የስፖርት ኮከቦች እና የንግድ ምልክቶቻቸው- ከቦልት እስከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የአትሌቲክሱ ዓለም ኮከብ እና ፈጣኑ ሰው ዩሴን ቦልት ከውድድር በፊት እና በኋላ የሚያሳየውን ታዋቂ የሆነውን ምልክት ለንግድ ምልክትነት ለመጠቀም ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል።
እሱ ብቻ ግን አይደለም የሚለይበትን ምልክት የሚያሳይ ኮከብ።
ዩሴን ቦልት
የአሜሪካ የፓተንት እና የንግድ ምልክት ቢሮ እንደገለጸው ቦልት ታዋቂውን ምልክቱን በንግድ ምልክትነት ለማስመዝገብ ማመልከቻውን ነሐሴ 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ አስገብቷል።
መቀመጫቸውን ዋሽንግተን ያደረጉት የንግድ ምልክት ጠበቃው ጆሽ ገርበን “አንድ እጁ ታጥፎ ወደ ጭንቅላቱ ሲጠቆም ሌላኛው እጁ በተመሳሳይ አቅጣጫ ወደ ላይ ከፍ ብሎ እንደሚዘረጋ” ያሳያል ብለዋል።
ቦልት ይህን የሚያደርገው ዝነኛ የድል አድራጊነቱን የሚያሳየውን አርማ የንግድ ምልክት በማድረግ ልብሶችን እና የፋሽን ዕቃዎችን ለመሸጥ በማሰቡ ነው።
ሜጋን ራፒኖይ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ታዋቂዋ የአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሜጋን ራፒኖ ጎል ካስቆጠረች በኋላ ደስታዋን በምትገልጽበት የተለየ መንገድ ትታወቃለች።
ከአሜሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ እና የኦሎምፒክ ወርቅ አሸናፊ ለመሆን የበቃችው ሜጋን እጆቿን ዘርግታ በምታሳየው ፈገግታ ወይም እርካታ ትለያለች።
እአአ በ2019 በፊፋ ኮከብ ተጫዋች ለመሆን የበቃችው ተጫዋቿ ቀላል እና በአድናቂዎች የተወደደ የደስታ አገላለጽ ነው ያላት።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሞ ፋራህ
ሞ ፋራህ የበርካታ የኦሎምፒክ፣ የዓለም እና የአውሮፓ የረዥም ርቀት ሩጫዎች ሻምፒዮን ነው። ብዙዎችም "የእንግሊዝ የምንግዜም ታላቅ አትሌት" እያሉ ይጠሩታል።
ውድድሮችን ሲያሸንፍ "ሞቦት" በማሳየት በጣም ታዋቂ ነው።
የሁለቱን አጅቹን ጣቶች በማገናኘት የጭንቅላቱ አናት ላይ በማድረግ የስሙ መነሻ የሆነውን ‘M’ የእንግሊዘኛ ፊደል ይሠራል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ክርስቲያኖ ሮናልዶ
ታዋቂው ፖርቹጋላዊ የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት መንገድ አዘጋጅቷል።
ይሮጥና ይዘላል፣ አየር ላይ እያለ ይዞርና እጆቹን ወደ ጎን እየወረወረ “ሲ” እያለ ይጮሃል። “ሲ” በፖርቹጋል ቋንቋ አዎ እንደማለት ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሶን ሄንግ-ሚን
ደቡብ ኮሪያዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሶን ሄንግ-ሚን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፈው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ይጫወታል።
አጥቂው ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበት የራሱን ልዩ ምልክት አዘጋጅቷል።
አውራ እና ጠቋሚ ጣቶቹን በማገናኘት ያንን ቅጽበት ለመቅረጽ የሚረዳውን ካሜራን የሚወክል ቅርጽ ይሠራል።
ስለእነዚህ ምልክተቶች ምን ያስባሉ?
ቦልት ዝነኛ ምልክት ያለው ብቸኛው ሰው ባይሆንም በዓለም ዙሪያ በጣም ታዋቂው ነው ማለት ግን ይቻላል።
የንግድ ምልክት ማመልከቻው ከተሳካ ደግሞ ምናልባት የበለጠ ዕውቅና ያገኛል።












