አውሮጳውያን ክርስትያኖች አጥንት በሚቆረጥም ብርድ የጥምቀት በዓል እያከበሩ ነው

የኦርቶዶክስ ክርስትና ዕምነት ተከታዮች የጥምቀት በዓልን ለማክበር በረዶ በሰራ ውሃ ውስጥ እየተጠመቁ ነው።

በኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል በሩሲያና በምስራቅ አውሮጳ አገራት በስፋት ይከበራል።

በዓሉ በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ አቆታጠር ጥር 19 ይከበራል።

በዓሉን ለማክበር በርካታ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በረዶ በሰራ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ይከታሉ። ውሃው ውስጥም ሶስቱን ስላሴዎች ለማሰብ ሦስት ጊዜ ይጠልቃሉ።

ይህች ሴት የሙቀት መጠኑ ከዜሮ በታች 10 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነበት ቅዝቃዜ ውስጥ ሩሲያ ኦምስክ በምትባል ከተማ ውስጥ የጥምቀት ሥነ ስርዓትን እያከናወነች ነው።

ጥምቀቱም ጤናን በማስፈንና ሃጢያትን ያስተሰርያል ተብሎ ይታመናል። ከላይ ያለው ምስል የሚያሳየው በሩሲያ መዲና ሞስኮ ዳርቻ አካባቢ ስቭያቶዬ በተባለ ስፍራ አንድ የኦርቶዶክስ ቄስ ውሃውን ሲባርኩት የሚያሳይ ነው።

አማኞች እንደሚሉት የጥምቀት ዕለት ሁሉም ውሃ ቅዱስ ይሆናል። በሌላ በኩል አንዳንዶቹ የቀዘቀዘው ውሃ ለጤና ጠቃሚ ነው ይላሉ። ከላይ የምንመለከታቸው ምዕመናን ከጥምቀት በኋላ ለፎቶ ተሰባስበው ነው።

እነዚህ እስረኞች በኦምስክ በከፍተኛ ጥበቃ ውስጥ ሆነው ለጥምቀቱ እራሳቸውን ወደ ጥልቁ የውሃ ጉድጓድ ሲወረውሩ የእስር ቤቱ ጠባቂዎች እየተመለከቱ ነው።