Essential English Conversation :1واحد
انتخاب واحد
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
جلسه 19
Listen to find out how to ask someone about their favourite place.
ሰዎችን ስለሚወዷቸው ቦታዎች እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
Session 19 score
0 / 3
- 0 / 3تمرین 1
تمرین 1
What’s your favourite place?
Listen to find out how to ask someone about their favourite place.
ሰዎችን ስለሚወዷቸው ቦታዎች እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ምህረት
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊተዋቸው የማይቻላቸውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ምህረትእባላለሁ። በዚህ ክፍል በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በጣም ስለሚወዱት ቦታ እንዴት መናገር እንደሚቻል ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች ስለሚወዷቸው ቦታዎች ሲያወሩ ያዳምጡ።
Sian
Hi Phil, what’s your favourite place?
Phil
My favourite place is the market. How about you?
Sian
Mine is the restaurant.
ምህረት
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ‘የምትወደው ቦታ የትኛው ነው?’ ‘What’s your favourite place?’ በማለት ነው የጠየቀችው። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
What’s your favourite place?
ምህረት
ሁለተኛው ተናጋሪ የሚወደው/የሚመርጠው ‘favourite’ ቦታ ገበያው ‘market’ እንደሆነ መልሶላታል። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይናገሩ።
My favourite place is the market.
ምህረት
ከዚያም የመጀመሪያዋን ተናጋሪ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቃት። አንድ ሰው የጠየቀዎትን ጥያቄ እራሱን እንዲመልስልዎት ከፈለጉ ‘እንችስ/አንተስ?’ ‘How about you?’ በማለት መጠየቅ ይችላሉ። ያዳምጡና ሐርጉን ደግመው ይበሉ።
How about you?
ምህረት
ስለምንወዳቸው ቦታዎች እያወራን እንዳለን ስለምናውቅ የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ደግማ ‘የምወደው/የምመርጠው ቦታ’ ‘My favourite place…’ ማለት አልተጠበቀባትም። እንዲሁ ብቻ ‘የእኔ’ ‘mine’ ‘ምግብ ቤቱ’ ‘restaurant’ ነው ብላለች። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Mine is the restaurant.
ምህረት
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ስለሚወዷቸው ስፍራዎች ሲያወሩ በማዳምጥ እርስዎ ያሉትን ይፈትሹ።
ማርክ ‘የመናፈሻ ስፍራውን’ ‘park’ ይወዳል፤ ፒት ደግሞ ‘ወንዙን’ ‘river’ይመርጣል።
Hi Mark, what’s your favourite place?
My favourite place is the park. How about you?
Mine is the river.
አሊስ የፖስታ ቤቱን ‘የመዋኛ ገንዳ’ ‘swimming pool’ ትወዳለች። የክሌር ተመራጭ ቦታ ደግሞ ‘ሲኒማ ቤቱ’ ‘cinema’ ነው።
Hi Alice, what’s your favourite place?
My favourite place is the swimming pool.
Mine is the cinema.
ምህረት
እሽ፥ አሁን ደግመን እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሩን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ይሰሟቸዋል።
What’s your favourite place?
What’s your favourite place?
My favourite place is the market.
My favourite place is the market.
How about you?
How about you?
Mine is the restaurant.
Mine is the restaurant.
ምህረት
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱት እንመልከት። አረፍተ ነገራቱን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይናገሩ።
ከሁሉ አስበልጠህ የምትወደው ቦታ የትኛው ነው?
What’s your favourite place?
እኔ የምወደው ገበያውን ነው።
My favourite place is the market.
አንችስ?
How about you?
እኔ ምግብ ቤቱን ነው።
Mine is the restaurant.
ምህረት
በጣም ጥሩ፤ እሽ አሁን በእንግሊዝኛ ስለቦታዎች መጠየቅ እና መመለስ እንደሚቻል አውቀዋል። ለመጀመሪያው ተናጋሪ ምላሽ በመስጠት፥ አቅጣጫ እየጠየቁ ልምምድ ያድርጉ።
What’s your favourite place?
Mine is the restaurant.
ምህረት
በጣም ጥሩ፤ አሁን መልስዎን ለማመሳከር ጠቅላላውን ውይይት እንደገና ያዳምጡ።
Sian
Hi Phil, what’s your favourite place?
Phil
My favourite place is the market. How about you?
Sian
Mine is the restaurant.
ምህረት
በጣም ጥሩ። አሁን በእንግሊዝኛ በሚኖሩበት ከተማ ስለሚወዱት ቦታ መጠየቅ እና መናገር ይችላሉ። የተማሩትን መለማምድን ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ስማችሁን መጠየቅና መናገርን ይለማመዱ። ለተጨማሪ የEssential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
What’s your favourite place?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
تمرین
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
እኔ፥ እኔን፥ የእኔን።Question 1 of 3
Help
تمرین
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
እኔ፥ እኔን፥ የእኔQuestion 2 of 3
Help
تمرین
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ነውን በእንግሊዝኛ የሚሉት እንዴት ነው?Question 3 of 3
Excellent!آفرین! نمره شماBad luck!:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
واژه های تازه این جلسه
What’s your favourite place?
የምትወጅው/የምትወደው ቦታ የትኛው ነው?
My favourite place is ______.
የምወደው ቦታ ______ ነው።
the market
ገበያው
the restaurant
ምግብ ቤቱ
the park
መናፈሻው
the river
ወንዙ
the swimming pool
መዋኛ ገንዳው
the cinema
የሲኒማ አዳራሹ
the city centre
የከተማ ማዕከሉ
the beach
የባህር ዳርቻው