ስለ ወንዶች ፊስቱላ ምን ያህል ያውቃሉ?

በአብዛኛው ፊስቱላ ሴቶችን የሚያጋጥም የጤና እክል ተደርጎ ይታሰባል። ነገር ግን የፊስቱላ ችግር ወንዶችንም ሊገጥም እንደሚችል በተለይ በፊስቱላ ህክምና ላይ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ዌስተን ኪሳ በተከታይነት በዝርዝር ያብራራሉ።

ከእውቀት ማነስ አይደለም የሚመጣው። ምክንያቱም ወንዶች በቤት ውስጥ ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን ስላላቸውና ከሴቶች በተሻለ በፈለጉ ጊዜ የጤና ባለሙያ ማማከር ይችላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ። ከዚህ በተጨማሪም የወንዶች የትምህርት ደረጃ ከፍ ያለ ስለሆነ መረጃ በቀላሉ ይደርሳቸዋል።

የወንዶች ፊሰቱላ እንዴት ይከሰታል?

ከፕሮስቴት እጢ እና ከፕሮስቴት እጢ አላግባብ መተለቅ ጋር እንደሚያያዝ ይታሰባል። የእጢው ካንሰር አንዳንድ ጊዜ ከወንዶች እድሜ መጨመር ጋር አብሮ ይመጣል።

ህጻናት ሲወለዱ ጀምሮ የሽንት ቧንቧቸው ከትክክለኛ ቦታው ዝቅ ወይም ከፍ ብሎ ከተወለዱ ፊስቱላ ሊከሰት ይችላል።

ይህ ማለት ወንዶች የሽንት ፊኛቸው ከሞላ ሽንታውን መቆጣጠር አይችሉም ማለት ነው።

ሌላኛው ወንዶችን ለፊስቱላ ሊያጋልጣቸው የሚችለው በግብረ-ሥጋ የሚተላለፉ በሽታዎች ናቸው። በሽታው ምቾት ይነሳል፤ ከጀርባ ጀምሮ እስከ ሽንት ቧንቧ ድረስ ህመም ያስከትላል።

የወንዶች ፊስቱላ ተጠቂዎች ልጅ ለመውለድ አስጋሪ ሊሆንባቸውም ይችላል።

ወንዶች ፊስቱላ ምልክቶች ምንድናቸው?

ፊስቱላ ያለበት ወንድ ሽንቱን መቆጣጠር ስለማይችል እንደሴቶች ተቀምጦ መሽናት አለበት።

የሽንት ቧንቧቸውም ከተደፈነ መሽናት ከባድ ይሆንባቸዋል። ይህ ችግር በጣም ህመም አለው። ስለዚህ ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መሄድ ይኖርባቸዋል። ህክምናው በመድሃኒት አልያም በቀዶ ጥገና ሊታከም ይችላል።

ከተለመደው ወጣ ያለ የሽንት ቧንቧ አፈጣጠር ያላቸው ህጻናት በቀዶ ትገና ሊድኑ ይችላሉ።