ለ100 ዓመት የሌኒን አስክሬን እንዴት ተጠብቆ ቆየ? 5 ነጥቦች ስለሌኒን የመታሰቢያ ስፍራ

የታላቁ የሩሲያ አብዮት መሪ ለነበረው ለቭላድሚር ኤሊች ሌኒን የተሠራው መታሰቢያ ስፍራ 100ኛ ዓመቱን በዚህ ዓመት ደፈነ።

በመታሰቢያነት በተሠራው በዚህ ስፍራ በርካታ ክንውኖችና ወታደራዊ ትዕይንቶች ይካሄዳሉ።

በአንድ ወቅት የሌኒን አስክሬን ከተቀበረበት ወጥቶ በዚህ መታሰቢያ ቦታ ተቀምጧል። የጆሴፍ ስታሊን አስክሬንም ወደዚህ ስፍራ ገብቶ ወጥቷል።

በ1970ዎቹ ጥይት በማይበሳው መስታወት የሌኒንን መታሰቢያ እንዲጠብቅ ቆሟል።

የሌኒን አስክሬን ሰውነቱ ባለበት ሁኔታ እንዲቆይ ተደርጎ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኗል።

ሶሻሊስቷ አገር ሶቪየት ኅብረት ስትፈራርስ በአውሮፓውያኔ 1990ዎቹ የሌኒን አስክሬን ከተቀመጠበት ወጥቶ እንዲቀበር ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።

የሌኒን አስከሬን ስለተቀመጠበት የመታሰቢያ ስፍራ መታወቅ ያለባቸው 5 ነጥቦች፡

ሐሳቡ የማን ነበር?

የሌኒንን አስከሬን ሳይፈርስ ጠብቆ የማቆየት ሐሳብ በ1923 የቀረበ በጆሴፍ ስታሊን እንደሆነ የታሪክ ምሁራን ይስማማሉ።

በወቅቱ ከኬጂቢ እና ከኤፍኤስቢ በፊት የነበረው የሩሲያ የስለላ ተቋም 'ሶቭየት ቻካ' መሪ አሁን ዩክሬን ውስጥ በምተጘነው ኻርኪቭ ሥራ ላይ ሳለ ሞቶ ነበር።

ቭላድሚር ቮሮብዮቭ የተባለ ወጣት ሳይንቲስት የመሪውን ሰውነት ባለበት ሆኖ አስክሬኑ እንዲቆይ አደረገ።

ሞስኮ ውስጥ አስክሬኑን የተመለከቱ ኮሚኒስቶች በጣም ተደነቁ።

በወቅቱ ሌኒን በጠና ታሞ ነበር። ስለ ሌኒን ሁኔታ ከፓርቲው ጋር ስታሊን ውይይት እያደረገም ነበር።

የሌኒን አስክሬን ተጠብቆ ባለበት ሁኔታ መኖር እንዳለበት ስታሊን ተከራክሯል።

ተቃዋሚዎቹ ግን ሐሳቡን አልተቀበሉም። እነዚህ ተቃዋሚዎች በ1930ዎቹ ተገድለዋል።

ሊዮን ትሮስኪ ቅርስ በማርክሲዝም ውስጥ ቦታ የለውም ሲል ተከራረከ። ኒኮላይ ቡክሀሪን በበኩሉ የአብዩታዊ መሪን አስክሬን ጠብቆ ማቆየት ትውስታውን ማጠልሸት ነው አለ።

የሌኒን ባለቤት ናድዛዳ ክሩፕካያ የሌኒን አስክሬን እንደ አምልኳዊ ቁስ እንዳይቀመጥ ጠየቀች።

ሆኖም ወደ ኃያልነት ማማ እየወጣ የነበረው ስታሊን ሐሳቡን አልተቀበለም።

ሐሳቡ ተቀባይነት እንዲያገኝ የሠራተኞች ስብስብ ደብዳቤዎችን አቀርቧል። እነዚህ ደብዳቤዎች የእውነት ይሁኑ አልያም ሐሳቡን ለማስረጽ የተፈጠሩ ይሁኑ እስካሁን አይታወቅም።

ደብዳቤዎቹ ሌኒን ሁሌም አብሮን መሆን አለበት ይላሉ።

ማን ገነባው?

የመጀመሪያው የሌኒን አስከሬን ያረፈበት የመታሰቢያ ስፍራ ሦስት ሜትር ከፍታ ያለው ነበር።

ከቀብሩ ከሦስት ቀናት በኋላ ነው የተጠናቀቀው። አርክቴክቱ አሌክሲ ሹቹስቭ ይባላል።

ሌኒን የሞተው እአአ ጥር 21/1924 ሲሆን፣ እስከ መጋቢት ድረስ የመሸኛ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በመታሰቢያው ስፍራ ተገኝተዋል።

በ1924 አጋማሽ አስክሬኑን ለዕይታ የማዋል ሐሳብ ዕውቅና አገኘ። የመታሰቢያው ሕንጻ ሥራም ተጀመረ። አርክቴክቱ ሌሎች ሁለት አሌክሲ ቮሮብዬቭ እና ቦሪስ ዛባርስኪ የተባሉ አርክቴክቶችን አሳተፈ።

እአአ ነሐሴ 1/1924 መታሰቢያው ለሕዝብ ክፍት ሆነ።

የተሠራው በእንጨት ቢሆንም ቅርጹ አሁን ያለውን ይመስላል።

ተገንብቶ ያለቀው በ1930 ነው። ቅርጹ የስታሊን ምርጫ ነበር። የሶቭየት ኅብረትን ታላቅነትን እና የተለየች መሆንን እንዲያሳይ ተፈልጎ ነው የተገነባው።

በአስክሬኑ ጎን ለማለፍ ሲሉ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይሰለፋሉ።

ሌኒን እና ስታሊን በመታሰቢያው በጋራ ቆይተዋል

በ1953 ስታሊን ሲሞት በሌኒን መታሰቢያ እንዲቀበር ተወሰነ።

የስታሊን አስክሬን ፊት በጥሩ ሁኔታ ላይ አልነበረም።

የመታሰቢያው መጠሪያ ‘ሌኒን-ስታሊን’ ወደሚል ተቀየረ። ዝናብ አዲሱ መጠሪያ ላይ ዘንቦ ሲፍቀው ከስር ያለው ‘ሌኒን’ የሚለው የመጀመሪያው መጠሪያ ይታይ ነበር።

የሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ስታሊንን የማጠልሸት ንቅናቄ ሲጀምር አስክሬኑ ከመታሰቢያው በ1961 ወጥቶ በክሬምሊን አካባቢ ተቀበረ።

የርዕዮተ ዓለም ‘አምልኮ’ ስፍራ

ከጦርነቱ በኋላ እና ሶቭየት ኅብረት እስከምትወድቅ ድረስ የመታሰቢያው ቦታ እንደ አምልኮ ስፍራ ነበር።

ከውጭ አገር የሚሄዱ ሰዎች እና የሶቭየት ኅብረት ተማሪዎችም ይጎበኙታል።

በግንቦት 1945 የድል ትዕይንት ሲታይ የናዚ ጀርመን ሰንደቅ አላማ በመታሰቢያው ፊት ተጥሎ ነበር። ይህም የሶቭየት ኅብረትን የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ድል ለመዘከር ነው።

ወደ ህዋ በመጓዝ የመጀመሪያው ሰው የሆነው የሶቪየት ጠፈረተኛ ዩሪ ጋጋሪ፣ በሶቪየት መሪ ኒኪታ ክሩሼቭ ሰላምታ የተሰጠው በዚህ መታሰቢያ ስፍራ ነው።

ከ1950ዎቹ እስከ 1970ዎቹ ማገባደጃ የሌኒን አስክሬን የተለያየ ጥቃት ይደርስበት ነበር። ድንጋይ፣ መዶሻ ወይም ተቀጣጣይ ነገሮችን መወርወር የተለመደ ነበር።

ጥቃት ሲፈጽሙ የተያዙ ሰዎች የሥነ ልቦና ሕክምና ይሰጣቸው ነበር።

በ1973 በፈንጂ ምክንያት ብዙ ቱሪስቶች ተገድለዋል። ከዚያ በኋላ የሌኒን አስክሬን ያለበት ቦታ ጥይት በማይበሳው መስታወት ተሸፈነ።

የሌኒን አስክሬን

ከሶቪየት ኅብረት መፈራረስ በኋላ ኮሚኒዝምን የሚጠሉት ፕሬዝዳንት ቦሪስ የልሲን ንግግር ያደረጉት መታሰቢያው ባለበት ‘ቀዩ አደባባይ’ አደባባይ ነበር።

በ1990ዎቹ መባቻ የሌኒንን አስክሬን ጠብቆ የሚያቆየው ቤተ ሙከራ የሚሰጠው የገንዘብ ድጎማ ተቋረጠ።

ከዚያን ጊዜ በኋላ ስለ መታሰቢያው እና የአስክሬኑ ጥበቃ ብዙ ዘጋቢ ፊልሞች ተሠርተው በሩሲያ ቴሌቭዥን ጣቢያ ታይተዋል።

የሌኒን ሰውነት ከቀድሞ ገጽታው 23 በመቶ ብቻው እንደቀረ በፊልሞቹ ተነግሯል። የተቀረው የሰውነት ክፍሉ ሰው ሠራሽ እንደሆነም ተገልጿል።

አሁንም ድረስ ይህ የሌኒን የመቃብር እና የመታሰቢያ ስፍራ በቱሪስቶች ይጎበኛል።

የቱሪስት መዳረሻዎች ጠቋሚው ‘ትሪፕ አድቫይዘር’ ከአምስት ነጥብ አራት ሰጥቶታል።

አንድ አስተያየት ሰጪ “ልጄ ቢጫ ፊቱን አይታ ፈርታ ነበር” ሲሉ ሌላ ሰው “ስለ ሶቭየት የሚያውቅ ሰው መጎብኘት ያለበት ቦታ ነው” ብለዋል።

በምሥራቅ እና ደቡብ ምሥራቅ እስያ ያሉ የኮሚኒስት መሪዎች አስክሬን አሁንም ድረስ ይገኛል። ከእነዚህ መካከል የቻይናው መሪ ማኦ ዜ ዶንግ፣ የቬትናም መሪ ሆ ቺ ሚን ይገኙበታል።

በሰሜን ኮሪያ የኪም ኤል ሱንግ እና ኪም ጆንግ ኢል አስክሬኖች በመታሰቢያ ስፍራ ይገኛሉ።