บทเรียน 1: How do I...
เลือกบทเรียน
- 1How do I...
- 2Unit 2
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
บทเรียนย่อย 3
Listen to find out how to talk about your likes and dislikes.
ስለሚወዷቸው እና ስለማይወዷቸው ነግሮች እንዴት መናገር እንደሚችሉ ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
แบบฝึกหัด 1
How do I talk about likes and dislikes?
ቃላቱን/ሐረጎቹን በጣም አዎንታዊ ከሆነው በጣም አሉታዊ ወደሆነው በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
- don’t like
- like
- really hate
- love
- don’t mind
መልሶዎን ለማጣራት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። ከዚያ ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩት።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ ‘How do I…’ ዝግጅታችን ደደህና መጡ። አዘጋጆቹ እኔ ዘሩባቤል እና ሳም ነን።
Sam
Hello, everybody. Welcome!
ዘሩባቤል
በዚህ ክፍል መውደድ እና አለመውደዳችንን የምንገልፅባቸውን መንገዶች እናያለን። የተወሰኑ ሰዎች ስለ ቡና ሲያወሩ በማዳመጥ እንጀምር። ሁሉም ነገር ባይገባዎት ብዙም አይጨነቁ፤ በኋላ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ግን ከሁሉም በበለጠ የትኛው ሰው ቡና እንደሚወድ ብቻ ወስኑ።
I like coffee.
I love coffee.
I don’t mind coffee.
I really hate coffee!
ዘሩባቤል
ሰማችሁት? አዎ፥ የመጨረሻው ሰው ስለቡና በጣም ጠንካራ ስሜት አለው! ስለዚህ ሳም እስቲ መውደዳችንን እና አለመውደዳችንን የምንገልፅባቸውን መንገዶች እንመልከት?
Sam
Yes, let’s do it!
ዘሩባቤል
በእነዚህ አረፍተ ነገሮች ሁሉ ሰዎች የሚያወሩት ስም ስለሆነው ስለ ‘coffee’ ነበር። የመጀመሪያው ተናጋሪ ስለ ቡና ለማውራት የተጠቀመው ቃል ምንድን ነው? እስኪ ደግመን እናዳምጠው።
I like coffee.
ዘሩባቤል
ጥቅም ላይ የዋለው ግስ መውደድ ‘like’ ነው። የ ‘like’ ን ተቃራኒ መግለፅ ከፈለጉ ከፊቱ ‘don’t’ የሚለውን ቃል ያስገባሉ። ስለዚህም እንዲህ ይሆናል ማለት ነው። ‘I don’t like coffee.’
Sam
Now, let’s quickly practise the pronunciation together! Repeat after me:
‘I like coffee.’
‘I don’t like coffee.’
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! ቀጣዩ ተናጋሪ ሌላ ግስ ነው የተጠቀመው። የትኛውን እንደሆነ ለመለየት በድጋሚ እንስማው።
I love coffee.
ዘሩባቤል
‘Love’። ይህ ከlike የበለጠ ጠንካራ ስሜት ነው?
Sam
Yes, it is! Let’s practise the pronunciation together. Repeat after me:
‘I love coffee.’
ዘሩባቤል
ቀጥሎ ተናጋሪውን እናዳምጥና ቀጣዩ ሐረግ ምን እንደሆነ እንለይ።
I don’t mind coffee.
ዘሩባቤል
እሺ፤ ይህ ሰው የተጠቀመው ‘don’t mind’ ብዙም ግድ አይሰጠኝም የሚለውን ሐረግ ነው፤ ይህም ስሜታቸው በጣም አሉታዊ ወይንም አዎንታዊም አይደለም ማለት ነው፤ መሃል ላይ ናቸው። ከ‘like’ የተለየ በሆነው በዚህ አጋጣሚ ሁሌጊዜም ‘don’t’ አብረን እንጠቀማለን።
Sam
And let’s practise the pronunciation together. Repeat after me:
‘I don’t mind coffee.’
ዘሩባቤል
And we have one more! የመጨረሻው ሰው ስለ ቡና ምንድን ነው ያሉት?
I really hate coffee!
ዘሩባቤል
‘Really hate’ በጣም ነው የምጠላው ነው ያሉት። ‘hate’ ብቻውን መጠቀም ይችላሉ፤ ‘really’ ጨምረው ከተጠቀሙ ግን ያ ስሜት የበለጠ ጠንካራ ይሆናል ማለት ነው። ‘really’ ከ ‘like’ እና ‘love’ በፊት በመጠቀም የሚገልፁትን አዎንታዊ ስሜት የበለጠ ጠንካራ ያደርገዋል ከ ‘don’t like’ በፊት መጠቀም ደግሞ የሚገልፁትን አሉታዊ ስሜት የበለጠ ጠንካራ ያደርገዋል።
Sam
Yes, so you can say ‘I really like coffee’ or ‘I really love coffee’. The way you say ‘really’ is important here, so let’s practise together. Repeat after me:
‘really’
‘I really hate coffee!’
‘I really love coffee!’
ዘሩባቤል
Thanks, Sam! አሁን መውደድ እና አለመውደድን የምንገልፅባቸውን እነዚህን ሁሉ መንገዶች ተምረዋል፤ ስለዚህም አሁን የመለማመጃ ሰዓት ነው።
‘Chocolate’ ቼኮሌት በጣም እንደሚወዱ ያስቡ፤ ስሜትዎ በጣም አዎንታዊ ስለሆነ ‘really’ መጠቀም አይርሱ። በኋላ ላይ ለንፅፅር የሳምን ምላሽ ያዳምጣሉ።
Sam
I really love chocolate.
ዘሩባቤል
Did you say the same? ስሜቱ እንደዚያኛው ጠንካራ አይሆንም እንጂ ‘I really like chocolate’ ሊሉ ይችሉ ነበር።
አሁን ስሜትዎ የ ‘like’ ተቀራኒ ሆኖ ‘hate’ እስኪባል ድረስ ግን ጠንካራ እንዳለሆነ ያስቡ። ስለ ‘chocolate’ምን እንደሚያስቡ ይንገሩን። በኋላ ላይ ለንፅፅር የሳምን ምላሽ ያዳምጣሉ።
Sam
I don’t like chocolate.
ዘሩባቤል
Did you say the same?
Sam
Well done! Now you know how to talk about things you ‘love’, ‘like’, ‘don’t mind’, ‘don’t like’ and ‘hate’, find a friend and tell them about the foods you like and don’t like!
ዘሩባቤል
Good idea! We really like it when you practise! Bye!
Sam
Bye!
Learn more!
1. የ'like' ተቃራኒ ምንድን ነው?
Don’t like.
2. 'Love' እና 'hate' ከ'like' እና 'don’t like'የበለጡ ጠንካራ ስሜቶችን ይገልፃሉ?
አዎ 'love' ከ 'like' የበለጠ፥ 'hate' ደግሞ ከ 'don’t like' የበለጠ ጠንካራ ስሜትን ይገልጻሉ።
3. 'Love' እና 'hate' ከዚህም በበለጠ ጠንካራ ማድረግ እንችላለው?
አዎ፤ 'really' በመጠቀም ስሜቶችን የበለጠ ጠንካራ ማድረግ እንችላለን። 'really' ከ 'like' እና 'don’t like' እንዲሁም በፊት መጠቀም ይችላሉ።
4. 'Don’t mind' አሉታዎ ስሜት ነው?
አይደለም፤ ምንም እንኳ ሐረጉ 'don’t' ቢጠቀምም፥ አሉታዊ ስሜትን ይገልፃል ማለት አይደለም። 'don’t mind' ከተጠቀሙ ስለአንዳች ነገር አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ስሜት የለዎትም ማለት ነው፤ የሚወራለት ጉዳይ ለእርስዎ እምብዛም ስሜት ኤእሰጦትም ማለት ነው።
How do I talk about likes and dislikes?
4 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
คำใบ้
ያስታውሱ! ይህንን ቃል የምንጠቀመው አሉታዊ ለማድረግ ነው።Question 1 of 4
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
คำใบ้
ይህ በጣም አዎንታዊ ስሜትን የሚገልፅ ነው።Question 2 of 4
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
คำใบ้
አዎንታዊ ስሜትን ይገልፃል።Question 3 of 4
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
คำใบ้
ይህ ቃል በጣም ጠንካራ የሆነ አሉታዊ ስሜትን ይገልፃል።Question 4 of 4
Excellent!เยี่ยม!แย่หน่อย!คุณทำคะแนนได้:
Tell us what foods you like and dislike on our Facebook group!
ምን ዓይነት ምግቦችን እንደሚወዱ እና እንደማይወዱ በፌስቡክ ቡድናችን ይግለፁልን።
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ አጠቃቀሞችን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ How do I... ክፍላችን ይጠብቁን።
Session Vocabulary
I like…
እወዳለሁI don’t like…
አልወድምI love…
አጥብቄ እወዳለሁ፥ አፈቅራለሁI hate…
እጠላለሁI don’t mind…
ምንም አይመስለኝምreally
ከምርcoffee
ቡና
chocolate
ቡና