የዝውውር ጭምጭምታዎች፡ ዳግላስ ሉዊዝ ወደ አርሰናል፤ ኔይማር ወደ አል-ሂላል?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ባየርን ሙኒክ እንግሊዛዊው አጥቂ ሃሪ ኬንን ለማስፈረም 100 ሚሊዮን ዩሮ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል ይላል የስካይ ስፖርትስ ዘግቧል።
100 ሚሊዮን ዩሮው ለተጫዋቹ ግዥ ለቶተንሃም የሚከፈለውና ተጨማሪ ሌሎች ክፍያዎችን ያካተተ ነው።
ነገር ግን ሙኒክና ቶተንሃም አሁንም በሃሪ ኬን ጉዳይ ከስምምነት ባለመድረሳቸው የ30 ዓመቱ አጥቂ በቶተንሃም ሊቆይ ይችላል።
የሰሜን ለንደን ተቀናቃኞቹ አርሰናል እና ቶተንሃም የአስተን ቪላው የ25 ዓመት ብራዚላዊ አማካይ ዳግላስ ሉዊዝ ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ይላል የፉትቦል ኢንሳይደር ፅሑፍ።
ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደሚለው ከሆነ አርሰናል የብሬንትፈርዱን ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራይ በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል።
የሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል-ሂላል የፓሪ ሳን ዠርማ ብራዚላዊ አጥቂ ኔይማር ጁኒየር ለማስፈረም እንደሚፈልግ ፉትመርካቶ አስነብቧል።
አል-ሂላል የ31 ዓመቱን ኔይማር ለማስፈረም በሚል ከአባቱ ጋር ለመገናኘት ዕቅድ መያዙ የተሰማ ሲሆን ተጫዋቹ ፒኤስጂን ከለቀቀ ለአንድ ዓመት በውሰት ወደ ባርሴሎናል ሊያቀና እንደሚችል ተዘግቧል።
ኤቨርተን የማንቸስተር ዩናይትዱን እንግሊዛዊ ተከላካይ ሃሪ ማጓዬር ወደ ጉዲሰን ፓርክ ማምጣት እንደሚፈልግ የዘገበው ሚረር ዩናይትድ ደግሞ ቤልጂየማዊውን አማካይ አማዱ ኦናና ሊወስድ እንደሚሻ ፅፏል።
እንደ ፈረንሳዩ አርኤምሲስፖርት ዘገባ ማንቸስተር ዩናይትድ የ23 ዓመቱ ፈረንሳዊ የመሃል ተከላካይ ጂን-ክሌይር ቶዲቦ ከኒስ በማስፈረም የማጓዬር መተኪያ ሊያደርገው አስቧል።
በተያያዘ ዩናይትድ የ25 ዓመቱን እንግሊዛዊ ተከላካይ አሮን ዋን-ቢሳካ ውል የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ለማራዘም እንዳቀደ ሜይል ፅፏል።
በጀርመኑ ባየርን ሙኒክ የሚፈለገው የ33 ዓመቱ እንግሊዛዊው ተከላካይ ካይል ዎከር ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ለመቆየት መወሱኑን የአትሌቲክ ዘገባ ያሳያል።
የስፔኑ ሪያል ሶሲዬዳድ የአርሰናሉን ስኮትላንዳዊ የግራ መስመር ተመላላሽ ኪየራን ቲየርኒ በውሰት ለአንድ ዓመት ሊወስደው ይሻል።
ባርሴሎና በ16 ዓመቱ ጀርመናዊ አማካይ ኖዋህ ዳርቪች መልቀቂያ ውል ላይ 1 ቢሊዮን ዩሮ እንዳሰፈረ ፉትቦል ትራንስፈርስ ገልጧል።
ይህ ማለት ተጫዋቹን ወደፊት ማስፈረም የሚፈልግ ክለብ 1 ቢሊዮን ዩሮ ውል ማፍረሻ መክፈል ይጠበቅበታል።
ኔዘርላንዳዊው አጥቂ ዋውት ቬግሆርስት በአንድ ዓመት ውል ከበርንሊ ወደ ዎልፍስበርግ ይሄዳል።












