'ከምንግዜም ምርጡ' የፍጻሜ ጨዋታ በኋላ ማን ምን አለ?

የአርጀንቲና ተጫዋቾች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

“እንደዚህ ዓይነት ነገር በፍጹም ደግም አናይም” ያለው የእንግሊዝ የቀድሞ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ ነው። ፈርዲናንድ ብዙዎች ያሰቡትን ነው ቅልብጭ አድርጎ የገለጸው።

ሁሉም ሙሉ የነበረበት ነው። ከዋክብቱ ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔ የተፋጠጡበት። ጨዋታው አበቃ ሲባል ድጋሚ ነፍስ የሚዘራበት አስገራሚ ምሽት። ስሜትን ሰቅዞ የሚይዝ የመለያ ምት ያለበት ጨዋታ።

ማህበራዊ ሚዲያው የተጥለቀለቀበት። የስፖርት ከዋክብት የፈዘዙበት፤ በሉሳይል ስታዲም የተገኙ ደግሞ ታሪክ በዓይናቸው ያዩበት ምሽት።

“ይህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም። ሁለት ግዙፍ ቡድኖች እግር በእግር የተያያዙበት ነው” ሲል ፈርዲናንድ ለቢቢሲ ዋን ገልጿል።

"በሁለቱም ቡድኖች ያሉት ሁለቱ ኮከቦች ጎል በጎል ላይ ያስቆጠሩበት . . . ግሩም" ብሎታል።

የቀድሞ እንግሊዝ አጥቂ አለን ሺረር ደግሞ "ትንፋሽ አጥሮናል፤ ለማመን የሚከብድ ፍጻሜ ነበር። እንደዚህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። እንደገናም አያለሁ ብዬ አላስብም። በጣም አስገራሚ ነበር" ሲል ተናግሯል።

የአርጀንቲናው አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ከጨዋታው በኋላ "ተረጋግቻለሁ" ቢልም ስሜቱን ግን መደበቅ አልቻለም።

"ጨዋታው ሙሉ በሙሉ እብደት ነበር። ጥሩ እንደተጫወትን አውቃለሁ። በ90 ደቂቃው ማሸነፍ እንችል ነበር" ብሏል።

“ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ጥሩ ስሜት ተፈጥሮብኛል። በጣም አስፈላጊው ነገር ይህንን ያሳካንበት መንገድ ነው" ሲል አክሏል።

አስደናቂው ፍጻሜ እንዴት ተጠናቀቀ

  • 23 ደቂቃ - አርጀንቲና 1-0 ፈረንሳይ - ሜሲ ከፍጹም ቅጣት ምት አስቆጠረ
  • 36 ደቂቃ - አርጀንቲና 2-0 ፈረንሳይ - ኤንጄል ዲ ማሪያ የአርጀንቲናን መሪነት አሰፋ
  • 80 ደቂቃ - አርጀንቲና 2-1 ፈረንሳይ - ምባፔ ከፍጹም ቅጣት ምት አስቆጠረ
  • 81 ደቂቃ - አርጀንቲና 2-2 ፈረንሳይ - ምባፔ በአስደናቂ ጎል ቡድኑን አቻ አደረገ
  • 108 ደቂቃ - አርጀንቲና 3-2 ፈረንሳይ - ሜሲ በተጭማሪ ሰዓት አርጀንቲና ወደ መሪነት መለሰ
  • 118 ደቂቃ - አርጀንቲና 3-3 ፈረንሣይ - ምባፔ ሃትሪክ በመሥራት ጨዋታው በመለያ ምት እንዲጠናቀቅ አስገደደ
Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ከጨዋታው በፊት አብዛኛው ትኩረት አርጀንቲናዊው ሜሲ እና ፈረንሳዊው ምባፔ ላይ ነበር። ለኮከብ ጎል አግቢነት ከሚደረገው ግብግብ ሌላ ቡድናቸው ለዋንጫ የሚያበቁ መሆኑ ሲነገርላቸው ነበር።

ምባፔ በመጀመርያው አጋማሽ ሜዳ ላይ መኖሩም ተረስቶ ነበር። አርጀንቲና በአሌክሲስ ማክ አሊስተር አማካኝነት የመጀመሪያውን ሙከራ ለማድረግ አራት ደቂቃ ብቻ ወሰደባት። ከዚያ በኋላም ጨዋታውን በበላይነት ተቆጣጠረች።

የሜሲ ተሳትፎ የጀመረው በ23ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ፍጹም ቅጣት ምት አርጀንቲናን ቀዳሚ ሲያድርገ ነው። አንጄል ዲ ማሪያ ከ13 ደቂቃ በኋላ ሁለተኛዋን አስቆጠረ።

ፈረንሳዮች ግራ ተጋብተው ነበር። ምባፔ ተሳትፎው በጣም ተገድቦ ነበር።

በቃኝ ያሉት አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ 41ኛው ደቂቃ ሁለት ተጫዋቾችን ቀየሩ። ኦሊቪዬ ዥሩ እና ኦስማን ዴምቤሌ ወጥተው ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ እና ማርከስ ቱራምን ተኳቸው።

ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል ሁለቱ ቡድኖች ሲያመሩ ፈረንሳይ ወደ ጎል ምንም ሙከራ አላደረገችም። አርጀንቲና 2 ለ 0 እየመራች ነው። ጨዋታው ተጠናቋል በሚል ጋዜጠኞች የጨዋታ ሪፖርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ነበሩ።

ድራማው ግን ገና አልተጀመረም።

የአርጀንቲናውን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን በ67ኛው ደቂቃ ስትፈትን እንኳን ፈረንሳይ ገና ወደ ጨዋታው አልተመለሰችም። ወዲው ግን ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ያዙ. . .

ሙአኒ በፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ በኒኮላስ ኦታሜንዲ ተጠልፎ ወደቀ። ምባፔ ፍጹም ቅጣት ምት ሊመታ ማርቲኔዝ ጎሉን ላለማስደፈር ተፋጠጡ።

አሁን ጨዋታ ደራ።

አርጀንቲና 2 ፈረንሳይ 1።

አርጀንቲናዎች ትንፋሽ እንኳን ሳይሰበስቡ ምባፔ በአስደናቂው ሁኔታ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 2-2 ሆነ። ተጨማሪ 30 ደቂቃ ተጀመረ።

የሜሲ ምሽት ነበር በ 108 ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ዋንጫዋ ወደ አርጀንቲና አዘነበለች።

ምባፔ ግን ሥራውን አላጠናቀቅም። ሃትሪክ ያስቆተረበትን ጎል በ118ኛው አሳካ። ይህም ከእንግሊዙ ሰር ጂኦፍ ሁረስት (1966) በመቀጠል 3 ጎሎችን በዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያስቆጠረ ሁለተኛው ተጫዋች አድርጎታል። አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ማምራት ግድ ሆነ።

በጨዋታው ሁለት ጊዜ መምራት ችላ የነበረችው አርጀንቲና ከ1986 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አነሳች። ማርቲኔዝ የኪንግስሌይ ኮማንን ኳስ ሲኣድን እና አውሬሊ ቹአሜኒ ደግሞ ኳሷን ወደ ው ሰዷታል።