እስራኤል፦በዌስት ባንክ ዘጠኝ ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ጭምብል ተገኘ

በዌስት ባንክ የተገኘው ዘመን ተሻጋሪ ጨምብል

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty

በዓይነታቸው የተለየዩና በአለም ላይ 15 ብቻ ከሆኑ የጭምብል አይነቶች አንዱ በዌስት ባንክ መገኘቱን እስራኤል አስታወቀች።

ዘመን ተሻጋሪው ጭምብል የተገኘው በእስራኤል ይዞታ ስር በሚገኘው የዌስት ባንክ ክፍል ሄብሮን በተሰኘ ቦታ ነው።

ከብርቱካናማና ቢጫ ድንጋይ የተሰራው ጭምብል በአሁኑ ወቅት በእስራኤል ቅርስ ጥበቃ ተቋም እንዲገባ ተደርጓል።

በቅርስ ተቋሙ የቅርስ ተመራማሪ የሆኑት ሮኒት ሉፑ "ጭምብሉ በጣም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ የተሰራ ነው" ብለዋል።

ባለሙያዋ እንደሚገምቱት ጭምብሉ ምናልባትም ጥንት ከሃይማኖታዊ በአላት አከባበር ላይ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነው።

ጭምብሉ ላይ ያሉ ቀዳዳዎች ሲታዩ ደግሞ ለእይታ ይሰቀል እንደነበር ያመለክታል። ጭምብሉ የሰው ዘር አዳኝና ፍራፍሬ ለቃሚ በነበረበት ዘመን የይጠቀምበት እንደነበር ተመራማሪዋ ግምታቸውን ይናገራሉ።

አለም ላይ ካሉት ከነዚህ 15 ጨምብሎች 13 የሆኑነት በግለቦች እጅ የሚገኙ መሆኑ የጭምብሎቹ ዓይነት ላይ በቂ ምርምር ማድረግ እንዳይቻል አድርጓል።

እስካሁን የተደረጉ ምርምሮች ውጤት ግን በቀጣዩ ሳምንት በእየሩሳሌም የእስራኤል ሙዚየም ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል።