የስምንት ዓመት ልጁን በዕፅ አዘዋዋሪነት የመለመለው ግለሰብ ታሠረ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የጣልያን ፖሊስ የስምንት ዓመት ልጁን ለዕፅ አዘዋዋሪነት መልምሏል ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አዋለ።
አውገስቲኖ ካምባሪሪ የተባለው የ46 ዓመት ግለሰብ፤ የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ሲሆን፤ ልጁ ቡድኑን በምን መንገድ ማገዝ እንደሚችል ይነግረው እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።
ታዳጊው ገበያ ላይ በሚገኙት ዕፆች መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ እንዲረዳ ስልጠና እንተሰጠውም ተነግሯል።
የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድኑ አባላት የሚግባቡበትን የሚስጥር ቋንቋም አባት ለልጁ አስተምሯል ተብሏል።
ከአውገስቲኖ ካምባሪሪ በተጨማሪ 13 ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ተጠርጣሪዎቹ ካላቢራ በተባለችው የጣልያን ግዛት ካናቢስ እና ኮኬይን ያዘዋውሩ ነበር ተብሏል።












