ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) "የሚነግራችሁን በጭፍን አትመኑ" ሲል የጉግል ኃላፊ አስጠነቀቀ

የጉግል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳንዳር ፒቻይ
የምስሉ መግለጫ, የጉግል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳንዳር ፒቻይ

ሰዎች ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሚነግራቸውን ሁሉ "በጭፍን ማመን" የለባቸውም ሲሉ የጉግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገረ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳንዳር ፒቻይ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የኤአይ ሞዴሎች "ለስህተት የተጋለጡ" ናቸው በማለት ሰዎች ከሌሎች መሳሪያዎች ጋር እንዲጠቀሟቸው አሳስበዋል።

ፒቻይ በኤአይ ቴክኖሎጂ ላይ ብቻ ከመተማመን ይልቅ የበለፀገ የመረጃ ሥነ ምኅዳር የመኖርን አስፈላጊነት አጉልተው አቅርበዋል።

"ለዚህም ነው ሰዎች ጎግልን የሚጠቀሙት እና ትክክለኛ መረጃን ለማቅረብ የበለጠ ቅርብ የሆኑ ሌሎች ምርቶች አሉን።"

የኤአይ መሳሪያዎች "አንድ ነገር ለመፃፍ ከፈለጉ" ጠቃሚ ቢሆኑም፣ ሰዎች "እነዚህን መሳሪያዎች ጥሩ በሆኑት ጉዳይ ላይ ብቻ መጠቀምን መማር እንዲሁም የሚናገሩትን ሁሉ በጭፍን አለማመን አለባቸው" ብለዋል።

ፒቻይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "በተቻለ መጠን ትክክለኛ መረጃ እንዲሰጠን በምንሠራው ሥራ እንኮራለን፤ ነገር ግን አሁን ያለው ዘመናዊ የኤአይ ቴክኖሎጂ ለአንዳንድ ስህተቶች የተጋለጠ ነው።"

ስልክ የያዘ እጅ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

'አዲስ ምዕራፍ'

የቴክኖሎጂው ዓለም የቻትጂፒቲ የገበያ ድርሻን ይቀናቀናል የተባለው ጀሚኒ 3.0 የተባለ አዲስ ኤአይ ሞዴል ይፋ እስኪሆን እየጠበቀ ነው።

ካለፈው ዓመት ከግንቦት ወር ጀምሮ ጎግል አዲስ "ኤአይ ሞድ" ማስተዋወቅ ጀምሯል፤ ይህም ጄሚኒ ቻትቦትን በማዋሃድ ተጠቃሚዎች ከባለሙያዎች ጋር የመነጋገር ያህል ዕድል እንዲሰጣቸው የሚያደርግ ነው።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

በወቅቱ ፒቻይ የጄሚኒን ከጉግል መፈለጊያ ጋር ማቀናጀት "የኤአይ መድረክ ለውጥ አዲስ ምዕራፍ" ምልክት እንደሆነ ተናግረዋል።

እርምጃው የጉግልን መፈለጊያ የበላይነት አደጋ ላይ ከጣሉት እንደ ቻትጂፒቲ ካሉ የኤአይአይ አገልግሎቶች ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል የሚያስችለው የቴክኖሎጂው ግዙፉ አካል ነው።

የኃላፊው አስተያየቶች የቢቢሲ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የኤአይ ቻትቦቶች የዜና ዘገባዎችን ስህተት በሆነ መንገድ ጠቅለል አድርገው ያቀርባሉ ሲል ያቀረበውን የምርመራ ዘገባ የሚደግፍ ነው።

የኦፕንኤአይ ቻትጂፒቲ፣ የማይክሮሶፍት ኮፓይለት፣ የጎግል ጄሚኒ፣እና ፐርፕሌክሲቲ ኤአይ ሁሉም ከቢቢሲ ድረ ገጽ ላይ የተወሰዱ ዘገባዎች ተሰጥቷቸው ጥያቄዎችን ጠይቀዋል።

በጥናቱ የኤአይ መልሶች "ጉልህ ስህተቶች " እንዳለባቸው አረጋግጧል።

ፒቻይ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቴክኖሎጂ ፍጥነት እያደገ ቢሆንም ጉዳቶችን ለመከላከል ማቃለያዎች የሚሠሩበት ፍጥነት መካከል መጠነኛ ልዩነት እንዳለ ተናግሯል።

ለአልፋቤት ልዩነቶቹን መቆጣጠር ማለት "ደፋር እና በተመሳሳይ ጊዜ ተጠያቂ መሆን" ማለት ነው ብለዋል።

"ስለዚህ በአሁኑ ወቅት በፍጥነት እየተጓዝን ነው። ተጠቃሚዎቻችን የሚጠይቁትም ይህንን ይመስለኛል" ብሏል።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በኤአይ ላይ ፈሰስ ከሚደረገው መዋዕለ ነዋይ ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ በኤአይ ደኅንነት ላይ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ጨምሯል ሲሉ ፒቻይ ተናግሯል።

"ለምሳሌ እኛ ምሥል በኤአይ የተሠራ መሆኑን ለማወቅ የሚያስችል ለሁሉም ክፍት የሆነ ቴክኖሎጂ አለን" ብለዋል።

አሁን በጉግል ባለቤትነት የተያዘው ዲፕማይንድኤአይ (DeepMind AI) "አምባገነንነት" ሊፈጥር ይችላል የሚለውን ስጋቱን የቴክኖሎጂ ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ ለኦፕንኤአይ መሥራቾች መናገሩን በተመለከተ የተጠየቀው ፒቻይ "ማንም ኩባንያ እንደ ኤአይ ኃይለኛ ቴክኖሎጂ ሊኖረው አይገባም" ብለዋል።

ነገር ግን ዛሬ በኤአይ ላይ የሚሠሩ በርካታ ኩባንያዎች መኖራቸውንም ገልጿል።

"የአይአይ ቴክኖሎጂን እየገነባ ያለው አንድ ኩባንያ ብቻ ቢሆን እና ሁሉም ሰው ሊጠቀምበት ቢገባ ኖሮ እኔም ያሳስበኝ ነበር፤ ነገር ግን አሁን ከዚህ ሁኔታ በጣም ርቀናል" ብሏል።