ቼልሲ ከማንቸስተር ሲቲ እና ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

32ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መርሐ ግብር ከሳምንታት በኋላ አርብ፣ ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናል።

ቅዳሜ እና እሑድ አራት አራት ጨዋታዎች ሲከናወኑ ቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች አርብ እና ሰኞ ይከናወናሉ።

በሳምንቱ ከሚከናወኑት መርሐ ግብሮች መካከል ኤልሲ በሜዳው ማንቸስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የቢቢሲው የእግር ተንታኝ ለክሪስ ሱተን የጨዋታዎቹን ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

አርብ

ዌስት ሃም ከ ዎልቭስ

ዎልቭስ ከሊጉ የመውረዱ ጉዳይ የማያጠያይቅ ቢሆንም በአሰልጣኝ ሮብ ኤድዋርድ ስር መሻሻል አሳይተዋል።

ዌስት ሃም ከሊድስ ጋር ባደረገው የኤፍኤ ካፕ ጨዋታ ወደ ተጨማሪ ሰዓት ማምራቱ ቡድኑን እንዳያዳክመው ያሰጋል።

ቡድኑ ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ቢያሸንፍም ከወራጅ ቀጠና እንደሚወጣ እገምታለሁ።

ዘንድሮ ዎልቭስ ሁለት ጊዜ ከዌስትሃም ጋር ተገናኝቶ ማሸነፍ ቢችልም ይህንን ጨዋታ በድል የሚያጠናቅቀው የለንደኑ ክልብ እንደሚሆን አስባለሁ።

ግምት፡ 2 - 1

ቅዳሜ

አርሰናል ከ በርንመዝ

የሚኬል አርቴታ ቡድን ከሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ በማሸነፍ ጥሩ ምላሽ የሰጠበትን አካሄድ እንደምንመለከት አስባለሁ።

በርንመዝ ባለፉት 11 ጨዋታዎች አለመሸነፉ በዚህ መርሐ ግብርም ጥሩ እንደሚፎካከር ማሳያ ነው።

አርሰናል በየአቅጣጫው ጫና ቢደረግበትም ከቀሩት ጨዋታዎችን አንጻር በመጀመሪያው ዙር ያላሸነፈው ሲቲን ብቻ መሆኑን ማሰብ አስፈላጊ ነው።

ግምት፡ 2 - 0

ብሬንትፎርድ ከ ኤቨርተን

ሁለቱም ቡድኖች በ46 ነጥብ ስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃ ላይ ከመገኘታቸው አንጻር በሻምፒዮንስ ሊግ ስለመሳተፍ ማለም ይኖርባቸዋል።

የውድድር ዓመቱ ሲጀመር ኤቨርተን ከሊቨርፑል በላይ እንደሚሆን ማን ገምቶ ነበር? በቀጣይ ሁለቱ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ወሳኝ ነው።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ብሬንትፎርድ ከሜዳው ውጭ 4 ለ 2 ማሸንፍ ችሎ ነበር።

በዚህ ጨዋታ ሁሉም ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው እንደሚወጡ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

በርንሌይ ከ ብራይተን

ብራይተን ውድድሩ ለዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ከመቋረጡ በፊት ወደ ጥሩ አቋሙ መመለስ ችሎ ነበር።

ካለፉት አምስት ጨዋታዎችም አራቱን ማሸነፍ ችለዋል።

በርንሌይ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑን ደጋግሞ ማሳየት ቢችልም ወደ ውጤት ግን ሊቀይረው አልቻለም።

በተደጋጋሚ እንዳልኩት ቡድኑ ከሊጉ መውረዱ አይቀሬ ይመስላል።

ግምት፡ 0 - 1

ሊቨርፑል ከ ፉልሃም

የሊቨርፑል ደጋፊዎች አሰልጣኝ አርን ስሎት እንዲባረሩ ቢፈልጉም ካለፈው ዓመት የሊጉ ዋንጫ ባለቤትነታቸው አንጻር ተገቢ አይመስለኝም።

ቡድኑ ጥሩ መጫወት ባይችልም ባሉት ጥሩ ተጫዋቾች ምክንያት ጥሩ ውጤት ሊያስመዘግብ እንደሚችል እገምታለሁ።

ፉልሃም ጥሩ ቡድን ከመሆኑ አንጻር ለሊቨርፑል ፈታኝ ጨዋታ ይሆናል።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ሁለት አቻ የተለያዩ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ጎሎች እንደሚቆጠሩ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 - 2

እሑድ

ክሪስታል ፓላስ ከ ኒውካስል

ፓላስ በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ከፊዮሬንቲና ጋር በሚያደርጓቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች መካከል የሚከናወን መርሃ ግብር ነው።

ይህ ለኒውካስል ጥሩ ዕድል ቢመስልም ቡድኑ ከሜዳው ውጭ ያለው አቋም ደካማ ነው።

ኒውካስል በጥሩ ውጤት የውድድር ዓመቱን ማጠናቀቅ ቢኖርበትም በሜዳ ላይ ያለው ውጤት ግን በቂ አይደለም።

ግምት፡ 1 - 1

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ አስቶን ቪላ

ቪላ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ሲጫወት ፎረስት ደግሞ ላለመውረድ በመታገል ላይ ይገኛል።

ቡድኑ አጥቂው ክሪስ ዉድ ከረዥም ጊዜ ጉዳት በኋላ መመለሱ ምርጥ ዜና ሆኖለታል።

ለሁለቱም ቡድኖች ማሸነፍ ትልቅ ጉዳይ ቢሆንም ነጥብ እንደሚጋሩ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

ሰንደርላንድ ከ ቶተንሃም

አዲሱ የቶተንሃም አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዜብሪ ምን ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ?

ሰንደርላንድ በሜዳው ያለው አቋም የተዳከመ ቢመስልም ከሳምንታት በፊት ኒውካስልን ማሸነፋቸው መነቃቃትን እንደሚፈጥርላቸው ይጠበቃል።

ስፐርስ ዲ ዜብሪ የሚመርጡትን አጨዋወት ከተከተለ ለተጋጣሚዎች ዕድል ሊፈጠር ይችላል። በዚህ ወቅት ይህንን ኃላፊነት ይወስዳሉ?

ሰንደርላንድ ወደ ጨዋታው የሚገባው በጥሩ መንፈስ ላይ ሆኖ ነው።

ግምት፡ 1 - 0

ቼልሲ ከ ማንቸስተር ሲቲ

ሁሉም ተጫዋች ለትልቅ ቡድን የመጫወት ህልም አለው። ተጫዋቹ ለሪያል ማድሪድ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው ጠቅሷል። በዚህ ምክንያትም ሊያም ሮዘኒየር አማካዩ ኤንዞ ፈርናንዴዝን በተመለከተ የያዙትን አቋም አልደግፍም።

ኤንዞ የቼልሲ ጥሩ ብቻ ሳይሆን ኮከብ ተጫዋቻቸውም ጭምር ነው።

ባለፉት ጨዋታዎች በተገመተው ልክ ያልነበረው ሲቲ ከአርሰናል እና ከሊቨርፑል ጋር ድንቅ አቋም ማሳየት ችሏል።

የሊጉ ውድድር ደምቆ እንዲቀጥል ስለምፈልግ ሲቲ እንዲያሸንፍ ብፈልግም ነጥብ ሊጥልም ይችላል።

ግምት፡ 1 - 2

ሰኞ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊድስ ዩናይትድ

ዳንኤል ፋርክ በሊድስ እየሠሩት ያለው ነገር መልካም ሲሆን ለኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜም ለማለፍ ችለዋል።

ማይክል ካሪክ በበኩሉ የቡድኑን ውጤት በመቀየር በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እንዲፎካከሩ አስችሏቸዋል።

በሜዳው ካለው አቋም አንጻር ማንም ድሉን ከማንቸስተር ውጭ እንደማይገምት አስባላሁ።

ግምት፡ 2 - 1