ድሬ ዳዋ ስለሚገኙት የለገ ኦዳ የዋሻ ሥዕሎች ያውቃሉ?

የለገ ኦዳ ዋሻ
የምስሉ መግለጫ, የለገ ኦዳ ዋሻ

ከድሬ ዳዋ ከተማ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የለገ ኦዳ ዋሻ ወደ 600 የሚጠጉ ጥንታዊ የዋሻ ሥዕሎች ይገኙበታል። በ1920ዎቹ አካባቢ በተመራማሪዎች ዕውቅና እንዳገኙ የሚነገርላቸው የዋሻ ሥዕሎች ከ7,000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

በብዛት በቀይ፣ በቢጫና ግራጫ ቀለም ከተሠሩት ሥዕሎች መካከል የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳ ቁሶች እንዲሁም እንስሳት የሚያሳዩት ይገኙበታል።

የድሬ ዳዋ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ባለሙያ የሆኑት አቶ ደረጄ ታደሰ፤ ሥዕሎቹ ጥንት በአካባቢው ይኖሩ በነበሩ ሰዎች እንደተሠሩና፤ የአኗኗር ዘይቤያቸውን እንደሚያሳዩ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ሥዕሎቹ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋም እንደተጋረጠባቸው አቶ ደረጄ ተናግረዋል። ዋሻ ሥር የሚገኙት ሥዕሎች በዝናብ ሳቢያ እየደበዘዙ መጥተዋል። በሰው ንክኪ ምክንያትም የቀድሞ ይዘታቸውን እያጡ ነው።

አቶ ደረጄ እንደሚሉት፤ ቅርሱ በአግባቡ ባለመያዙ የአገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል።

ቅርሱን ከዝናብ ለመከላከል መጠለያ ቢሠራም፤ የበለጠ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ባለሙያው ተናግረዋል። የቢቢሲ ባልደረባ ወደሥፍራው አቅንቶ ካነሳቸው ፎቶግራፎች የሚከተሉት ይገኙበታል።

በለገ ኦዳ ዋሻ ከሚገኙት ጥንታዊ ሥዕሎች አንዱ
የምስሉ መግለጫ, በለገ ኦዳ ዋሻ ከሚገኙት ጥንታዊ ሥዕሎች አንዱ
በቢጫና ግራጫ ቀለም ከተሠሩት ሥዕሎች መካከል የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳ ቁሶች እንዲሁም እንስሳት የሚያሳዩት ይገኙበታል
የምስሉ መግለጫ, በቢጫና ግራጫ ቀለም ከተሠሩት ሥዕሎች መካከል የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳ ቁሶች እንዲሁም እንስሳት የሚያሳዩት ይገኙበታል
የዋሻ ሥዕሎቹ ከ7,000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ ይነገርላቸዋል
የምስሉ መግለጫ, የዋሻ ሥዕሎቹ ከ7,000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ ይነገርላቸዋል
በዋሻው ውስጥ ወደ 600 ሥዕሎች ይገኛሉ
የምስሉ መግለጫ, በዋሻው ውስጥ ወደ 600 ሥዕሎች ይገኛሉ
ሥዕሎቹ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋም ተጋርጦባቸዋል
የምስሉ መግለጫ, ሥዕሎቹ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋም ተጋርጦባቸዋል
ሥዕሎቹን ከዝናብ ለመከላከል የተሠራው መጠለያ
የምስሉ መግለጫ, ሥዕሎቹን ከዝናብ ለመከላከል የተሠራው መጠለያ
የለገ ኦዳ ዋሻ
የምስሉ መግለጫ, የለገ ኦዳ ዋሻ
የዋሻ ሥዕሎቹ በ1920ዎቹ አካባቢ በተመራማሪዎች እውቅና ማግኘታቸው ይነገራል
የምስሉ መግለጫ, የዋሻ ሥዕሎቹ በ1920ዎቹ አካባቢ በተመራማሪዎች እውቅና ማግኘታቸው ይነገራል