ስፔን ከፈረንሳይ እና ኔዘርላንድ ከእንግሊዝ የአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግምቶች

ለአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ ማን ይደርስ ይሆን?

በጀርመን አስተናጋጅነት የሚካሄደው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጨዋታዎች ቀርተውታል።

ዛሬ እና ነገ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ትልቅ ግምት የተሰጠው የስፔን እና ፈረንሳይ እንዲሁም ኔዘርላንድ ከእንግሊዝ የሚያደርጉትን ጨዋታ ግምት የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን እንደሚከተለው ግምቱን አስቀምጧል።

ስፔን ከፈረንሳይ

ግማሽ ፍጻሜ ማክሰኞ ስፔን ከ ፈረንሳይ

ፈረንሳይ ከዚህ ቀደም እንደነበሯት ቡድኖች ሳቢ የሆነ ጨዋታ ማሳየት አልቻለችም።

የዊሊያም ሳሊባ እና ዳዮ አፓሜካኖ ጥምረት ተከላካይ መስመሩን ጠንካራ ከማድረጉም በላይ ግብ ጠባቂው ማይክ ማይግናንም በድንቅ አቋም ላይ ይገኛል።

ከፖርቹጋል ጋር በነበረው ጨዋታ የአጥቂ መስመራቸው ደካማ ነበር። ኡስማን ዴምቤሌ ተቀይሮ በመግባት የአጥቂ መስመሩን ቢያሻሽልም ክሊያን ምባፔ ነገሮች እንዳሰቡለት እየሄዱ አይደለም።

ስፔን ደግሞ በተቃራኒው የውድድሩ ምርጥ ቡድን መሆኗን አዘጋጇን ጀርመንን በማሸነፍ ጭምር እያሳየች ነው።

ጎሎችን በመጨረስ ረገድ ካላቸው መጠነኛ ክፍተት ውጭ በሁሉም የሜዳው ክፍሎች ውጤታማ መሆናቸውን እያሳዩ ነው።

በዚህ ጨዋታ ሮቢን ለ ኖርማድ እና ዳኒ ካርቫሃል በቅጣት እና ፔድሪ ደግሞ በጉዳት ከዚህ ጨዋታ ውጭ ናቸው።

ምክንያታዊ ከሆንኩኝ ላሚን ያማል፣ ኒኮ ዊሊያምስ፣ ሮድሪ እና ፋብያን ሩዊዝ እያሳዩ ካሉት ብቃት አንጻር ስፔን ጨዋታውን ታሸንፋለች። ስሜቴ ግን ፈረንሳይ ወደ ፍጻሜው እንደምታልፍ ይነግረኛል።

ግምት፡ 2 – 1

ኔዘርላንድስ ከእንግሊዝ

ረቡዕ ኔዘርላንድስ ከ እንግሊዝ

ኔዘርላንድስ ከእረፍት በፊት በተቆጠራበት ጎል በቱርክ 1 ለምንም ብትመራም ዉት ቬጎረስት ቅያሪ ብርቱካናማዎቹን ለድል አብቅቷል።

በተጫዋች ቅያሪ ላይ በድፍረት ከመወሰን አንጻር የአንግሊዙ አሰልጣኝ ጋሬት ሳውዝጌት ሲተች ሮናልድ ኩማን ደግሞ በዚህ በኩል እየተሞገሰ ነው።

የእንግሊዝ ተጫዋቾች ቬጎረስት ከተቀያሪ ወንበር ላይ እየተነሳ ከሚፈጥረው ስጋት በተጨማሪ የኮዲ ጋክፖን አደገኛ አጨዋወትም መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል።

ጋክፖ ለሊቨርፑል በሚጠበቀው መልኩ መንቀሳቀስ ባይችልም በአውሮፓ ዋንጫው የኔዘርላንድ ኮከብ ተጫዋች መሆኑን እያሳየ ይገኛል።

ኩማን ትልቅ ተጋጣሚ ከፊታቸው ሲገኝ በሦስት ተካላይ መጫወትን ይመርጣሉ።

ይህ ደግሞ የተሻለ የአማካይ ተጫዋቾች ስብስብ ላላት እንግሊዝ የተመቸ ነው።

እንግሊዝ የአጥቂ መስመር እስካሁን ውጤታማ መሆን አልቻለም።

በዚህ ጨዋታ እንግሊዝ ካለፉት ጨዋታዎች ተሻሽላ በመግባት ኔዘርላንድን ታንበረክካለች ብዬ አልጠብቅም።

እንግሊዝ ለተከታታይ ሁለተኛ የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ ለመድረስ የተጫዋቾች የግል ብቃት ሊያስፈልጋት ይችላል።

በውድድሩ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጠንካራ ቡድን የሚጠብቃት እንግሊዝ በጠባብ ውጤት ታሰንፋለች።

ግምት፡ 1 – 2