጥ ማየት ያጓጓል።
ግምት፡ 2 - 0
ሌስተር ከ ዎልቭስ
ዎልቭሶች ቮቶር ፔሬራን ቢሾሙም አጥቂያቸው ማቲየስ ኩኛ ከዚህ ጨዋታ ውች ሆኗል።
ሌስተሮች በቫን ሊስተሮይ ስር መነሳሳጥ ቢያሳዩም አሁንም በጃሚ ቫርዲ ላይ ጥገኛ ናቸው።
ፔሬራ ለመቅረፍ የሚቸገሩበት አይነት የተከላካይ መስመር ክፍተት ዎልቭሶች ዘንድ አለ።
ግምት፡ 1 - 1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከበርንመዝ
ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት ሲቲን ቢያሸንፍም ከበርንመዝ ሰባት ደረጃ ርቀው 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ቡድኑ ብዙ መሥራት ያለበት ሲሆን ማርከስ ረሽፎርድ ለዚህ ዝግጁ አይመስልም።
አሰልጣኝ ሩበን ኦሞሪም አዲስ አሰራር ለመዝረጋት ጥረት እያደረጉ ይገኛል።
በርንመዝ ጥሩ እየተጓዘ ሲሆን በርካታ ዕድሎችንም እየፈጠረ ነው።
አማድ ዲያሎ ከአዲሱ አሰልጣኝ መምጣት በኋላ በድንቅ አቋም ላይ ቢገኝም ቡድኑ በበርንመዝ ይሸነፋል።
ግምት፡ 1 - 2

ቶተንሃም ከሊቨርፑል
ስፐርስ በውድድር ዓመቱ ከፍ እና ዝቅ እያለ ቀጥሏል።
ፉክክር የሚኖረው ጨዋታ በመሆኑ ቶተንሃሞች የሚመርጡት ጨዋታ ቢሆንም ሊቨርፑሎችም እጃቸውን አጣጥፈው አይቀመጡም።
ቶተንሃሞች ሞሐመድ ሳላህን ለማቆም የሚያደርጉት ሙከራ ትኩረት ቢስብም የሚሳካ አይመስልም።
ብዙዎች ሊቨርፑል ባለፈው ሳምንትከፉልሃም አቻ መለያየቱ መጥፎ ውጤት ነው ቢሉም በ10 ተጫዋች አንድ ነጥብ ማግኘታቸው ትልቅ ነገር ነው።
ተጫዋች ወጥቶባቸውም ተጨማሪ ተጫዋች ያለባቸው ይመስል ነበር።
ግምት፡ 2 - 3












