ቻይና፤ ኤአይ ራስን ከመጉዳት ጋር የተያያዙ ምክሮችን ለታዳጊዎች እንዳይሰጥ የሚከለክል ሕግ ልታወጣ ነው

ሞባይል እየተጠቀመች ያለች ሕጻን ልጅ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ቻይና ለሕፃናት ደህንነት ጥበቃ የሚሰጡ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቻትቦቶች ራስን ለመጉዳት ወይም ለጥቃት የሚዳርጉ ምክሮችን እንዳይሰጡ የሚከለክሉ አዳዲስ ጥብቅ ሕጎችን ይፋ አደረገች።

የአገሪቱ መንግሥት ያዘጋጀው ረቂቅ ሕግ፤ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚያቀርቧቸው የኤአይ ሞዴሎች ቁማርን የሚያበረታቱ እንደሆኑ የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለባቸው ይደነግጋል።

ይህንን ህግ ያስተዋወቀችው በቻይና እና በዓለም ዙሪያ በርካታ ይፋ የሚደረጉ የኤአይ ቻትቦቶች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመሩን ተከትሎ ነው።

ሕጉ ሲጸድቅ ቻይና ውስጥ ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን በሚያቀርቡ ሁሉም የኤአይ ኩባንያዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል። ይህ የቻይና ሕግ፤ በደቀናቸው የደህንነት ስጋቶች ምክንያት ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገበት እና በፍጥነት እያደገ የመጣውን ቴክኖሎጂ ለመቆጣጠር የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ይሆናል።

በቻይና የሳይበርስፔስ አስተዳደር አማካኝነት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ይፋ የተደረገው ረቂቅ ሕጉ፤ የሕጻናትን ደህንነት የሚያስጠብቁ እርምጃዎችን አካትቷል። የኤአይ ኩባንያዎች የአጠቃቀም የሰዓት ገደብን እንዲያበጁ እንዲሁም ለስሜታዊ አጋርነት (emotional companionship) አገልግሎት ከመስጠታቸው በፊት ከአሳዳጊዎች ፈቃድ እንዲያገኙ የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን ይዟል።

የኤአይ ኩባንያዎች በመተግበሪያዎቻቸው ላይ በግለሰባዊ ምርጫዎች ላይ የተመሰረቱ ማስተካከያዎችን (personalised settings) እንዲያቀርቡም ይገደዳሉ።

የኤአይ ቻይቦት ኦፕሬተሮች፤ ማንኛውም ራስን ከማጥፋት ወይም ራስን ከመጉዳት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሚነሱበት ወቅት ንግግሩን ከኤአይ ወጥቶ በሰዎች ቁጥጥር ስር እንዲሆን የማድረግ ግዴታ ይጣልባቸዋል። ወዲያውኑም ሁኔታውን ለተጠቃሚውን አሳዳጊ ወይም የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅራቢዎች አገልግሎቶቻቸው "ብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል፣ ብሔራዊ ክብርን እና ጥቅምን የሚጎዳ [ወይም] ብሔራዊ አንድነትን የሚያናጋ ይዘት" እንዳያመነጩ ወይም እንዳያሰራጩ ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸውም መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

መስሪያ ቤቱ ቴክኖሎጂው ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ እስከሆነ ድረስ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀምን እንደሚያበረታታ ገልጿል። ተቋሙ በምሳሌነት ካነሳቸው የኤአይ አገልግሎቶች መካከል የአካባቢን ባህል ለማስተዋወቅ እና ለአረጋውያን የአጋርነት ለመፍጠር የሚሉት ይገኙበታል።

በአውሮፓውያኑ 2025 'ዲፕሲክ' የተባለው የቻይና የኤይ ከኩባንያ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

በዚህ ወር ደግሞ 'Z.ai' እና 'Minimax' የተባሉ ሁለት የቻይና ጀማሪ ጤሌክኖሎጂ ድርጅቶች የአክስዮን ገበያ ውስጥ እንደሚገቡ ካስታወቁ በኋላ በድምሩ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠር ተጠቃሚዎችን ማግኘት ችለዋል።

የአይአይ ቴክኖሎጂው በፍጥነት እጅግ በጣም ብዙ ተጠቃሚዎችን ያገኘ ሲሆን አንዳንዶችም ለአጋርነት ወይም ለስነ-ልቦና ህክምና (therapy) አገልግሎት እየተጠቀሙበት ነው።

ኤአይ በሰዎች ባህሪ ላይ ከሚያደርሰው ተጽዕኖ ጋር በተያያዘ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ትችት እየተቀረበበት ነው።

የቻይትጂፒቲ ዋና ኃላፊ የሆነው ሳም አልትማን እንደሚናገሩት፤ ኩባንያው አስቸጋሪ ሁኔታዎች አንዱ፤ ቻትቦቶች ከሰዎች ጋር በሚደረጉ ንግግሮች ወቅት ራስን ከመጉዳት ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች የሚሰጡት ምላሽ የሚሰጡበት መንገድ ነው።

ነሐሴ ላይ፤ በአሜሪካ ካሊፋርኒያ ግዛት የሚገኝ አንድ ቤተሰብ የ16 ዓመት ልጃቸው ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ የቻትጂፒቲ ፈጣሪ የሆነው ኦፕንኤአይ ላይ ክስ መስርተዋል። የታዳጊው ወላጆች፤ ቻትጂፒቲ ልጃቸው ራሱን እንዲያጠፋ እንዳበረታታው በመጥቀስ ወንጅለዋል።

ይህ ክስ ኦፕንኤአይን በሰው ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ በማድረግ የተከፈተ የመጀመሪያው ክስ ነው።