በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኤታማዦር ሹሙ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጋር ችግኝ ሲተክሉ

የፎቶው ባለመብት, Abiy Ahmed Ali/fb

የምስሉ መግለጫ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኤታማዦር ሹሙ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጋር ችግኝ ሲተክሉ

የኢትዮጵያ መንግሥት በየዓመቱ የሚያካሂደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አንድ አካል የሆነው የችግኝ ተከላ ሂደት በአንድ ቀን 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ በመላው አገሪቱ እየተካሄደ ነው።

ዛሬ አርብ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም. እየተካሄደ ባለው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምዕራባዊው የአገሪቱ ክፍል ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ተገኝተው ችግኞችን መትከላቸውን አሳውቀዋል።

በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ከፌደራል እና ከክልል ባለሥልጣናት ጀምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ችግኞችን እየተከሉ መሆናቸውን የመገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ምክትላቸው ችግኝ ሲተክሉ

የፎቶው ባለመብት, PM Abiy Ahmed FB

የምስሉ መግለጫ, ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ምክትላቸው ችግኝ ሲተክሉ

የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በዛሬው ዕለት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካይነት የሚተከሉት 600 ሚሊዮን ችግኞች ባለፉት አምስት ዓመታት በአገሪቱ የተተከሉትን ችግኞች ቁጥር ወደ 40 ቢሊየን ያደርሰዋል።

የመከላከያ ሠራዊት አባላት ችግኝ ሲተክሉ

የፎቶው ባለመብት, FDRE Defense Force/fb

የመከላከያ ሠራዊት አባላት ችግኝ ሲተክሉ

የፎቶው ባለመብት, Shimelis Abdisa/fb

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመረሃ ግብሩ አማካከይነት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ችግኞችን መትከላቸውን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት፣ በተመሳሳይ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፈው ዓመት ከተተከሉት ችግኞች “50 ከመቶው በምግብ ዋስትና፣ አፈር ጥበቃ እና የመሬት መራቆት ላይ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ የተተከሉ” መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለዚህ የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በሚገኝበት የቤኒሻንጉል ክልል የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም እንደ አባይ ተፋሰስ ባሉ አካባቢዎች ችግኞችን በመትከል የውሃ ጥበቃ ሥራን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ችግኝ ተከላ

የፎቶው ባለመብት, Takele Uma Banti/fb

ችግርኝ ተከላ

የፎቶው ባለመብት, Shimelis Abdisa/fb