ጋና ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበትን የወባ ክትባት በማጽደቅ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች

ባበለጸጉት ሳይንቲስቶች “ዓለምን ቀያሪ” የሚል ስያሜ የተሰጠወን የወባ ክትባት በማጽደቅ ጋና የመጀመሪያው ሀገር ሆናለች።

R21 በመባል የሚጠራው ክትባቱ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ክትባቶች ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ውጤታማ ነው ተብሏል።

የክትባቱን ደህንነትና ውጤታማነት ሲፈትሽ የቆየው የጋና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ይፋ ባያደርገውም ጥቅም ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።

የዓለም ጤና ድርጅትም ክትባቱን ለማጽደቅ እያሰበ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

በዓለም ዙሪያ ወባ በየዓመቱ 620 ሺህ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው።

ሰውነትን ከወባ አምጪ ተውሳክ የሚከላከለውን ይህንን ክትባት ለማበልጸግ አንድ ክፍለ ዘመንን የፈጀ ሰፊ ምርመራ ተደርጓል።

በቡርኪና ፋሶ በቅድመ ጥናት ወቅት በተደረገ ሙከራ R21ን ሶስት ጊዜ የወሰዱና በዓመቱ ማጠናከሪያ ክትባት የተሰጣቸው በሽታውን የመከላከል አቅማቸው 80 በመቶ አድጓል።

ሆኖም የክትባቱን ውጤት ማረጋገጫ ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ሕጻናት የሚሳተፉበት የሙከራ ክትባት የሚያስገኘው ውጤት ላይ የሚመረኮዝ ነው።

ይህንንም ባለፈው ዓመት መጨረሻ እንደሚደረግ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ውጤቱ እስካሁን ይፋ አልሆነም። ነገር ግን በአፍሪካ ለሚገኙ አንዳንድ ባለስልጣት እና ሳይንቲስቶች ደርሷል።

የሙከራውን ወጤት የተመለከው የጋና ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ክትባቱ ከ5 ወር እስከ 3 ዓመት ያሉ ህጻናት እንዲወስዱት ይሁንታ ሰጥቷል።

እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ክትባቱን ለማጽደቅ የቀረበላቸውን መረጃ እያጠኑ ነው።

አንድ በጋና የሚገኝ የህንድ ተቋም በዓመት ከ100 እስከ 200 ሚሊዮን ክትባቶችን የሚያመርት ፋብሪካ በጋና ይገነባል።

አንዱ የ R21 ክትባት እስከ ሁለት ዶላር ሊሸጥ እንደሚችል ተገምቷል።