ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አውስትራሊያ፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ እንቁላል ተወረወረባቸው
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንቁላል ተወረወረባቸው።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሀገሪቱ ምርጫ አስቀድመው ቅስቀሳ ሲያድጉ ነበር በእንቁላል የተመቱት።
የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት፤ እንቁላሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ ካረፈ በኋል ሳይሰበር ወድቋል።
ክስተቱን ተከትሎም አንዲት የ25 ዓመት ሴት በቁጥጥር ስር መዋሏ ተሰምቷል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ድርጊቱን "እፍርታምነት ነው" ብለው፤ ጠባቂዎቻቸው ነገሩን በፍጥነት በቁጥጥር ስር በማዋላቸው አመስግነዋቸዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን በሀገሪቱ የሴቶች ማኅበር ውስጥ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት ነበር በእንቁላል የተመቱት። በቦታው ሌላ ምንም ጉዳት አለመድረሱ ተዘግቧል።
ስኮት ሞሪሰን በዚህ ዓመት በእንቁላል የተመቱ ብቸኛው አውስትራሊያዊ ፖለቲከኛ አይደሉም።
ፍራስተር አኒንንግ የተባሉ ፖለቲከኛ በኒውዝላንድ መስጊድ ውስጥ ስለደረሰው ጥቃት አወዛጋቢ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ እንቁላል ተወርውሮባቸው ነበር።
በወቅቱ አንድ የ17 ዓመት ወጣትን ፖሊሶች ተጠያቂ አድርገዋል።
የአውስትራሊያ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከሰባት ቀን በኋላ ይካሄዳል።