የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጩኸት፤ የመንግሥት ዝምታ

ከሚማሩበት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቀ ወጣቶች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ አላገኘም።
ተማሪዎቹ ከታገቱ 50 ቀናት አልፏቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸው መታገታቸውን ከሰሙ አንስቶ ለሚመለከታቸው አካላት ልጆቻቸውን እንዲመለሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጠም።
የተማሪዎችን መታገት ተከትሎ ከቀናት በፊት ወደ አዲስ ዘመን ያቀናው የቢቢሲ ዘጋቢ ከተማዋ ሃዘን እንዳጠላባት ይናገራል።
የታጋች ቤተሰቦች ፊታቸው ጠቁሮ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው ነው ያገኘኋቸው የሚለው ዘጋቢያችን ቤተሰቦችን ማነጋገር እጅግ አሳዛኝ እንደነበር ያስረዳል።

መሪጌታ የኔነህ አዱኛ የተማሪ ግርማሽ የኔነህ አባት ናቸው።
መሪጌታ የኔነህ ''በጥር 2 ተለቀዋል ስንባል ደስ ብሎን ነበር፤ ነገር ግን እስካሁን ከልጆቻችን ጋር አልተገናኘንም። መንግሥትም ያለን ነገር የለም። ገድለውብን ይሆናል ብለን እየፈራን ነው። በዚያ ላይ ልጆቹ አይተውት የማያውቁትን ነገር ሲያዩ ይደነግጣሉ ብለን እናስባለን። ሞተውም ከሆነ እውነቱን ነግረውን ቤተሰብ ጋር ተሰባስበን አልቅሰን እርማችንን ብናወጣ ይሻለናል፤ እንዲህ በየቀኑ ምን ሆነው ይሆን እያልን በሰቆቃ ከምንኖር" ይላሉ።
መሪጌታ እንደሚሉት የልጃቻቸው መታገት በቤተሰባቸው ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ማሳደሩን ይናገራሉ። "ባለቤቴ ጨንቅላቷ ተጨንቆ ጸበል ወስጄ ነው ያከረምኳት" በማለት ይናገራሉ።
ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ

ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ ናቸው።
ወ/ሮ ማሬ የእጅ ስልክ ስለሌላቸው በላይነሽን በስልክ ካገኙ ሰነባባተዋል። "ስልክ ስለሌለኝ የሆነው ሁሉ የምሰማው ከሰው ነው" ይላሉ።
''እህል አልበላ። ሌተ ተቀነ አይ ጉድ እያልኩ ነው። እግዜር ቢሰማን፤ መንግሥትም ቢራራልን፣ ልጆቻችን ቢሰዱልን እያልን ነው . . . አሳድጌ አሳድጌ ልጅ የለኝም ማለት ነው?" ሲሉም መልሰው ይጠይቃሉ።
ተማሪዎቹን መንግሥት እንዳስለቀቃቸው ሲሰሙ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸው እንደነበረ የሚያስታውሱት ወ/ሮ ማሬ፤ "ወሬ ሆኖ ቀረ እንጂ" በማለት ተማሪዎቹ ተለቀዋል ቢባልም ከልጃቸው ጋር ሳይገናኙ እንደቀሩ ያስረዳሉ።

አቶ ሃብቴ እማኙ የተማሪ ግርማ ሃብቴ ወላጅ አባት ናቸው።
ልጃቸው ግርማ ከታገተ በሶስተኛው ቀን በአጋቾቹ ስልክ ደውሎላቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ። "የነበረበትን አልነገረኝም። ብቻ ደህና ነኝ ነው ያለኝ።"
"ተስፋዬ የነበረው እሱ ነው" የሚሉት አቶ ሃብቴ፤ "እናቱ ቤተ-ክርስቲያን እየተንፏቀቀች እኔም የምሰራው ቅጡ ጠፋኝ። ልጄ የሚያውቀው ነገር የለም፤ የቤት ልጅ ነው። እንኳን የሰው አገር የራሱንም አያውቀው። . . . እናቱም የእሱን ሁኔታ አይታ በቤት ውስጥ የሉትን ልጆች ልትመራልኝ አልቻለችም" ይላሉ።
አቶ ሃብቴ "የማደርገው ጠፋኝ፤ ከፍ ብል ሰማይ ዝቅ ብል መሬት ሆኖብኝ፤ የእሱን መከራ ሳላይ ብሞት አይነደኝም ነበር" ይላሉ።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ከታገቱ ተማሪዎች ወላጆች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሬአለሁ ይላሉ። ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ፤ እንደ አገር ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት አናሳ በመሆኑ ፈጥኖ መፍትሔ ማግኘት አልቻለም ባይ ናቸው።
«በተለይም አካባቢውን የሚያስተዳድረው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና የፌዴራሉ መንግሥት ትኩረት መስጠትና ተማሪዎችን ማስለቀቅ አለባቸው» በማለት ለክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
የማሕበራዊ ሚድያ ጩኸት
የተማሪዎች መታገት ከተሰማ ወዲህ ጀምሮ በማሕበራዊ ሚድያዎች በተለይም በፌስቡክና ትዊተር አለፍ ገደም ያሉ ዘመቻዎች መካሄድ ጀምረው ነበር። ከጥቂት ቀናት በፊት ጀምሮ ግን የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ጩኸታቸውን በሰፊው ማሰማት ጀምረዋል።
ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችም ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በተለይ ትዊተር በተሰኘው ማሕበራዊ መድረክ ላይ #Bringourgirlsback #Bringourstudentsback #WhereAreTheStudents? #ተማሪዎችየትገቡ? የተሰኙ ዘመቻዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 3
ፌስቡክ ላይም ያሉ ታዋቂና በርካታ ተከታይ ያሏቸው ኢትዮጵያውያን ድምፃቸውን ስለታገቱት ተማሪዎች ለመናገር እየተጠቀሙበት ነው።
የሚፈልጉት ይዘት የለም
በ Facebook ተጨማሪ ይመልከቱቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.የ Facebook ይዘት መጨረሻ, 1
የሚፈልጉት ይዘት የለም
በ Facebook ተጨማሪ ይመልከቱቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.የ Facebook ይዘት መጨረሻ, 2
ስለታገቱት ተማሪዎች መንግሥት ከጥር 2/2012 ውጭ በይፋ ያለው የለም። የቤተሰቦች ሰቀቀንና የኢትዮጵያውያን ጩኸት ግን ቀጥሏል።
የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት ምዕራብ ኦሮሚያ በኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ ሥር ነው የሚገኘው። አልፎም የቴሌኮም ኔትወርክ ከራቀው ሰነባብቷል።
ተማሪዎቹን ያገታቸው ማነው?
ምንም እንኳ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በጥር 2 ቃለ-ምልልሳቸው ታግተው ከነበሩ አብዛኞቹ ተለቀዋል ቢሉም፤ ተማሪዎቹን ያገታቸው ማነው? ከተለቀቁ የት ነው የሚገኙት? ከወላጆቻቸው ጋር ለምን እንዲገናኙ አልተደረገም? ለሚሉ እና ለሌሎች ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ አልነበረም።
ከዚህ በተጨማሪ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ታግተዋል ያሉት የተማሪዎች ቁጥር እና የፌደራል መንግሥት ከእገታው አስልቅቄያለሁ የሚለው ቁጥር ልዩነት፤ በመንግሥት መካከል በራሱ የመረጃ መጣረስ መኖሩን ያሳያል የሚሉ በርካቶች ናቸው።
አስምራ የታገቱበትን ሁኔታ ስታስረዳ "ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል 'ሱድ' የምትባል ቦታ ላይ ስንደርስ መኪናውን አስቁመው፤ ወጠምሻ ወጣቶች መጥተው አፈኑን። የአፋኞቹ ቁጥር ከእኛ ቁጥር በላይ ነበር" ትላለች። ወጣቶቹ በወቅቱ የጦር መሣሪያ እንዳልታጠቁም ነው የምታስረዳው።
ተማሪዎቹን ያገታቸው የትኛው አካል እንደሆነ በይፋ ባይነገርም፤ የጃል መሮ ነው የሚመራው ኃይል ስለመሆኑ ብዙዎች ግምታቸው አላቸው።
ከተማሪዎቹ መታገት በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቃለ-ምልልስ አድርጎ የነበረው በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የቀድሞ የኦነግ ጦር አዛዥ ዲሪባ ኩምሳ ወይም ጃል መሮ "ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ከእናንተ ነው። የትግል ዓላማችን ከተማሪዎች ጋር አይገናኝም። በተማሪዎቹ ላይም ይህን የተባለውን አይነት ተግባር አልፈጸምንም። እንደተለመደው የእኛን ስም ለማጉደፍ የተወራ ነው እንጂ በፍጽም እንዲህ አይነት ተግባር አሁንም ወደፊትም እንፈጽምም'' ሲል አስተባብሏል።

ቢቢሲ የተማሪዎቹን መታገት ከሰማበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው። ይሁን እንጅ የተሰጠው ውል ያለው ምላሽ የለም።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁንም ሆኑ ቢልለኔ ስዩም፤ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ ብንደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ልናገኛቸው አልቻልንም።
የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌትነት ይርሳውን፣ የሰላም ግንባታና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ ምላሽ አላገኘም።
ስለታገቱት ተማሪዎች በድጋሚ የጠየቅናቸው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ መልሳችሁ ደውሉልኝ ካሉ በኋላ ስልክ ሊያነሱ ፈቃደኛ አልሆኑም።
ስለታገቱት ተማሪዎች ተጨማሪ ዘገባዎችን ለማንበብ፡












